ታላቅ የምስራች

ታላቅ የምስራች

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ያስገነባውን ባለ 13 ወለል የቤተመዛግብት ሕንጻ የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከ2፡30 ጀምሮ ታላላቅ የመንግሥት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮች፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ግለሰቦች በተገኙበት በደማቅ ሥነ-ስርዓት ያስመርቃል ፤ የ80ኛ ዓመት ክብረ በዓሉንም ያከብራል፡፡

እነዚህን ሁነቶች ምክንያት በማድረግ በተቋሙ ተመዝግበውና ተጠብቀው የሚገኙ እና በሌሎች ተባባሪ ተቋማት እጅ የሚገኙ የጽሑፍ ቅርሶች አውደ ርዕይና ሌሎች ተቋሙን ሊያስተዋውቁ የሚችሉ ክንውኖች ለእይታ ይቀርባሉ፡፡

በመሆኑም ዝግጅቶቹ  ከእሁድ የካቲት 17/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለእይታ ክፍት ስለሚሆኑ መጥታችሁ እንድትጎበኙ ተጋብዛችኃል፡፡

Share this Post