News News

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ከትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከመቐለ ከተማ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጋር በመተባበር “በመጻሕፍት እንታረም በሚል መሪ ቃል ሰኔ 21/20011ዓ.ም በመቀሌከተማ ማረሚያ ቤት ተካሂዷል፡፡

ለመቐለው ዝግጅት ጉዞውን ሰኔ አስራ ዘጠኝ ወደ መቐለ ያደረገው ቡድን በሰኔ ሃያ አንድ ዝግጅቱን በመቀሌ ማረሚያ ቤት ጀምሯል፡፡

በዝግጅቱሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በኮማንደር ትበርዝ ሲደረግ የመክፈቻ ንግግር በኤጀንሲው የኢትዮጵያ ጥንትና ህግ ክምችት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወ/ሮ እስከዳር ግሩም የዝግጅቱ ዓላማ የንባብ ባህል በማዳበር የለማና የበለጸገ አእምሮ ያለው ዜጋ በመፍጠር ሀገርንና ወገንን የሚጠቅም ትውልድ ለማድረግ የመጽሐፍት የገበያ ትስስር በመፍጠር ለደራሲንና በዘርፉ ለሚገኙ ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡

የዝግጅቱም መሐል በታራሚዎቹ የተጻፉ ትምህርት አዘል የሆኑ ሥነ-ጽሑፎች እየቀረቡ ታዳሚውን እያዝናኑ እንዲማሩ ሲያደርጓቸው ተስተውሏል፡፡

ደራሲና ተርጓሚ ኃይለመለኮት መዋዕል እና ደራሲ እየሩሳሌም ነጋ የህይወት ልምድ ተሞክሮ ቀርቦ ከታራሚዎቹ ሀሳብና አስተያየት ሲሰጥ የደራሲ ኃይመለኮት መዋዕል ጉንጉን ረጅም ልብወለድ መጽሐፍ በማረሚያ ቤቱ አለመኖሩን ታራሚዎች ጠቁመው ደራሲው እንደሚልኩላቸውና ማንበብ እንደሚችሉ ገልጸውላቸው አምስት ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በደራሲ ኃይለመለኮት የተተረጎመ የዊሊያም ሼክስፒር “ኦቴሎ” ቲያትር መጻሕፍትም ለማረሚያ ቤቱ ደራሲው አበርክተዋል፡፡

በዕለቱም በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በተሀድሶና ልማት ዘርፍ በትምህርትና ስልጠና ዳይሬክተር የትምህርትና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ተከተል ለታራሚዎቹ ሲናገሩ ይህን ፕሮግራም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ በኢትጵያ ውስጥ ላሉት የህግ ታራሚዎች መሪ ቃል አዘጋጅቶ ይህን ስራ ሊሰራ መነሳቱ የሚበረታታና ቀጣይነት እንዲኖረው ገልጸው በህግ ታራሚዎች ላይ እንዲሰራ መደረጉ ትክክለኛ እይታ ነው ምክንያቱም የህግ ታራሚው በህግ ጥላ ሥር ሆኖ የሚኖር ዜጋችን ነው በፍርድ ቤት ውሳኔ ለረጅም ዓመት በማረሚያ ቤት ሊቆዩ የሚችሉ ታራሚዎች ይኖራሉ ለእነዚህ የህግ  ታራሚዎች በወቅቱ ያሉትን የውጭ እባ የሀገር ውስጥ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉትን ሁኔታዎች ከሚድያ ቴክኖሎጂ ውጪ የሚያስተዋውቋቸው የተለያዩ መጽሐፍትን በማንበብና በማወቅ በመሆኑ እንደፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስድስት ማረሚያ ቤቶች እንዳሉና በሁሉም ማረሚያ ቤቶች ታራሚዎች ተደራጅተው የራሳቸውን ገቢ እንዲያገኑ በማድረግ በተለያዩ ስልጠናዎች በማሰልጠንና በማስተማር አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው በማረሚያ ቤቶች ሁሉ የሚገኙትን ለማሳተፍ እንደማይቻልና ምክንያቱም ያሉት የህግ ታራሚዎች ማንበብ መጻፍ ማስላት ከማይችን ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው በመሆኑ በተለያ ስልጠናዎች ላይ ማሣተፍ ያልተቻለው የህግ ታራሚዎች በየታራሚው መምሪያ ዞን ቤተ-መጻሕፍት ተከፍቶ የንባብ እና የውይይት አገልግሎት በመስጠት የተለያ መጻሕፍቶችን በማንበብ እትሙን በማጎልበት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ተግባር ከዚህ በፊት በእነርሱም በዝዋይ ማረሚያ ቤት የንባብ ቀን የመጽሐፍት አውደርዕይ በማዘጋጀት አምስት መቶ ስልሳ መጻሕፍት የማበርከት ስራ መሰራቱን ገልጸው አሁንም ታዲያ ይህ መጽሐፍ ከኤጀንሲው መበርከቱ ታራሚዎቹ መጻሕፍቶችን በማንበብ አቅማቸውን እና እውቀታቸውን በማዳበር ያጠፉትን እና የበደሉትን ማህበረሰብ ይቅርታ በመጠየቅና በመፀፀት ለሀገሩና ለወገኑ የሚያስብ ዜጋ ማፍራት ስለሚቻል ፕሮግራሙ ለግዜው ብቻ ሳይሆን ቀጣይነት ባለው መልኩ በየዓመቱ መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

