የንባብ ክበባት ምስረታና ማጠናከሪያ እና በንባብ ባህል ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ባህል ቱሪዝም ቢሮ እና ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባካሄደው የንባብ ሳምንት መርሃግብር ላይ ሰኔ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. በባህርዳር ከተማ የሚገኙ 10 ት/ቤቶችን ያሳተፈ የንባብ ክበባት ምስረታና ማጠናከሪያ እና የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን ፤ በመድረኩ ጋዜጠኛ የትናየት አበራ፣ ጋዜጠኛ በፍቃዱ አባይ፣ መምህርት ደስታ ወ/መስቀል እና መምህር መሰረት አበጀ የተማሪዎችን የንባብ ባህል የሚያጎለብቱ አነቃቂ ንግግሮችን አድርገዋል። በተመሳሳይ "የመረጃ ተደራሽነት ለዘመነ አመራርና አስተዳደር" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት በዕለቱ የተካሄደ ሲሆን የተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዎች ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ጥናታዊ ጽሑፎችን አቅርበው ውይይት ተካሄዶባቸዋል።

Share this Post