የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከሰባት መቶ ሚልየን ብር በላይ ፈጅቶ ያስገነባውን ሕንጻ አስመረቋል።
የካቲት 16/2016 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከሰባት መቶ ሚልየን ብር በላይ ፈጅቶ ያስገነባውን ሕንጻ አስመረቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የኤ.ፌ.ድ.ሪ ባህልና ስፓርት ሚኒስትር ሚኒስቴር የተከበሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ የተከበሩ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ አምባሳደሮች፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ ምሁራኖች፣ጸሐፊያን፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶቾ ተገኝተውበታል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ሲደረግ በባህልና ስፓርት ሚኒስትር ሚኒስቴር በክቡር አቶ ቀጄላ መርዳሳ የመክፈቻ ንግግርሲደረግ በንግግራቸው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የነጻነት ጉዞ ተምሳሌትና ጽናት ከመሆኗ ባለፈ መልክሃ ምድሯና በተፈጥሮ ሀብቷ ከሚነገርላት በላይ በባህልና በቅርሶቿ ያልተነገረላት ምድረ ቀደምትና የአሥራ ሦሥት ወር ጸጋ ባለቤት እንደሆነችና ያሏትን መንፈሳዊና ቁሳዊ ባህልና ሐይማኖታዊ ቱርፋቶችን ማሳያ የሆኑ ታሪክን ሰብስበው እና መዝግበው ጥበብና እውቀትን አስፍረው የያዙ የጽሑፍና የቃል ያልተጻፉ በቃል የተላለፉ የጽሑፍና የቃል፣ታሪካዊ ቅርሶች ሀገሪቷ ያለፈቻቸውን ጠመዝማዛ መንገዶችና የተሻለውን ነገ ለማሳየት ከማገዛቸውም በተጨማሪ በአንድ መልኩ መረጃ ማስረጃ በመሆን የጥያቄዎቻችንን ምላሽ ሲሰጥ በሌላ በኩል ሀገር በቀል እውቀት ጥበብና ስልጣኔን ከትውልድ ወደትውልድ መተላለፍ እንዲችሉ ማገዝ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ከክቡር ሚኒስተሩ ንግግር በመቀጠል ከአገልግሎቱ የተዘጋጀ ቀድሞ ተቋሙን ለመሩ እና ሕንጻውን በተመለከተ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የእውቅና ስጦታ ተበርክቶ
ከሰባት መቶ ሚልየን ብር በላይ የፈጀው ባለ 13 ወለል የመዛግብት ሕንጻ በክቡር ሚኒስቴር የተከበሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ተመርቆ ሲከፈት ተቋሙ በግልና በመቀናጀት ያዘጋጃቸው የስዕል፣ የፎቶግራፍ፣ ጥንታዊ የጽሑፍ ቅርሶች (የእስልምናና የክርስትና እምነት) መዛግብቶች ፣የድምጽና የምስል ቅጅዎች ኤግዚቢሽን ተጎብኝቶ የተዘጋጀው ኤግዚቢሽን ለእይታ ክፍት ተደርጓል።