የአብሮነት ቀን ተከበረ


የአብሮነት ቀን ተከበረ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠውን የአብሮነት ቀን ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም አክብሯል።
ተቋሙ ከባህል ስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በስፖርት አካዳሚ የአዲስ አመት መልካም ምኞት መግለጫ መለዋወጥን፣ ይቅርታ መጠያየቅን፣ ከማረፊያ የአረጋውያን እንክብካቤና ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በመጡ ታዳጊዎች የአበባዮሽ ዜማ፣ የእግር ጉዞና በባህላዊ ቡና አፈላል ስርአት የታጀበውን የአብሮነት ቀንን ሲያከብር የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ወርቅነሽ ብሩ ከቀደመው ጊዜ ጀምሮ እስካሁን የዘለቀውን አብሮነታችንን ጠብቀን ለትውልድ ልናሻግር እንደሚገባ አጽኖት የሚሰጥ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ሚኒስቴር ድኤታዎች ክብርት ነፊዛ አልማህዲ፣ ክቡር አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የሚኒስቴር መስሪያቤቱ እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት ዳይሬክተሮችና ስራ አስፈጻሚዎች ተገኝተዋል።

Share this Post