በወላይታ ሶዶ ከተማ ለወላይታ ሶዶ ማረሚያ ቤት የመጽሐፍ ስጦታ መርሐግብር ተከናወነ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከደቡብ ህዝቦች ብሔር ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ.ም  በወላይታ ሶዶ ከተማ ማረሚያ  ቤት የንባብ ልምድ ልውውጥ እና የመጽሐፍት ስጦታ መርሐግብር አከናውኗል።  ተቋሙ ለማረሚያ ቤቱ ያበረከተው 500 መጽሐፍት  በገንዘብ ሲተመን 96,981 ብር ሲሆን መርሐግብሩን በእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ቤት ዋና አዛዥ  ኮማንደር ደጀኔ ዳርጮ ከየኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የስልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ መኮንን ከፋለ ተረክበዋል ።
የዚህን መርሐ መርሐግብር አላማ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎትን በመወከል የተቋሙ የአብያተ መጽሐፍት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ተፈራ ያብራሩ ሲሆንደራሲ ዘነበ ወላ፣ ደራሲና ሀያሲ ገዛኸኝ ሀብቴ እና ደራሲ ሊዲያ ተስፋዬ ከማረሚያ ቤት ጋር የተሳሰሩ የንባብ ልምድና ተሞክሮዎችን አጋርተዋል። በዕለቱ ለተከናወነው የአሳታፊ ጥያቄዎች ተሳታፊ ለሆኑ ታራሚዎች የመጽሐፍ ስጦታ የተሰጠ ሲሆን የደቡብ ህዝቦች ብሔር ብሔረሰቦች ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ጋጋዶ የማጠቃለያ ንግግር አድርገዋል።

Share this Post