ህጋዊ የሆኑ የሰነድ አወጋገድ ሒደቶችን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ።

ህጋዊ የሆኑ የሰነድ አወጋገድ ሒደቶችን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ።

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ከእንቅስቃሴ ውጪ የሆኑ ሰነዶችን ህጋዊ በሆነ መንገድ ለማስወገድ እንዲረዳ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ከተለያዩ የፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር አውደ ውይይት አካሒዷል።

በአውደ ውይይቱ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ የአውደ ውይይቱን ዓላማ ሲገልጹ ስለሰነዶች እና መዛግብት አመራረጥ፣ግምገማና አወጋገድ ህጋዊነት ግንዛቤ ማስጨበጥ፤ህጉን በተጠናከረ መልኩ እንዴት መፈጸም እንደሚገባ፤የመረጃ ሃብቶችን በአግባብ መያዝ እንደሚያስፈልግ እና መዛግብትን ከሚይዙ አካላት ጋር በቅርበት በመነጋገር የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ቀጣይነት ያለው ውይይት በማድረግ የሀገሪቱን ሰነዶች ለመታደግ የሚያስችል ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩም በዶ/ር አልማው ክፍሌ ስለመዛግብትና ሰነዶች አወጋገድ የሀገር ውስጥና የዓለም አቀፍ የህግ ማእቀፎችና ተሞክሮዎች ዳሰሳ ጥናት እንዲሁም በተቋሙ የሰነድ እና መዛግብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ በአቶ ሰለሞን ጠና የሰነድ ስራ አመራርና ህጋዊ የሰነድ ውገዳ ሂደት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የተዘጋጁ በርካታ ሃሳቦችን የያዙ ጽሑፎች ለውይይት ቀርበው ከተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች እና ሃሳብ አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው አውደ ውይይቱ ሲጠናቀቅ በስተመጨረሻም የተቋሙን ቤተ- መዛግብት በመጎብኘት ዝግጅቱ ተጠናቋል።

Share this Post