የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በአብያተ መጻሕፍት እንደዚሁም በሰነድና መዛግብት አስተዳደር ዙሪያ በጥር 21 2016ዓ.ም በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ የፓናል ውይይት አዘጋጀ፡፡
በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የአብያተ መጻሕፍት መረጃ ሀብቶች ማሰባሰብ ስራ ክፍል ቡድን መሪ የሆኑት አቶ እስራኤል በዙ “የህዝብ ቤተ መጻሕፍት ለማህበረሰብ እድገት ያለው አስተዋጽኦ’’ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳ/ር አቶ ታደለ ሙላት ተቋሙ እየሰራበት የሚገኘውን የተቀናጀ የቤተ መጻሕፍት፣ የመዛግብትና የሰነድ ስራ አመራር ሥርዓት (ILARMS) ተሞክሮ አቅርበዋል፡፡ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቤተ መጻሕፍት ዳ/ር በሆኑት ዶ/ር ሲሳይ ሳሙኤል የዩኒቨርሲቲው የዲጂታል ቤተ መጻሕፍት ተሞክሮ ቀረቧል፡፡
በተመሳሳይ ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ተመስገን ካሴ “ቴክኖሎጂ እና የንባብ ባህል” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል፡፡
በሰነድና መዛግብት አስተዳደር ዙርያ ደግሞ በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት በቤተ መጻሕፍት፣ መዛግብትና ሰነድ አያያዝ ስልጠናና የማማከር አገልግሎት የስራ ክፍል ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሀብቴ ቶሎሳ “የሰነድና መዛግብት ጽንሰሃሳብና ፋይዳ” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡በቀረቡት የውይይት መነሻ ጽሑፎች ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