በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ሰራተኞች አመታዊ ውይይት ተካሄደ


የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት  ሰራተኞች የ2014 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና በ2015 ዕቅድ ላይ በአዳማ ከተማ የባ ሆቴል ጥልቅ ውይይት አድርጓል። 
ተቋሙ በ 2014 ዓ.ም እያንዳንዱ የሰራ ክፍል አቅዶ የነበረውን እና የፈፀመውን በማነፃፀር በዕቅድ ፖሊሲ ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀው ሪፖርት እየቀረበ በእያንዳንዱ አፈፃፀም ላይ ጥያቄ እየቀረበባቸው ውይይት እየተደረገ ሲሆን፤ የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ እና የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ መነሻ በማድረግ የቀጣይ የ2015 ጠቋሚ ዕቅድ ላይም ውይይት በማድረግ ዕቅዱን ተቋማዊ ማድረግ ተችሏል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ልቦና መምህር እና አማካሪ የሆኑት ዶ/ር እንዳልካቸው ተፈራ፣ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ለረዥም አመታት በማስተማርና በምርምር ስራ ላይ ያሉት ዶ/ር ጋሻው ኃይሌ እና በባህልና ስፖርት ሚኒስተር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ዳይሬክተር በሆኑት በወ/ሮ ወይንሸት ኃ/ማርያም በ2015 ዓ.ም የተሻለ የስራ አፈፃፀም ይመዘገብ ዘንድ ከሰራተኞች ሥነ-ምግባር ጋር በተያያዘ አነቃቂ ስልጠናዎችን ሰጥተዋል፡፡ ስልጠናዎቹ  በአዲሱ ዓመት የስራ ዘመን ቀድሞ የነበሩ ጥሩ የአገልጋይነት መንፈስ በማጠናከር እና ለስራ ስኬት እንቅፋት የሆኑትን በማስወገድ መልካም ጎኖችን ከቀድሞው በተሻለ አጠናክሮ ተቋምን መለወጥ የሁሉም ድርሻ ሊሆን እንደሚገባ የሚያጎሉ ስልጠናዎች ናቸው::
በዝግጅቱ ማብቂያም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከየስራ ክፍሉ ከፍተኛ አፈጻጸም ለነበራቸው ባለሙያዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።

Share this Post