የተማሪዎች የንባብ መርሐ ግብር ተካሔደ

የተማሪዎች የንባብ መርሐ ግብር ተካሔደ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ጥቅምት 1/2016 ዓ.ም ከለባዊ ዓለም ዓቀፍ ትምህርት ቤት ለመጡ የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች ያዘጋጀውን የግማሽ ቀን የንባብ መርሐ ግብር አካሒዷል፡፡

መርሐ ግብሩ የተካሔደው የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት የሕፃናት ቤተ-መጻሕፍት ክፍል ውስጥ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ከኢትዮጵያ ሪድስ ድርጅት በተወከሉ ወጣት እሌኒ ነጋሽ እና በተቋሙ የተጋበዘው በኮሜድያንነቱ እንዲሁም የልጆች መጽሐፍትን በጻፈው አርቲስት አስረስ በቀለ ለተማሪዎቹ ተረት ተነግሮ ከተነበቡት የተረት መጽሐፍት ውስጥ ጥያቄ አቅርቦ እንዲሰሩ በማድረግ በቀኑ ጥሩ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት የተዘጋጁ የተረት መጽሐፍት በተቋሙ የአብያተ መጻሕፍት አገልግሎት መሪ ሥራ አስፈፃሚ በሆኑት በአቶ ያሬድ ተፈራ እጅ ተበርክቶላቸው መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

Share this Post