በተቋሙ የሥነ-ምግባር ስልጠና ተሰጠ

መጋቢት 28/2ዐ14 ዓ.ም የአገልግሎቱ የሥነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና መከታተያ ቡድን በተቋሙ “ኦኘሬሽናል” ስራ ይሰራሉ ብሎ ለመረጣቸው የሥራ ክፍሎች ከስራ ሥነ-ምግባር እና መሪነት ጋር በተያያዘ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የዕቅድ ዝግጅትና ክትትል፣የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር፣ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች፣ የኦዲት፣ የግዢ ፋይናንስ፣ የንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች የቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሲሆኑ፤

ስልጠናውም “Ethics and Leadership in organization” በሚል ርዕስ በተቋሙ የአብያተ መዛግብትና አብያተ መጻሕፍት ስልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት አሰልጣኝ በአቶ እስራኤል በዙ ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን አስመልክቶ የተቋሙ የሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና መከታተያ ቡድን ባለሙያና የስልጠናው አስተባባሪ መ/ር ካሳዬ ስሜ እንደገለፁት ስልጠናው የሥራ ክፍሎቹ ሠራተኞች የስራ ሥነ-ምግባር እና የመሪነት ምንነት ብሎም ሚናው ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማስፋት ለተሻለ አፈጻጸምና ተቋማዊ ለውጥ ያግዛቸዋል በማለት መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡  

Share this Post