የሰልጣኞች ምረቃ ተከናወነ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከየካቲት 28 ቀን 2ዐ14.ዓ.ም ጀምሮ በሰነድ ሥራ አመራር እና መዛግብት አስተዳደር ዙሪያ ያሰለጠናቸውን 63 የዘርፉ ባለሙያ ሰልጣኞች መጋቢት 9 ቀን 2ዐ14 ዓ.ም አስመርቋል፡፡
በተቋሙ የሰነድ ሥራ አመራር እና ቤተመዛግብት አስተዳደር እንዲሁም በቤተመጻሕፍት ሙያ ሳይንስ ዘርፍ የስልጠና እና የምክር አገልግሎት ሥራን የሚሠራው የአብያተ መዛግብትና አብያተ መጻሕፍት ጥናትና ምርምር ስልጠና ዳይሬክቶሬት እንዳሳወቀው ሰልጣኞቹ 51 ሴት እና 12 ወንድ ሲሆኑ ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ ብ/ብ/ሕዝቦች፣ ከአማራ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ናቸው፡፡
የሥራ ክፍሉ ባልደረባና ስልጠናውን ከሰጡት መሐል አንዱ የሆኑት አሰልጣኝ ሐብቴ ቶሎሳ እንደገለፁት ስልጠናው ሰልጣኞችን በሙያው እውቀትና ክህሎትን ያጣመረ፣ የሰነዶችን ጠቀሜታና ፋይዳ በአግባቡ የተገነዘበ የዘርፉ ባለሙያ ይሆኑ ዘንድ ያግዛቸዋል ብለዋል፡፡
 

Share this Post