ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

የአንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ተርጓሚና የጥበብ ሰው
ነብይ መኮንን ያዘጋጃቸውን ፤
• ነገም ሌላ ቀን ነው
• የእኛ ሰው በአሜሪካ
• የመጨረሻው ንግግር የተሰኙ መጽሐፍትን ሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ለማስመረቅ የተዘጋጀውን ፕሮግራም በሚመለከት ሐሙስ ነሐሴ 26 ቀን2014 በኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት አዳራሽ ከቀኑ 8 ሰዓት ተኩል ላይ በቦታው ለተገኙት የሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መገለጫ ተሰጥቷል።
ጋዜጣዊ መገለጫውን የሰጡት  ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ተርጓሚና የጥበብ ሰው ነብይ መኮንን፣ የጋዜጠኛ ነብይ መኮንን አርት ማኔጀር ዳዳይት ሐድራ፣ አቶ ያሬድ ተፈራ ከኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት እና የግራር የጠቢባን መናኸሪያ ዋና የስራ ኃላፊ አቶ ሴሚናስ ሐድራ ናቸው።
በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አገልግሎት የመርሐ ግብሩ አጋር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ተቋሙ በቀጣይ አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ተርጓሚና የጥበብ ሰው ነብይ መኮንን በቀጣይ ለህዝብ  ሊያደርሳቸው በዝግጅት ላይ ያሉትን ስራዎች እንደሚደግፍም ተነግሯል።
የመጽሐፍ ምረቃው ሰኞ ነሐሴ 30 ቀን2014 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በቦሌ ፍሬንድሺፕ ሆቴል እንደሚከናወንና የቪአይፒ መግቢያ 1000 (አንድሺህ) ብር እና የመደበኛ መግቢያ 300 ብር እንደሆነየተገለፀ ሲሆን ትኬቱ በጃፋር መጽሐፍት መደብር፣ በፍንደቃ እና አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዝግጅት ቢሮ እንደሚገኝ ጠቁመው በዕለቱ ከሚመረቁት መጽሐፍት በተጨማሪ ሌሎቹም የደራሲው ስራዎች በአንድነት በልዩ ጥቅል ለአንባቢያን ለሽያጭ እንደሚቀርብ አሳውቀዋል።

Share this Post