አክለውም በማረሚያ ቤት ውስጥ ያሉት መጻሕፍቶች ውስን በመሆናቸው አንዳንድ ታራሚዎች አንዱን መጽሐፍ ሁለትና ሶስት ግዜ እንዳነበቡት አስተያየት ሲሰጡ ሰምተናልና እኛም እንደፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አዲስ እየተገነቡ ባሉ ማረሚያ ቦች ደረጃውን የጠበቀ ቤተ-መጻሕፍት ለማደራጀት በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ተናግረው ከብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ ጋርም በጋራ እየተሰራ ያለው ነገር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ምክንያቱም ሁለቱም ተቋማቶች ሀገራዊ ግዴታ ያለባቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ የክፍልና የትምህርት ደረጃ የያዙ ሶስት መቶ አርባ አንድ መጻሕት ለማረሚያ ቤቱ ተወካይ ሲሰጥ በእለቱ በሥነ-ጽሑፍ ዘርፍ ለተወዳደሩ አምስት ታራሚዎች መጻሕፍት ፤ ኤጀንሲው ለማረሚያ ቤቱ ያዘጋጀውን የምስጋና ምስክር ወረቀት ከኤጀንሲው የስልጠናና ጥናት ምርምር ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተሩ ከአቶ መኰንን ከፈለ እጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡

የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተወካይ እና የባህል ልማት አስተባባሪ አቶ ዳዊት ትከቦ የዝግጅቱን ዓላማና በክልሉ መካሄዶ ያለውን ጠቀሜታ አስመልክቶ ለታሪሚዎቹ በመንገር ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

 

በመጨረሻም ከታራሚዎቹ መካከል ያነጋገርናቸው ታራሚ መ/ር ሞገስ ካልሃይ እና ታራሚ አዜብ እንደተናገሩት በትምህርት ቤቶችና ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታ በርካታ ቤተ-መጻሕፍቶች አሉ በማረሚያ ቤት ግን ስለማይኖር ማረሚያ ቤት ያለው ታራሚ ገዝቶ ለማንበብ ፍላጎቱም የለውም ታራሚው ተስፋ የመቁረጥ ነገር ስለሚታይበት ዓለምን ለማወቅ ደግሞ መረጃ ሀብት ነው ስለዚህ ቤተ-መጻሕፍት በማረሚያ ቤት መኖሩ በርካታ ሰው እንዲያነብና ቀድሞ የነበረውን አስተሳሰቡን እንዲቀይር ይረዳዋል ሴቶች እንደወንዶቹ እንዲያነቡም እድል ይፈጥራል ሌላው እንደዚህ ደራሲያን ከታራሚዎች ር በሚቀራረቡበት ወቅት ከህይወት ተሞክሯቸው ውጪ መጻሕፍቶችን ለማረሚያ ቤቱ ስለሚለግሱና አንባቢ እንዲፈጠር ስለሚያደርጉ ይህ ስራ በኤጀንሲውና በማረሚያ ቤቱ ተጠናክሮ ቢሰራ በማለት ተናግረዋል፡፡

የማህበረሰቡን የንባብ ባህል ለማዳበር የንባብ ሳምንት ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ከትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የማህበረሰቡን የንባብ ባህል ለማዳበር “ክረም ተ መጻሕፍት ” በሚል መሪ ቃል ሰኔ 22 /20011ዓ.ም በመቐለ ከተማ በእንድራእሲ ሎጅ የንባብ ሳምንት ሲካሄድ በዝግጅቱም ላይ በርካታ ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡

 

