የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ጋር ጥር 29/2016 ዓ.ም የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት አገልግሎት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳው እና ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሰንበቶ ቡሻ ሲሆኑ በፊርማው ወቅትም የሪፍት ቫሊ ዩንቨርሲቲ የጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሰንበቴ ቡሻ እንደተናገሩት የሪፍት ቫሊ ዩንቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋምነቱ ለሀገር እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦና በሀገሪቱ ባሉት 52 ካምፖሶቹ በርካታ ለሀገር የሚጠቅም ዜጎችን እያፈራ የሚገኝ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ ለጥናትና ምርምር ስራውም መረጃ አስፈላጊ በመሆኑ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ይህንን ተግባሩን ለማስፈጸም ሀብቱን ማግኘት የሚችለው ለ80 ዓመታት የሀገሪቱን ማናቸውም ሀብቶች ጠብቆና ተንከባክቦ ከሚገኘው ከአንጋፋው ተቋም ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት መሆኑን በመረዳት እንደ አማራጭ በጋራ ለመስራት ከያዟቸው በርካታ ተቋማት መካከል መርጠው እንደመጡ ተናግረዋል፡፡

በመቀጠልም ንግግር ያደረጉት ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳውም  እንደተናገሩት ትልቅ ሀብት የሆነውን የሰው አዕምሮ ማልማት ስራ ላይ በመስራታችን፣ የጥናትና ምርምር ስራ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እንደመሆኑ በተለይም ቀዳሚ የመረጃ ሀብቶችን በማሰባሰብና አደራጅቶ ለትውልድ በማስጠበቃችን፣ እንዲሁም የአንድን ህዝብ ታሪክ በሰነድ ለማስቀመጥ አንድ ተቋም ብቻ በቂ ስለማይሆን በስፋት ቤተ መዛግብት እንዲከፈቱ የምናደርገው እንቅስቃሴ በጋራ እንድንሰራ የዓላማ ትስስር እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በሰነድ መፈራረሙ ላይ የተሳተፉት ተቋማቶቹን ወክለው የተገኙ ተሳታፊዎች የየግላቸውን ሃሳብ አስተያየት ካቀረቡ በኃላ የመግባቢያ ሰነዱ በአቶ አባተ ካሳው እና በዶ/ር ሰንበቴ ቡሻ ተፈርሞ ዝግጅቱ  ሲጠናቀቅ እንግዶቹም የተቋሙን መዛግብት ክፍል ጎብኝተዋል፡፡

Share this Post