News News

"ክረም ተ መጻሕፍት!" እንዲሁም "በመጻሕፍት እንታረም!"  በሚል መሪ ቃል የክረምት ንባብ ዘመቻ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ሊጀመር ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ በዋናነት የሚመራውና ከሳይንስና እውቀት ሽግግር ቴክኖሎጂ ማህበርና ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ጋር በመተባበር የሚካሄደው የክረምት የንባብ ዘመቻ ከስኔ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ይጀመራል።

አዲስ አበባ ከተማና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን ጨምሮ በሚካሄደው ክረምተ ንባብ ድሬዳዋ ከተማና ድሬዳዋ ማረሚያ ቤት፣ደብረ ብርሀን ከተማና ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት፣ባህርዳር ከተማና የባህርዳር ከተማ ማረሚያ ቤት፣መቀሌ ከተማና መቀሌ ማረሚያ ቤት እንዲሁም ባሌ ሮቤ ከተማና ሮቤ ማረሚያ ቤት ዘመቻው የሚካሄድባቸው ከተሞች ናቸው።

ለዚህ የንባብ ዘመቻ ለእያንዳንዱ ከተማ የ100,000 (የአንድ መቶ ሺህብር መጻህፍት በግዢ የሚሰጥ ሲሆን የሳይንስ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማህበር ደግሞ አምስት ሺህ መጻሕፍትን ያበረክታል ተብሏል፡፡ ከዚህ ዘመቻ ህብረተሰቡ የተለያዩ ልምዶችና ዕውቀት ይቀስማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 

 


ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ግንቦት 29/2011 ዓ.ም. ኤጀንሲያችንን ጎበኙ። በጉብኝታቸውና በምክር አዘል ንግግራቸው ደንበኞቻችን እጅግ ደስተኛ ነበሩ። የሳቸውም ደስታ ከፊታቸው ይነበባል። ሀገራችን በጭንቅ ውስጥ በነበረች ጊዜ መፍትሄ የሆኑን እሳቸው በማንበብ ስለተገነቡና ሙሉ በመሆናቸው ነው። ወመዘክር መስራቹ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተደጋጋሚ ይጎበኙትና ያነቡበትም ነበር። ጊዜው ሆኖ ባያነቡም ዶ/ር አብይ ተቋሙን መጎብኝታቸው ለሁሉም ትልቅ ሞራል ነው። ቀድሞም ብዙ ድጋፍ ሲያደርጉልን ቆይተዋልና ምስጋናችንን እናቀርባለን። ዛሬም ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋልና ሌሎች ኃላፊዎችም የሳቸውም አርኣያነት ቢከተሉ መልካም ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ከክልልና ከማዕከል ለተውጣጡ 44 የዘርፉ ባለሙያዎች ከየካቲት 11-29 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድረስ ለአንድ ወር በመደኛ ሮግራም በቤተመጻሕፍት ሙያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናው የተለያዩ ዘርፎች ያሉት ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማ ለዘርፉ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ በሙያው የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በማፍራት የሀገሪቱ የቤተመጻሕፍት ሙያ ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ በዘርፉ የሚሰጠው አገልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ እንዲቻል ታስቦ  የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡

 


ኤጀንሲው 123ኛውን የአድዋ ድል በዓል “አድዋ የሰውነት ማህተም” በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከየካቲት 16-23 2ዐ11 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ አከበረ፡፡

ዝግጅቱ በዋናነት ከሰውኛ ኘሮዳክሽን ጋር የተዘጋጀ ሲሆን በተባባሪነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር በተባባሪነት የተዘጋጀ ነበር፡፡ በዝግጅቱም ላይ የኤጀንሲው ሠራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ወጣቶች፣ የድርጅት ተወካዮች እና አባት አርበኞች ታድመዋል፡፡

በዝግጅቱም ላይ ዐውደ-ርዕይ፣ የፊልም ፌስቲቫል፣ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የምሽት የዛፍ ሥር ወግ እና የፖናል ውይይት ዋና ዋናዎቹ የኘሮግራሙ አካላት ናቸው፡፡ የአድዋ ድል የጭቁን ጥቁር ሕዝቦችን እንባ ያበሰ፣ የፀረ-ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ትግል ውጤት አፍሪካውያንና ደቡብ አሜሪካውያን ከባርነት ቀንበር እንዲላቀቁ በር የከፈተ ለፍትህ ለነፃነትና ለእኩልነት እንዲሰፍን እንደጧፍ ነደው እንደሰም ቀልጠው ለሀገር ፍቅርና ክብር የተከፈለ ታላቅና ውድ መስዋዕትነት ነው፡፡

