የኢትዮጽያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአርባ ምንጭ ከተማ "አርባ ምንጭ ታንብብ" በሚል መሪ ቃል የንባብ ሳምንት ተካሄደ::

የኢትዮጽያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአርባ ምንጭ ከተማ "አርባ ምንጭ ታንብብ" በሚል መሪ ቃል የንባብ ሳምንት ተካሄደ::

የኢትዮጽያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ እና ከጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ "አርባ ምንጭ ታንብብ" በሚል መሪ ቃል ከጥር 18 2016ዓ.ም ጀምሮ የንባብ ሳምንት፣ ቡክፌር፣ ኤግዚቢሽን እና የፓናል ውይይት አዘጋጀ::

በአርባ ምንጭ ከተማ “ጋሞ አደባባይ” በተዘጋጀው  ቡክፌርና ኤግዚቢሽን  አከባቢዉን የሚገልፁ ጥንታዊ የጽሑፍ ቅርሶች  መዛግብትና የፎቶ አውደርዕይ ተጐብኝቷል እንዲሁም የህፃናት የንባብ ኤግዚቢሽን ተካሂዷል ::

በመክፈቻ መርሀ ግብሩም  የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ኘሬዝዳንት ዶ/ር ዳምጠው ደርዛ የኢትዮጽያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ያሬድ ተፈራ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የማህበራዊ ሳይንስ ተባባሪ ኘሮፌሰር በሀይሉ መርደኪዮስ እና ሌሌች ተጋባዥ እንግዶች ደራሲዎች ተማሪዎችና የከተማው ወጣቶች ታድመዋል::

ዶ/ር ዳምጠው ደርዛ በመክፈቻ ንግግራቸው ኘሮግራሙ ንባብን ያገዘፈ ከፍ ያለ ዓላማ ያለው ነው ያሉ ሲሆን የሚጐበኙትን ታሪካዊ ቅርሶች ከፍ አርገን ማየት አለብን ብለዋል::

አቶ ያሬድ ተፈራ በንግግራቸው ዓላማው ለትምህርት ቤቶችና ለህዝብ ቤተ መጻሕፍት መጻሕፍት በመለገስ የንባብ ባህልን ማሳደግ ነው ብለው የአርባ ምንጭ ማረሚያ ቤትና  የጨንቻ ማረሚያ ቤት የፕሮግራሙ አካል እንደሆኑ ገልፀዋል::

ተባባሪ ኘሮፌሰር በሀይሉ መርደኪዮስ በእንኳን ደና መጣችሁ ንግግራቸው የኢትዮጽያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎትን በዚህ የንባብ ባህል እየቀነሰ በመጣበት የዲጂታል ዘመን የንባብ ባህል ለማሳደግ በመምጣታችሁ እናመሰግናለን ያሉ ሲሆን ንባብ ከዕዉቀት በተጨማሪ ርህራሄን ፈጠራን እና የማሰብ ችሎታን ያሳድጋል ብለዋል::

በመጨረሻም ደራሲ ዘነበ ኦላ ለተማሪዎችና ወጣቶች ህሊናችሁ እንዲገራ አካላችሁ እንዲፍታታ በቀን 15 ደቂቃ ከማንበብ ጀምሩ በማለት ጥናታዊ ጽሑፎችን በማጣቀስ መክረዋል::

Share this Post