በህፃናት የተረት መጽሐፍት ዙሪያ ንባብ ሳይንሳዊ ገለጻ እና ውይይት ተደረገ!

በህፃናት የተረት መጽሐፍት ዙሪያ ንባብ ሳይንሳዊ ገለጻ እና ውይይት ተደረገ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከኢትዮጵያን ሪድስ ጋር በመሆን "ጥራት ያለው የህፃናት የተረት መጽሐፍት ለህፃናት የግንዛቤ ክህሎት እድገት ያለው ሚና" በሚል ርዕሰ ጉዳይ የሳይንሳዊ ገለጻ እና ውይይት መርሐ ግብር ሕዳር 11/ 2016 ዓ.ም በዋቢ ሸበሌ ሆቴል አካሂዷል።

የኢትዮጵያን ሪድስ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር የምስራች ወርቁ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ይህ መርሐግብር የህፃናት መጽሐፍት ላይ የሚሰሩ ስራዎችን ለማጠናከር እና ከቀዳማይ ልጅነት ጀምሮ ያለው የንባብ ሂደት ምን ይመስላል? ምን አስተዋጽኦ አለው? ምን ላይ ትኩረት ይሰጥ የሚለውን ከሳይንሱ አንጻር ያለውን እውነታ በማስተሳሰር ለመወያየት የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የመወያያ ጽሑፉ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዶክተር የግዛው ኃይሌ ሲቀርብ የመወያያ ጽሑፉም የልጆች የባህሪ ሒደትን የተመለከቱ እንዲሁም የንባብ ክሒላቸውንና የትምህርት አሰጣጥን በተመለከከተ ከቀዳማይ ልጅነት ጀምሮ ያላቸው የንባብ ሂደት ምን እንደሚመስል መምህራንና ወላጆች ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲሁም አስተዋእጾዋቸውን ያመላከተ ጽሑፍ ቀርቦ ሰፊ ገለጻ ተደርጓል፡፡

በመርሐ ግብሩ የተሳተፉ ንባብ ላይ ትኩረት በማድረግ የሚሰሩ የግልና የመንግስት ተቋማቶች፣የልጆች መጽሐፍት ጸሐፊያን እንዲሁም በህጻናት ዙሪያ የሚሰሩ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች፣ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራን ሲሳተፉ በዕለቱም በርካታ ጥያቄዎች፣ሃሳብ አስተያየቶች ሲቀርቡ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንባብን ከቅድመ ልጅነት ጀምሮ ልጆች ላይ ለመስራት የተጀመሩ ጅማሮዎች ተሞክሮ ሲቀርብ ሀገሬቷን በንባብ የተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ግን ብቻ መስራት አማራጭ ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበትና በዘርፉ የሚሰሩ የሚድያ አካላትንም ጨምሮ በጋራ በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ከበርካታ ተሳታፊዎች ሃሳብ ተሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም ለተነሱ ጥያቄዎችና ሃሳብ አስተያየቶች በዶክተር የግዛው ምላሽ ተሰጥቶ ንባብ ላይ የሚሰሩ የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማት ብቻ ለብቻ ከመስራት ትምህርት ሚኒስቴርም ትኩረት ሰጥቶት በቅንጅት መሰራት እንዳለበት በማሳሰብ እና ለእይታ የተዘጋጁ የህጻናት መጽሐፍት ተጎብኝተው የዕለቱ መርሐ ግብር ተጠናቋል፡፡

Share this Post