ለተቋሙ አመራሮች የመሪነት ስልጠና ተሰጠ 

 የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዲስ የተገበረውን ተቋማዊ መዋቅር ተከትሎ ለዴስክ ኃላፊ፣ ቡድን መሪ፣ ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራ አስፈጻሚነት ደረጃ ለመጡ አዲስና ነባር አመራሮች ለስራቸው ስኬታማ መሆን የሚያዘጋጅ ስልጠና ሰኔ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ተሰጥቷል።
ይህ ኃላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት እንደ መነሳሻና ማነቃቂያ የሆነው ስልጠና የተሰጠው በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ መምህር እንዲሁም በግል አማካሪ በሆኑት ዶ/ር አሸናፊ ኃይሌ ሲሆን የአመራሩን የመሪነት ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችሉ ስልጠናዎችም በቀጣይነት እንደሚሰጡ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የብቃት እና ሰው ሀብት አስተዳደር ተወካይ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ደሜ ደሳለኝ ሲያሳውቁ የተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብነት አበራ ይህ ስልጠና በአዲሱ የ2016 ዓ.ም በጀት አመት መግቢያ ላይ መሰጠቱ ለስራው ጥሩ ስንቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

Share this Post