በመረጃ አደረጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ!
በመረጃ አደረጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ!
የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሥር ሀገር-በቀል እውቀት ልማት ምርምር ተቋም፤ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በመረጃ አደረጃጀትና አጠቃቀም ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻህፍት ኤጀንሲ ባለሙያዎች በመጻሕፍትና መረጃ አያያዝ ዙሪያ የነበረውን ልምድ በዩኒቨርሲቲው ተዘዋውረው በመመልከት በመረጃ አያያዝ፤ ቤተ-መጻህፍት አደረጃጀት እንዲሁም የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብት እና ቤተ-መጻህፍት አጠቃቀምን አስመልክቶ ለዩኒቨርሲቲው የቤተ-መጻህፍት፤ ቤተ-መዛግብት ባለሙያዎች፤ የሙዚየም ሠራተኞች እና የታሪክ ት/ት ክፍል ተማሪዎች በተሳተፉበት የመረጃ አያያዝና የመጻህፍት አጠቃቀም ልምድን ለማካፈል እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚቀርብ የግንዛቤ ማስጨበጫ የጋራ መድረክ መሆኑን ከክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
በጋራ የውይይት መድረኩ ላይ ዶ/ር አብዮት አስረስ ( ተባባሪ ፕሮፌሰር ) የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ተገኝተዋል ።