የወር ወንበር በወመዘክር ተዘረጋ
የወር ወንበር በወመዘክር ተዘረጋ
በጥንታዊው ሥርዓተ ትምህርታችን: ወንበር: ረግቶ የማሰብ፣ እውቀትን የመሰብሰብ፣ ስብስቡን የማካፈል ኺደት የሚገለጽበት የትምህርት ፅንሰ ሐሳብ ነው። ወንበር ተዘረጋ፣ ተተከለ ከተባለ ትምህርት በወጉ ተጀመረ ማለት ነው።
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር በወር ለአንድ ቀን: ከአንድ ቀንም የአንድ ሠዓት ተኩል ቆይታ ያለውን መርሐግብር የመጀመሪያውን ወንበር
ቅዳሜ ሰኔ 15፣ 2016 ቀን “ከርሠ ግጥም” በሚል አርዕስት የሦስት ግጥሞች ምልከታ ላይ በማድረግ ግሩም፣ ጥልቅ፣ ጥበባዊ ሃሳቦችን አንስቶ አወያይቷል፡፡
በዚህ በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻሕፍት (ወመዘክር) ግቢ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ አዳራሽ የተዘጋጀውና በግጥሞቹ ላይ ጥበባዊ፣ ቴክኒካዊ፣ ምናባዊ ትንተናን ያቀረቡት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ይኩኖ አምላክ መዝገቡ መርሐግብሩ ቀጣይነት ያለው ወርሐዊ ክንዋኔ እንደሆነ ተናግረዋል።