አድዋ የነፃነት ቀንዲል የፖን አፍሪካ መመስረት ፋና ወጊ ታሪክን የቀየረ በጨለማ ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች የሰለጠነውን እና በሳይንስ የዳበረውን የአውሮፖ ሀያላን መንግስታት ያንበረከከና የውርደት ካባቸውን ያከናነበ ዓለም አቀፍ የጭቁን ሕዝቦች የድል እና የነፃነት ቀን  ነው፡፡

አድዋ ጀግኖች አባቶቻችን ሊወሩንና ቅኝ ሊገዛ የመጣውን የጣልያን ጦር በአንድነትና በመተባበር በይቻላል መንፈስ ከዳር እስከዳር በሕብረት በመንቀሳቀስ ኋላቀር በሆነ መሳሪያ በመታገዝ ጠላትን ያንበረከኩበት የእናቶቻችንና የአባቶቻችን የነፃነትና የአንድነት ተምሳሌት እና የሕዝብ ድል በዓል ነው፡፡

የአድዋ ድል የሕዝብ ድል ነው፡፡ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ሴቶች፣ ወንዶች፣ ነገስታት፣ አርሶአደር፣ ነጋዴ፣ አዝማሪ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጐችና በአጠቃላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የአፍሪካውያንና የዓለም ጥቁር ሕዝቦች የሉዓላዊነት  በዓል ነው፡፡

የታሪክ መዛግብት እንደሚነግሩን የጦርነቱ ዋና መነሻ ምክንያት የጣልያን መንግስት የቅኝ ግዛት ፍላጎት መኖርና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ በመጣል ሲሆን የወጣው የስምምነት ውል አንቀጽ 17 እንደ ዋና ምክንያት ይጠቀሳል፡፡ የውጫሌ ውል አንቀጽ 17 ሲተረጐም የአማርኛውና የጣልያንኛው ትርጉም ሆን ተብሎ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ሉአላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ስለነበር የጦርነቱ መቀስቀስ እንደ ምክንያት ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ የካቲት 23/1888 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ጦርነቱ በአድዋ የተካሔደ ሲሆን በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ተጠናቋል፡፡

ከአድዋ ድል በኋላ በርካታ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ውጤቶች የመጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል የፖን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መጀመር፣ በርካታ የአውሮፖ መንግስታት በአዲስ አበባ ኤምባሲያቸውን መክፈት መቻላቸው በዘመናዊ የኢትዮጵያ የዲኘሎማሲ ታሪክ እንደመነሻ መቆጠርና ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ የዲኘሎማት መቀመጫ መሆንና መስፋት የመሰረተ ልማት /የመንገድ፣ ባቡርና መገናኛ ዘዴዎች መስፋፋት በአጠቃላይ ወደ ዘመናዊነት መጓዝ መቻል፡፡

በኢትዮጵያኒዝም የሚል የሀይማኖት እንቅስቃሴ መጀመር በአሜሪካ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ መቀንቀንና መስፋፋት፣ የጣልያንና ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ይህም ኢትዮጵያ ፍፁም ነፃና ሉዓላዊት ሀገር መሆኗ መረጋገጥ፣ ሌሎች በወቅቱ የነበሩ የአውሮፖ ሀያላን መንግስታት ቅኝ ግዛትን እንደ መብት የሚቆጥሩ ማለትም እንግሊዝና ፈረንሳይ ይህን ሽንፈት በመመልከት እጃቸውን መሰብሰብ መቻላቸውና ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን የድንበር ውል መዋዋል መቻላቸውና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ማክበራቸው ሌሎች በቅኝ ግዛት የተያዙ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን እንደ ተምሳሌት በመመልከት ከቅኝ ግዛት ነፃ ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመር መቻላቸው ዋና ዋናዎቹ የድሉ ትሩፋቶች ናቸው፡፡

