ታሪካዊ  አውደ ርእይ ተዘጋጀ

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት 82ተኛውን የአርበኞች የድል በዓል ምክንያት በማድረግ በተቋሙ ህንፃ ውስጥ በተዘጋጀ ስፍራ ሁነቱን የሚያሳዩ ፎቶ ግራፎችና መዛግብትን ለእይታ አደራጅቶ ከረቡዕ ሚያዝያ 25 /2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተመልካች ክፍት አድርጓል።

አውደ ርእዩ በ1928 ዓ.ም ወራሪው የጣሊያን ጦር ያደረሰውን ጉዳት፣የመላው ኢትዮጵያዊያን ተጋድሎን፣የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እና የስመጥር አርበኞችና የጦር መሪዎች የጦር ሜዳ ፎቶ እንዲሁም ግርማዊ ንጉሠ ነገስት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የጣሊያን ወረራን አስመልክቶ ለዓለም መንግስታት ማህበር  ያቀረቡት ንግግር ረቂቅ እና ሌሎች ተያያዥ መዛግብትም የተካተቱበት ሲሆን እስከ ሐሙስ ሚያዝያ 26 /2015 ዓ.ም ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ያለ ምንም ክፍያ ሊጎበኘው የሚችለው መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

Share this Post