የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት የመጽሐፍ ስጦታን አበረከተ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት  የመጽሐፍ ስጦታን አበረከተ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ለሚገኙ 18 2ተኛ ደረጃና መለስተኛ ት/ቤቶች እንዲሁም ለ1 የህዝብ ቤተ መጻሕፍት በድምሩ 4328 መጻሕፍት በስጦታ አበርክቷል።

ተቋሙ 1 ሚሊየን 214 ሺህ 126.5 ብር ወጪ የተደረገባቸውን መጻሕፍት ያበረከተው በጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ከግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባዘጋጀው በንባብ የልምድ ልውውጥና የንባብ ክበባት ምስረታ እንዲሁም በመዛግብትና ሰነድ፣ በመረጃ ሀብቶች አሰባሰብና አደረጃጀት አውደ ውይይትና ስልጠና መርሐግብር ነው።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ እና የመርሐግብሩ ዝግጅት መነሻ የሆኑት አምባሳደር ዶ/ር ኮአንግ ቱትላም ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ኩአንግ ኡኳይ እና ለክልሉ የቱሪዝም ዘርፍ ም/ኃላፊ አቶ ፔል ፒተር መጻሕፍቱን ባስረከቡበት ወቅት መጻሕፍቱ ለታለመላቸው ዓላማ ይውሉ ዘንድ አበክረው ተናግረዋል።

Share this Post