ተቋሙ በቅንጅት የጽዳት ዘመቻ መርሐ ግብር አካሄደ።

የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት  ከፌደራል ፖሊስ እና ከከተማ ልማት ሚኒስቴር፣ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፣ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዲሁም ከቪዥን ክሊኒክ ጋር በመሆን "ክብረ በዓላቶቻችን የወንድማማችነትና የአንድነታችን መገለጫ ናቸው!"በሚል መሪ ቃል የጽዳት ዘመቻ መርሐ ግብር አካሂዷል።
በጽዳት ዘመቻው ከተቋማቱ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች በተጨማሪ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ጽዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች የጽዳት ንቅናቄውን በማስተባበር የመርሐ ግብሩ አካል ሆነዋል።

Share this Post