በዝግጅቱም መጀመሪያ በአቶ ግርማይ ፍሮዝ የሚያሰለጥነው የወወክማ መቐለ የሙዚቃ ቡድን ባህላዊ ውዝዋዜ አቅርቦ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በተወካይ በአቶ ዩናስ ከተደረገ በኃላ የመክፈቻ ንግግር በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ሲደረግ የዝግጅቱን ዓላማ፣መሪቃሉንና በክልሉ አጠቃላይ 1200 መጽሐፍት እንደተሰጠ ተናግረው እነዚህ መጻሕፍቶች ተማሪውም ሆነ ማህበረሰቡ በማንበብ እራሱንና ሀገሩን መለወጥ ይኖርበታል በማለት አበክረው ተናግረዋል፡፡

 

የደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕልና  የደራሲ እየሩሳሌም ነጋ የህይወት ተሞክሮ አስተማሪ በሆነ መልኩ ለታዳሚ ቀርቧል፡፡በዝግጅቱም ደራሲ እየሩሳሌም ነጋ ህጻን ሶሊያና ባቀረበችው ግጥም ተማርካ በእርስዋ የተፃፉ የልጆች መጻሕፍትን ለወወክማ መቐለ በስጦታ እንደምታበረክት ቃል ገብታለች፡፡

 

በመቀጠልም ጅማሮው ላይ ሲያዝናና የነበረው ወወክማ መቐለ የሙዚቃ ቡድን ንባብ ላይ ያተኮሩ በርካታ ግጥሞችን፣መነባንቦችንና አጭር ድራማ በማቅረብ ታዳሚውን አዝናንቷል፡፡

ከኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ይኩኖአምላክ እጅ ታዳሚውን በግጥምና በስነ-ፅሑፍ ላዝናኑት የመቐለ ወወክማ የሙዚቃ ቡድንና ለቡድኑ መሪ ለአቶ ግርማይ መጻሕፍት ሲበረከት በጋራ ለማዘጋጀት እቅዱን ቢያቅድም ብዙም በኃላፊነት ሥራዬ ነው ብሎ መስራት ላልደፈረው የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የምስጋና ምስክር ወረቀት በማበርከት ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


ኤጀንሲው “ክረም ተ መጻሕፍት በአንባቢዋ ድሬ” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ከተማ ከድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት በስኬት ተጠናቋል፡፡ፕሮግራሙ ሰኔ 19 ቀን 2011ዓ.ም. በለገሀር የባቡር ጣቢያ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በከተማው የትምህርት ቢሮ የማርሺንግ ባንድ እና ከአስር ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ የተማሪዎች ሰልፍ ታጅቦ በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል፡፡ በመክፈቻው ሥነሥርዓት ላይ የከተማው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙራድ በደዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ በፕሮግራሙ ዓላማና አስፈላጊነት ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

የንባብ ሳምንቱ በተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር፣ የፓናል ውይይቶች፣ ኤግዚብሽን፣ የመጽሐፍት ሽያጭ፣  የንባብ ክበባትን በማቋቋም የመጽሐፍት ልገሳን እና የስነጽሑፍ ምሽትን ያካተተ ነው፡፡ የፓናል ውይይቶቹ ላይ የኤጀንሲው ባለሙያዎች ጥናታዊ ጽሑፎችን አቅርበው ሰፊ ምክክር የተደረገበት እና በደራሲ ዘነበ ወላና በደራሲ እሴተ ታደሰ የንባብ ልምድና ተሞክሮ የተገለጸበት መድረክ ነበር፡፡ በዚህም የንባብ ባህላችን የሚያድግበትን መንገድ ለማመላከት ተሞክሯል፡፡የዚህ ጉባኤ ተሳታፊዎች ከከተማው ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራንና ተማሪዎች፣ የመንግስት ቢሮ ሰራተኞችና የወጣት ማዕከላት ሰራተኞችና የቤተ መጻሕፍት ሰራተኞች ይገኙበታል፡፡  

