ተጨማሪ ስራን በመፍጠር ገቢን እና የኢኮኖሚ አቅምን ማሻሻል እንደሚገባ ተገለጸ

የተቋሙ የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ በቀን 29/9/2015 ዓ.ም በተቋሙ የሴቶችና የወጣቶች ፎረም ማጠናከሪያ ካዘጋጀው የውይይት መድረክ በተጨማሪ በተቋሙ የሚገኙ ሰራተኞችን ገቢና የኢኮኖሚ አቅም ለማጠናከር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር አካሒዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ የተገኙት ከአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ይልማ እና ከአዲስ እይታ የንግድና ኢንቨስትመንት የማማከር አገልግት ም/ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ኤልያስ በላይ እንደተናገሩት በተቋሙ ለሚገኙ ሰራተኞች ተጨማሪ ስራን በመፍጠር ገቢን እና የኢኮኖሚ አቅምን ለማሻሻል በአነስተኛ፣በመካከለኛና በከፍተኛ የገንዘብ መጠን ሊሰሩ የሚችሉ ተጨማሪ ስራዎችን የማስተዋወቅ እና እነዚህን ስራዎች ለመስራት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ከገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር እንዴት አባል መሆንና የቁጠባና የብድር አገልግሎቶችን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል፡፡

Share this Post