በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐግብር ተካሄደ፡፡

በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐግብር ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከባህልና ስፖርት ሚኒስትርና ከተጠሪ ተቋማቱ፣ ከስፖርት፣ ከባህል፣ ከኪነ ጥበብ ማህበራት እና ከልደታ ክ/ከ ወረዳ 08 አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ከስድስት ሺህ ችግኝ በላይ መካኒሳ በሚገኘው ጌዶ ዋሻ ተክሏል፡፡

ይህም ነሀሴ 17 2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ የሚገኘው በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐግብር አካል ነው፡፡

 መርሀ ግብሩም “የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖ አምላክ መዝገቡ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ፣ ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡ 

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ጃንካ ባስተላፉት መልዕክት በ2016 በጀት ዓመት 7.5 ቢልዮን ችግኝ ለመትከል በተካሄደው ንቅናቄ ሀገራችን ከአረንጓዴ አሻራ ልማት የምታገኘውን ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥቅም እውን ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

Share this Post