- Date: Jul 24 2026
- Attachment: ማውረድ
-
Content
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና መጻሕፍት አገልግሎት በቤተመጻሕፍት ዘርፍ የሚሰጣቸው ስልጠናዎች በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ይመደባሉ፡፡
1.መደበኛ ስልጠና
በተቋሙ የስልጠና ማዕከል ለህዝብ ቤተመጻሕፍት ለትምህርት ተቋማት፣ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች፤ ከሃይማኖት እና ከግል ተቋማት ለሚመጡ የቤተመጻሕፍት ባለሙያዎች የሚሰጥ የቤተመጻሕፍት ሙያ ሳይንስ ስልጠና ነው፡፡
2.በተቋማት በሚቀርብ ጥያቄ የሚሰጥ ሥልጠና
ማንኛውም የመንግሰት ወይም መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም በቤተ መጻሕፍት ዙሪያ ለሰራተኞቹ ስልጠና እንዲሰጥለት በሚጠይቅበት ወቅት 2 ወይንም ከዚያ በላይ እንደ አስፈላጊነቱ አሰልጣኞች ተመድበው ጠያቂው ተቋም በራሱ የስልጠና ቦታ ወይንም በሚያመቻቸው ሌላ ቦታ የሚሰጥ ስልጠና ነው፡፡
የመደበኛ ስልጠና የዓመቱ መርሐ ግብር
የስልጠና ሰዓት
ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት 2፡30-6፡30
7፡30- 11፡30
ለመደበኛ ስልጠና ከተቋማት የሚጠበቁ መስፈርቶች፤
· በደብዳቤ ጥያቄ ማቅረብ፤
· ለስልጠና ብቁና ከስራው ጋር ቀጥታ ተያያዥ ስራ የሚሰሩ ሰልጣኞችን መላክ፤
· በፕሮግራሙ መሰረት የሚፈልጉትን ስልጠና፣ የአገልግሎት ክፍያን በሚመለከት
በሚቀርብ ጥያቄ አሰልጣኞችን በመላክ ለሚሰጠው ስልጠና ክፍያዉ አዲስ በጸደቀው በደንቡ ቁጥር መሠረት የሚፈጸም ይሆናል::
ተ.ቁ የስልጠናው ዓይነት ስልጠናውየሚሰጥበት ጊዜ
1. በሠነድ ስራ አመራር እና መዛግብትአስተዳደር ባለሙያዎች ነሐሴ 18-29/2018 ዓ.ም
2. በሠነድ ስራ አመራር እና መዛግብት አስተዳደር ለፀኃፊዎች መስከረም 25-29/2019 ዓ.ም
3. ሰነድ ስራ አመራር እና መዛግብት አስተዳደር ባለሙያዎች ጥቅምት 16-27/2019ዓ.ም
4. ሰነድ ስራ አመራር እና መዛግብት አስተዳደር ለመካከለኛ አመራሮች ሕዳር 14-18/2019ዓ.ም
5. የአሰልጣኞች ስልጠና /TOT/ TOT ታህሳስ 12-23/2019 ዓ.ም
6. ሰነድ ስራ አመራር እና መዛግብት አስተዳደር ባለሙያዎች ጥር 17-28 /2019 ዓ.ም
7. ሰነድ ስራ አመራር እና መዛግብት አስተዳደር ለባለሙያዎች የካቲት 08-19/2019 ዓ.ም
8. ሰነድ ስራ አመራር እና መዛግብት አስተዳደር ባለሙያዎች መጋቢት 13-24 /2019 ዓ.ም
9. ሰነድ ስራ አመራር እና መዛግብት አስተዳደር ባለሙያዎች ሚያዝያ 04-15/2019 ዓ.ም
10. በሠነድ ስራ አመራር እናመዛግብት አስተዳደር ለፀኃፊዎች ግንቦት 09- 20/2019 ዓ.ም
11 ሰነድ ስራ አመራር እና መዛግብት አስተዳደር ባለሙያዎች ሰኔ 14-25/2018 ዓ.ም