ለተቋሙ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጽሐፍት አገልግሎት ለዳይሬክተሮች፣ ለቡድን መሪዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲቲዩት አሠልጣኝነት ከመጋቢት 05 - 07/ 2014 ዓ.ም. በኢንስቲቲዩቱ የስልጠና ማዕከል ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው በማኔጅመንትና በሊደርሺፕ መሠረታዊ እውቀት ላይ፣ በውሳኔ ሰጪነትና ችግር ፈቺነት ላይ፣ በተግባቦት እና ግጭት መፍታት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከመሪነት ጋር በማያያዝ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውን ከተቋማዊ ነባራዊው ሁኔታ ጋር በማቆራኘት ተግባራዊነቱ ላይ ተነሳሽነት ፈጥሯል።

 

Share this Post