የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሰልጣኞቹን አስመረቀ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሰልጣኞቹን አስመረቀ፡፡

በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የአብያተ መዛግብትና አብያተ መጻሕፍት ስልጠናና ምክር መሪ ስራ አስፈጻሚ ከመጋቢት 8/2016 ዓ.ም እስከ መጋቢት 13/2016 ዓ.ም በሪከርድ ስራ አመራር ምንነት እና በመረጃ ሀብቶች ጥበቃና እንክብካቤ ዙሪያ ያሰለጠናቸውን በቁጥር  49 ሰልጣኞች መጋቢት 13/2016 ዓ.ም አስመርቋል።

ሰልጣኞቹም ከፌደራል ተቋማትና ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ እንደሆኑ ስልጠናውን ሲሠጥ የነበረው የተቋሙ አብያተ መዛግብትና አብያተ መጻሕፍት ስልጠናና ምክር መሪ ስራ አስፈጻሚ አሳውቋል፡፡

በምርቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአገልግሎቱ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው ከስልጠናው ያገኛችሁትን እውቀቱንና ክህሎቱን እንኳን ብትተውት ስራውን ግን በሰለጠናችሁት ልክ ተግባራዊ በማድረግ ሰርታችሁበት የየተቋማቱ መዛግብቶቹ በአግባብ ተይዘውና ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ ግን የበኩላችሁን እንድትወጡ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈው ስልጠናውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች ከተቋሙ የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀት በማበርከት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

Share this Post