3ተኛው ዓመታዊ የህፃናት ንባብ ጉባኤ ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት እና ኢትዮጵያ ሪድስ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን ከመስከረም 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሳፋየር አዲስ ሆቴል እያከናወነ የነበረው 3ተኛውን ዓመታዊ የህፃናት ንባብ ጉባኤ ተጠናቀቀ፡፡ ጉባኤው የተለያዩ መርሃግብሮች የተከናወኑበት ሲሆን ከነዚህም መካከል ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተካሂደበታል፣ የአውደ ርዕይ ዝግጅትም ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

በማጠናቀቂያው መርሐ ግብር የውይይት መነሻ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ከመደረጉ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ሪድስ ታትመው በነፃ ለመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚሰራጩ 5 የልጆች መጻሕፍት የተመረቁ ሲሆን የመጻሕፍቱ ደራሲያን ሜሪ ጃፋር፣ ዳንኤል ወርቁ፣ አስረስ በቀለ፣ ሳምራዊት አርአያ እና ሰላማዊት ሙሉጌታ ናቸው። መጻሕፍቱም ትንሿ አበባ፣ ትንሿ ዶክተር፣ ሚጢ ሚጢጢ፣ ቡጉሊ ፍየል እና ጎበዙ ችክስ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም በንባብ በተለይም በህፃናት ንባብ ላይ አበርክቶ ላላቸው ግለሰቦችና ሙያተኞች በኢትዮጵያን ሪድስ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

Share this Post