የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት በአዘጋጅነት የተካፈለበት 4ኛው ሆሄ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት ተካሄደ

ማክሰኞ ጷግሜ 1 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) 4ኛው ሆሄ የሥነ-ጽሑፍ ሽልማት "መጻሕፍት ለዕውቀት ዳበራ! ለጥበብ ጎታ!" በሚል መሪ ቃል በስድስት የመጽሐፍ ዘርፎች፤ በአዲስ አበባ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት የቲያትርና ባህል አዳራሽ ጷግሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ማምሻውን ተካሂዷል።

ለ2 ዓመታት በዓለማቀፋዊና አገራዊ ምክንያቶች ሳይካሄድ የቆየው ሽልማቱ፤ አራተኛ መርሐግብሩን በርካታ የጥበብ ቤተሰቦች በተገኙበት አካሂዷል። በ2011 የታተሙ መጽሐፍትን በእጩነት ይዞ ያወዳደረው ሽልማቱ፤ ከተወዳዳሪ መጽሐፍት ባለፈ በ3 ዘርፎች ባለውለታዎችን እንዲሁም የእድሜ ዘመን ተሸላሚን እውቅና ሰጥቷል።

በዚህም መሰረት፦

*በባለውለታዎች ዘርፍ

(የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛና ልማት ማዕከል)(ECDD)፤ ለአካል ጉዳተኞች አካታች የሆነ የንባብ አበርክቶ በማድረግ

(መጻሕፍት ለሁሉም) "Book for All" ማህበራዊ መገናኛን ለንባብ በመጠቀም

(ፖፑሌሽን ሚዲያ ሴንተር) በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ባበረከቱት አስተዋፅዖ

* በየዓመቱ ምርጥ የልጆች መጽሐፍ ዘርፍ

(ልብስ ሰፊውና አይጦቹ) ደራሲ በሀይሉ ገብረ እግዚአብሔር

*በየዓመቱ ምርጥ አጭር ልቦለድ ዘርፍ

(ማታ ማታ እና ሌሎች ታሪኮች) ደራሲ ህይወት እምሻው

*በየዓመቱ ምርጥ የግጥም መፅሀፍ ዘርፍ

(ኮብላይ ዘመን) ደራሲ ተሾመ ብርሀኑ

*በየዓመቱ ምርጥ የጥናትና ምርምር መጽሀፍ ዘርፍ

(ኢትዮጵያዊው ሱራፊ) ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

*በየዓመቱ ምርጥ የግለ-ታሪክ መጽሀፍ ዘርፍ

(ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር) አንዳርጋቸው ጽጌ

*በየዓመቱ ምርጥ ረዥም ልብወለድ ዘርፍ፤

(ታለ በእውነት ሥም) ዓለማየሁ ገላጋይ አሸናፊ ሆነዋል።

በተጨማሪም በመድረኩ፤ የናቅፋው ደብዳቤ፣ እናት ሀገር፣ የፍቅር ቃንዛ፣ ነበር1፣ ነበር2፣ የበቀል ጥላ፣ የቀድሞ ጦር እንዲሁም በሌሎች ዘመን ተሻጋሪ መጽሐፎቻቸው የሚታወቁት አንጋፋው ደራሲ ገስጥ ተጫኔ በህይወት ዘመን ተሸላሚ ሆነዋል።

 

 

Share this Post