የተቋሙ ስራ አመራር ከባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ጋር በእቅድ ክንውን ላይ ተወያየ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የተቋሙን አዲሱን የስራ መዋቅር ድልድል አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ተከትሎ አዲሱ የስራ አመራር ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፎ ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ወርቅነሽ ብሩ እና በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ አወያይነት ከሰኔ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የምክክር መድረክ አድርጓል።
በዚህ የምክክር መድረክ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የ 2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት የስራ ክንውን የተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ በሆኑት በአቶ አብነት አበራ፤ የሚኒስቴር መስሪያቤቱን የባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ የስራ ክንውኖችን የብዝሀ ባህል አካታችነትና ማህበራዊ ትስስር ልማት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሞሲሳ ለሚ አቅርበዋል።
ከቀረበው የ 2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት የእቅድ ክንውን የስራ አፈጻጸም በመነሳት እንደ ሚኒስቴር መስሪያቤት በተለይም እንደ ባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ እና እንደ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ተጠናክረው ሊሰሩ የሚገቡ፣ በቅንጅት የሚሰሩ፣ ለስራ ውጤታማነት ተግዳሮት በመሆን አሉታዊ ተጽእኖ የሚፈጥሩ ጉዳዮች ስለሚፈቱባቸው ሁኔታ እና አጠቃላይ እንደ ሚኒስቴር መስሪያቤት በቀጣዩ የ 2016 ዓ.ም በጀት አመት የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ ለማምጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን በማሳለፍ እንደ ሀገር የሚኖረው አስተዋፅዖ ላይ ጠቃሚ ነጥቦች ተቀምጠዋል።