ከአዲስ አበባ ከተማ ለተመረጡ 10 ትምህርት ቤቶች የመጻሕፍት ሰጦታ ተበረከተ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከአዲስ አበባ ከተማ ለተመረጡ 10 ትምህርት ቤቶች 500,000/አምስት መቶ ሺህ /ብር የሚገመት የመጻሕፍት ሰጦታ አበረከተ።

ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማዕከል የጀመረው የመጻሕፍት እና የመዛግብት አውደ ርዕይ አካል የሆነው ይህ የመጻሕፍት ልገሳ መርሃ ግብር የየትምህርት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን፣ የክበባት ተጠሪ መምህራን፣ የአውደ ርዕዩ ጎብኚ ወላጆች እና የተቋማችን የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተከውኗል።

Share this Post