የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ::
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ::
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድጋ ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ሲሆኑ ይህ የመግባቢያ ሰነድ ተቋማቱ ከዚህ ቀደም የነበራቸውን የመረጃ ሀብትን ለዜጎች ተደራሽ የማድረግ ስራን በማጠናከር ከጥናት አጥኚዎችና ተመራማሪዎች ባለፈ ለወጣቱ የትምህርትና ግንዛቤ ማስፋፋቱን ስራ ለማሳዳግ እንደሚያስችል ተገልጿል።