በተመሳሳይ “በመጻሕፍት እንታረም” በሚል መሪ ቃል ከድሬዳዋ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጋር ለድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ታራሚዎች የተዘጋጀው ፕሮግራም ሰኔ 21 ቀን 2011ዓ.ም. በማረሚያ ቤቱ ኣዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በዚህ ዕለት ደራሲ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ እና ደራሲ እሴተ ታደሠ ታራሚዎቹ በማንበብ ራሳቸውን በእውቀት እንዲያንጹና በመጻሕፍት መታረምን እንዲያዘወትሩ መክረዋል፡፡ በተለይም ደራሲ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ በ20 ዓመት የማረሚያ ቤት ቆይታቸው እንዴት በማንበብ ራሳቸውን እንዳሳደጉና ደራሲ እከመሆን እንደደረሱ ምሳሌ ነኝ ብለው መክረዋል፡፡ በዋናነት ታራሚው የራሱን ንጽሕና እንዲጠብቅ፣ ያለበትን ሁኔታ መቀበልና ራሱን ማሳመን ተገቢ መሆኑን፣በማንበብ ራሱን ማነጽ እንደሚገባው በአንክሮ መክረዋል፡፡ታራሚዎቹ በንባብ ያዳበሩትን የግጥም ክህሎት አቅርበው ታዳሚውን አስደንቀዋል፡፡

በመጨረሻም ኤጀንሲው ለማረሚያ ቤቱ በግዥና በስጦታ ያሰባሰበውን መጻሕፍት በመለገስ እንዲሁም ማረሚያ ቤቱ ለዚህ ፕሮግራም ስኬት በመተባበሩ የምስጋና ምስክር ወረቀት በመስጠት የዕለቱ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡ 

በሌላ መኩል የዚሁ ፕሮግራም አካል የሆነው የሥነጽሑፍ ምሽት ሰኔ 21 ቀን 2011ዓ.ም. በድሬዳዋ ራስ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በመክፈቻ ላይ የአፍረን ቀሎ የባህል ቡድን  የሀረርን ባህላዊ ዘፈን በውዝዋዜ  አጅበው አቅርበዋል፡፡ የግጥምና የሥነጽሑፍ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች የግጥምና የመነባንብ ሥራዎቻቸውን አቅርበው ታዳሚዉን አስደምመውታል፡፡

በሥራዎቻቸው የተደነቁትና የሚያንጽ ምክር የለገሷቸው አንጋፋው ደራሲ ዘነበ ወላ ይህንን ችሎታችሁን በማንበብ ልታዳብሩት ይገባል ብለዋል፡፡ በተለይም አንድ ሰው በየቀኑ ለ15 ደቂቃ በማንበብ ጥሩ በሳምንት ከሁለት አስከ ሶስት መጻሕፍትን ስለሚያነብ ጥሩ አንባቢ ይወጣዋል ብለዋል እና ይህንን ልታዳብሩት ይገባል ብለው ምክራቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በማጠቃለያ ላይም ኤጀንሲው ለተወዳዳሪዎች የማበረታቻ የመጽሐፍት ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡  

  


መጋቢት 12/2011 ዓ.ም በአረማያ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ሳይንስ የሶስተኛ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎችወንድ 39/ሰላሳ ዘጠኝ/ ሴት 8 /ስምንት/ በድምሩ /47/አርባ ሰባት ተማሪዎች የኤጀንሲውን ላይብረሪዎች ጎበኙ፡፡ ተማሪዎቹ በመጀመሪያ በህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  አቶ ሽመልስ ታዬ ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች አጠቃላይ ዝርዝር ከተገለፀላቸው በኃላ ለመጡበት ዓላማ ፍንጭ ይሰጣቸዋል በማለት የተዘጋጀ ብሮሸርና መፅሔት ተሰጥቷቸው ወደመጡበት ጉዳይ ተራ በተራ በየክፍሎቹ እየገቡ እንዲጎበኙ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡

