የልጆች የንባብ መርሐ ግብር ተከናወነ

የልጆች የንባብ መርሐ ግብር ተከናወነ!

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው የንባብ ልምድ መዳበር እንቅስቃሴ አንዱ የሆነውን የልጆች የንባብ መርሐ ግብር በተቋሙ የህጻናት ቤተ መጻሕፍት ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም አከናወነ።

በዚህ መርሐ ግብር ከዶምቦስኩ ት/ቤት የመጡ ተማሪዎችና ለማንበብ በቤተ መጻሕፍቱ የተገኙ ህጻናት ተካፍለዋል።

ይህ መርሐ ግብር በኮሜዲያንነትና የልጆች መጻሕፍት በመጻፍ የሚታወቀው አስረስ በቀለና ከልጆች ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ስራን የሚሰሩት ሳምራዊት ተሬሳ እና ብጽአት ተስፋዬ አማካኝነት የተረት ነገራ እንዲሁም በጣም አስተማሪና አዝናኝ ጨዋታዎችን ያካተተ ነበር።

በእለቱ መልካም ተሳትፎ ላደረጉ ተማሪዎችም ከተቋሙ የመጻሕፍት ስጦታ ተበርክቷል።

Share this Post