የንባብ ሳምንት እና አውደ ርዕይ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በደመቀ ሁኔታ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ከንባብ ለህይወት ኢትዮጵያ ፐሮጀክት ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከሐምሌ 28 እስከ ነሐሴ 02/2014 ዓ.ም የሚቆየው የንባብ ሳምንት እና አውደ ርዕይ በደመቀ ሁኔታ ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም ተጀምሯል፡፡

በመክፈቻው ስለ ዓባይ የተዜሙ በጋዜጠኛ ቢኒያም ልጆች የተዘጋጀ ህብረ ዝማሬ የጀመረው በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ስለ ንባብ የሐሳብ ልውውጥ የንባብ ምንነትና ደረጃዎች ላይ ሰፋ ያለ ውይይትና ማጣቀሻዎችን በምሳሌ በመጠቀም ለተሳታፊው ገለጻ ከተደረገ በኃላ የዝግጅቱ ቀናት የሆኑትን የንባብ ሳምንታት ስለንባብ በመወያየት ለተዘጋጁ መድረኮች ካሉን ሰዓት በመመደብ የመጽሐፍ ውይይቶች ላይ እንድንሳተፍ በማለት መልዕክት ለታዳሚው አስተላልፈው፡፡

በመቀጠልም የንባብ ለህይወት ፕሮጀክት መስራች አባል እና የደራሲ ውድነህ ክፍሌ ልጅ አራት ጓደኞቼና ሌሎች መጽሐፍ ጸሐፊ ለሆነችው ህሊና ውድነህ ክፍሌ ምስጋናና መልዕክት አዘል ጽሑፍ ቀርቧል፡፡

በጠዋቱ መርሐ ግብር የተዘጋጀው ንባብ ለሕይወትና የምርምር ተቋማት አውደ ርዕይ ተከፍቶ በታዳሚዎች ሲጎበኝ ለቀሪዎቹ አምስት ተከታታይ ቀናትም አውደ ርዕዩ ለታዳሚው ክፍት ተደርጓል፡፡

Share this Post