የዝክረ-አድዋ ዋና ዓላማ አባቶቻችን የአንድነት ጽናትና አይበገሬነት ለአሁኑ ትውልድ ማስተማርና ወኔ ማስታጠቅ የሀገር ፍቅርና ሉዓላዊነት ምን ማለት እንደሆነ ማሳየት፣ አባቶቻችን ዘር ሃይማኖት ብሔር ማንነት ሀብትና ብልፅግና ሳይለያያቸው አንድ በመሆንና ሕብረት በመፍጠር እንዴት ሀገርን ከጠላትና ከወራሪ መታደግና ነፃነትን በመጐናፀፍ አንገትን ቀና አድርጐ መጓዝ እንደሚቻል የሚያስተምር ደማቅ የታሪክ አሻራ እና ህያው ምስክር ነው፡፡

በዝግጅቱ በርካታ ኘሮግራሞች የተካሄዱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዐወደ-ርዕይ፣ ፊልም ፌስቲቫል፣ ጥናታዊ ፅሐፍ ፣ የሙዚቃ ዝግጅት እና የአባቶች የዛፍ ሥር የምሽት ወግ ፣ የእግር ጉዞ እና የግብር ማብላት ፕሮግራም ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የዛፍ ስር የምሽት ፕሮግራም የተካሄደበት ዋናው አላማ አባቶቻችን እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን ሀገርን ሊወር የመጣውን  ጠላት ለመመከት ዛፍ ስር ቁጭ በለው በመምከር በመወያት እና ለመደማመጥ ያላቸውን ልዩነት በመተው አንድ በመሆን ሀገራቸውን ከጥፋት የታደጉ ሲሆን  ያሁኑ ትወልድም  ልዩነቱን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ያለውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አባቶቹ አስከብርው ያቆዩለትን ሉዓላዊት ሀገር ማስቀጠልና የአባቶቹን ታሪክ ለመዘከር ነው፡፡

በዝግጅቱ የፖናል ውይይት ሲካሄድ “የአድዋ ድል እና ኢትዮጵያ” ፣  “የኢትዮጵያ ሕዝቦች የፀረ-ቅኝ ግዛት ትንቅንቅ በአድዋ” ጦር ሜዳ በሚል የቀረቡ ሲሆን በውይይቱም ወቅት በርካታ ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጐባቸዋል፡፡

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት መከበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገች ሀገር ስትሆን ከነዚህም መካከል  ዓለም አቀፍ ተቋማትን በግንባር ቀደምትነት በመመስረት፣ በመምራት እና ድንጋጌዎችን በማክበርና በማስከበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተች ሲሆን ለምሳሌ እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፡ ሌግ ኦፍ ኔሽን አፍሪካ ህብረት ተጠቃሽ ሲሆኑ በተጨማሪ ሰላም በማስከበር እና በመጠበቅ እንደ ኮርያ፣ ሩዋንዳ፣ ላይቤሪያ፣ ሱዳን እና ኮንጎ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ሀገራችን ነፃነቷን ጠብቃ፣ አስከብራ ተፈረታ መኖር በመቻሏ ነው፡፡


የካቲት 2011 ዓ.ም

ኤጀንሲው በርካታ የጽሑፍ ሀብቶችን አሰባስቦ ለንባብ߹ለጥናትና ምርምር አገልግሎት እንደሚያውል ይታወቃል፡፡ ከዚህ ባሻገር በጥንታዊነታቸው በያዙት ጥልቅ ጥበባት እና በአዘገጃጀታቸው ጭምር አስደናቂ የብራና እና በልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ላይ የተጻፉ መጽሐፍት ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ቅርሶች የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በነጻ እየገቡ መጎብኝት የተለመደ ሲሆን በዚህ ወርም ከደቡብ ሱዳን የመጡ 25 ጎብኚዎች ኤጀንሲያችንን ጎንኝተዋል፡፡

ጎብኚዎቹም በተመለከቷቸው ቅርሶች መደነቃቸውን ገልጸፀው፡፡ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗንና ከጥንት ጀምሮ ብዙ ጠበብትና ባለሙያዎች ያሉባት ሀገር መሆኗን በተመለከቷቸው መረጃዎች ማረጋጋጣቸውን ተናግረዋል፡፡


News Archive News Archive

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 33 results.