ተማሪዎቹ በመጀመሪያ እንዲገቡ የተደረገው ወደመዛግብት ወደተባለው የስራ ክፍል ነበርና በክፍሉም ቀድሞ በባለሙያው ጥቂት ገለፃከተደረገ በኃላ በመዛግብት ንባብ አገልግሎት አሰጣጥ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ አብይ ሀይሉ የመዛግብትን ምንነት ከሳይንሳዊው ትርጓሜው ጀምሮ ተቋሙ እንዴት እየሰራ እንደሚገኝ ሰፊ ገለፃ ተሰጥቶ ተማሪዎቹም ጥያቄ አንስተዋል ከጥያቄዎቹም የተደራጀው የመዛግብት ብዛት ምን ያህል ነው? በክፍሉ ያለውን የአየር ሁኔታ በምንና እንዴት ነው የምትቆጣጠሩት? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተው ቡድን መሪውም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በመቀጠልም በኢትዮጵያ ጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርየቀረፀ ድምፅና ላይብረሪ ክፍል ገብተውም እዛም ጠለቅ ያለ መረጃ ከክፍሉ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የህትመት መፅሐፍ /ISBN/ ከፍተኛ ባለሙያ ወ/ሮ ቅድስትጌታቸው ግንዛቤ ተሰጥቷቸው ተማሪዎቹም የተለያዩ ጥያቄዎችን በግልም በግሩፕም እያነሱ ሲጠይቁ ከባለሙያዋ ያልተሰላቸ ምላሽ በመስጠት ተጠናቆ ወደ ጥንታውያን ጽሑፎች አገልግሎት ክፍል እዛም እንደቀረፀ ድምፅና ላይብረሪ ክፍልበባለሙያው አቶ ካሳይ ስሜ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ በህክምናውም በኪነ ስነ-ጥበቡም ዘርፍ የስልጣኔ መጀመሪያ እንደሆነች ተጠቃሽ ምሳሌዎችን በመስጠትና የሚታዩ የብራና ፅሁፎችን ብርቅና ድንቅ የሆኑ የጥበብ ስራዎችን በማስጎብኘትና ሰፋ ያለ ዕውቀትን በመስጠጥ እዚህ በመምጣታችሁ ሀገራችሁን የማወቅና ለቅርሶቻችን መጠበቅ እኔም ያገባኛል የሚለው ስሜትን ይጭርባችኃል ቅርሶች ተጠብቀው ለትውልድ መቆየታቸው መጪው ትውልድ ከማንነት ጥያቄ ውስጥ እንዳይገባ ይረዳዋልና ቅርሶችን መጠበቅ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድርሻ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረው ስለመጣችሁ ደስ ብሎኛል በማለት ሃሳባቸውን ጨርሰዋል፡፡

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ጥናት ክፍልን በወፍ በረር ተመልክተው ወደማይክሮ ፊልምና ኦዲዮቪዥዋል ክፍል በቡድን መሪው በመምህር  ኃይለ ሚካኤል ጌታሁን ጥሩ ገለፃ ተሰጥቶ ጉብኝቱ ተጠናቋል፡፡

የህዝብና ዓ/ዓ/ግ/ክፍልም ለአንዳንድ ጉብኚዎች የተለያዩ ቃለ-መጠይቅ አድርጎ ነበርና ኤጀንሲው እየሰራ ያለውን ተግባር እና በየዘርፉ የሚገኙ ባለሙያዎችንም ያላቸውን ክህሎት አድንቀው በኢትዩጵያ ብቻ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ዓይኖች ማረፊያ የሆኑ የብራና መፅሐፍቶች ከሁሉም በተለየና ከዚህ በጨመረ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግላቸውእንደሚገባ ተናግረው አክለውም ይህ ሲባል ግን ሌሎቹ መተኪያ አላቸው አይጠበቁ ለማለት እንዳልሆነ እንዲታወቅ ገልፀው ከዚህ በተሸለ ለመስራትና ሀገራችንም እንደሌሎች እንደአደጉ ሀገሮች ለመስራት ኤጀንሲውዲጂታላይዜሽኑ አሰራርተፋጥኖ ተግባር ላይ እንዲውልም ተናግረዋል፡፡


ከክልሎችና ከከተማ መስተዳድር ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ከማዕከል ለተውጣቱ 50 የሪከርድና መዛግብት ባለሙያዎች ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና አርብ መጋቢት 13/2011 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡

ስልጠናው ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማም በዘርፉ የሚታየውን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ በሙያው የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በማፍራት የሀገሪቱ የቤተመፃህፍት ሙያ በዘመናዊ ደረጃውን በጠበቀ መንገድና በጥራት ለመያዝ እንዲያስችል እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

በስልጠናውም መጨረሻ ከሰልጣኖች የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ስልጠናው በጣም ጥሩ ሆኖ የአይቲ ስልጠና ሰዓት አንሶናል ቢጨመር? ከጠበቅነው በላይ ነው ለስራችን ጠቃሚነውብዙ ግንዛቤ ተፈጥሮልናል ለሥራችን ነገር ግን ከክፍለ ሀገር  የሚመጡ ሰልጣኞች አልጋ ውድ ስለሆነ ኤጀንሲው ቢያስብበት? ስልጠናውን ወደ ስራ ለመቀየር ለከፍተኛና ለመካከለኛ አመራሩ ግንዛቤ ቢፈጠር? አዳራሹ ጠባብ ነው ሙቀት አለው አይሲ ቢኖር? ስልጠናው አሳታፊ አይደለም ቢስተካከል? ማኑዋል ቢኖረው? አይቲ ላይ ቅሬታ አለን  ሰልጣኙ እኩል ግንዛቤ የለውም ምንም ኮምፒውተር ነክቶ የማያውቅ አለ ