• Date: Jan 21 2022
  • Attachment: Download
  • Content

    የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት እንደቀድሞው ለአንባቢያን ተጠቃሚዎቻችን የመጻሕፍት ውሰት መጀመሩን እየጠቆምን

    ተጠቃሚዎች የውሰት አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፦ 

    1. ዋስ ማቅረብ የሚችል

    2. የግለሰብ ዋስ ከሆነ ግለሰቡ ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ለተጠቃሚው የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ወይም ተጠቃሚው ከሚሰራበት መስሪያ ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።

    • የአገልግሎት መደቦች

    1. የአዋቂዎች አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 70 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 3 መጽሐፍት ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት

    2. የተመራማሪዎች አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 250 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 5 መጽሐፍ ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት፣ መጽሕፍትን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት

    3. የተማሪ አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 70 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 2 መጽሐፍት ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት

    4. የተቋም አባል

    የአገልግሎት ክፍያ 1500 ብር ፣ መዋስ የሚችሉት 20 መጽሕፍት ፣ መጽሕፍትን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት

    5. የድርጅቱ ሰራተኞች

    የአገልግሎት ክፍያ ነፃ፣ መዋስ የሚችሉት 2 መጽሐፍት ፣ መጽሐፍቱን በውሰት ማቆየት የሚቻለው ለ 14 ቀናት መጽሐፍቱን መመለስ ካለባቸው ቀናት ሲያሳልፉ በየቀኑ 1 ብር ቅጣት መሆኑን ከወዲሁ መጠቆም እንወዳለን፡፡