ጥበብ ራስዋን ችላ ልትደመጥና ልትሰማ እንዲሁም በነጻነት መልዕክት በማስተላለፍ ለሀገር የራስዋን አሻራ ልታሳርፍ እንደሚገባ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት እና የግርማ ይራፍራሸዋ የሙዚቃ እና የጥበብ ማዕከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ 

የመግባቢያ ስምምነቱን ሰነድ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እና የግርማ ይራፍራሸዋ የሙዚቃ እና የጥበብ ማዕከል ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ ሰኔ 22/2015 ዓ.ም በይፋ ተፈራርመዋል፡፡

በዝግጅቱም ላይ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ፣ ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ የጥበብ ሰዎች፣በኢትዮጵያ የኦስትሪያ፣የጣሊያን እንዲሁም የቡልጋሪያ አምባሳደሮች እና በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች እና የሚድያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ ዋነኛ ዓላማም ሰዎች ተገናኝተው ሃሳብ፣መረጃ ክህሎትና ሀብት የሚለዋወጡበት ቦታ ማዘጋጀት እንደሆነም የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ተናግረዋል፡፡

አክለውም ዛሬ ለፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ አገልግሎቱ አዳራሽ ሲሰጠው ጥበብ ራስዋን ችላ ልትደመጥና ልትሰማም እንደሚገባና በነጻነት ለሀገርና ለትውልዱ የሚጠቅም ስራን በመስራት አሻራን መጣል እንደሚቻልም ጭምር ሚናው የጎላ እንደሆነም ተናግረው

በዚሁም መሰረት አገልግሎቱ የሙዚቃ ትርኢቶችን ለማቅረብ፣የሙዚቃ መሳሪያ ስልጠናዎችን ለመስጠት፣ኤግዚቢሽኖች እና ባህላዊ ዝግጅቶችን አዘጋጅቶ ለማቅረብ የሚያገለግል አዳራሽ ለማዕከሉ እንደሚሰጥም ተጠቁሟል፡፡

ፒያኒስቱም በህልም ደረጃ ያሰቡትን ሐሳብ ለተሳታፊው ሲያቀርቡ አንደኛው ሀገራቸውን በሙዚቃው ዓለም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ማድረግ፣ሁለተኛው  በስራ አጋጣሚ የተዋወቋቸው ዓለም አቀፍ ሙያተኞች ስለሏው ተተኪ ትውልዶች ላይ መስራት በተለይ ልጆች ላይ የስልጠና ማዕከል በመክፈት እንደሚያሰለጥኑ እና ኢትዮጵያዊያኖች በማንኛውም የዕውቀት ዘርፍ ስራቸውን የሚያስተዋውቁበትን መድረክ መፍጠር (ማመቻቸት ) እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ይህንን በጎ ጅማሮም ያደረገላቸውን ተቋምና የአገልግሎቱን ዋና ዳይሬክተር በተሳታፊው ፊት ሲያመሰግኑ ስራቸውን ከዚህ በፊት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሚያቀርቡበት ወቅት የረዷቸውንና ለዚህ ስኬት መድረስ የሚተባበሯቸውን ኢምባሲዎችንና አምባሳደሮችን እንዲሁም በስኬታቸው ውስጥ ድርሻ ያላቸውን ግለሰቦች አመስግነዋል፡፡

በርካታ ተሳታፊዎችም ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ በስራቸው ታታሪና ትጉ እንደሆኑም መስክረው በተጨማሪም የተቋሙን ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክም ለጥበብ ክብር በመስጠጥ በሙያው አምነው ቦታ በመስጠት ጥበብ ለሀገር እድገት አሻራዋ የጎላ መኖኑን በማመንና እንድትስፋፋ ላበረከቱት በጎ ስራ ተመስግነዋል፡፡

በዕለቱም የፒያኒስቱን ስራዎች ሃርድና ሶፍት ኮቪ በአገልግሎቱ ተጠብቀው ለትውልድ እንዲሸጋገሩ ከፒያኒስቱ ለአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር በስጦታ ሲበረከቱ የተበረከቱት  መረጃዎቹንም በተመለከተ በፒያኒስት ግርማ ገለጻ ተደርጎባቸዋል፡፡ 

በመጨረሻም ከአገልግሎቱ በስጦታ የተዘጋጀው አዳራሽ ለፒያኒስቱ ተበርክቶ አገልግሉቱ ለእይታ ያቀረባቸው የጽሑፍ ቅርሶች በእለቱ በዝግጅቱ በተሳተፉ ተሳታፊዎች ተጎብንቶ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

ሰኔ 22/2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት እና የግርማ ይራፍራሸዋ የሙዚቃ እና የጥበብ ማዕከል መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድም  የመግባቢያ ሰነዱ ዓላማ፣የትብብር መስኮች፣ለትብብሩ የሚያስፈልጉ ገንዘብና ሀብት የሚሸፈንበት አግባብ፣ልዩ ልዩ ጉዳዩች እና የመግባቢያ ስምምነቱ የሚተገበርበት አግባብ በማለት አምስት አበይት ተግባራትንም ዘርዘር ያሉ ሃሳቦችን ያስቀመጡ እንደሆኑ የተዘጋጀውን ሰነድ በመመልከት ለማወቅ ተሞክሯል፡፡

Share this Post