የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር ተፈራረመ።

መስከረም 2019 ዓ.ም አዲስ አበባ
ተቋሙ የተፈራረመው የመግባቢያ ሠነድ ዋነኛ ዓላማም አብያተ መጻሕፍትን በማጠናከር፣የንባብ ባህልን በማዳበር እና የማኀበረሰቡን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲቻል የተቀናጀ የትብብር ሥርዓት ለመዘርጋት የተደረገ ስምምነት እንደሆነም ተመላክቷል።
መግባቢያ ሠነዱ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ጠንካራ ስልታዊና ዘላቂ የትብብር ማዕቀፍ በመዘርጋት በሲዳማ  ክልል፣በሀዋሳ ከተማና በአካባቢው የሚገኙ የሕዝብ ትምህርት ቤት፣ በዩኒቨርሲቲ እና በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ አብያተ መጻሕፍትን ደረጃ ማሻሻል፣የህብረተሰቡን የንባብ ባህልና የመረጃ አጠቃቀም ማሳደግ፣ሙያዊና ተቋማዊ አቅምን መገንባት እንዲሁም በጋራ ጥናትና ምርምርን ማካሄድ እንደሆነም ተጠቁሟል።

Share this Post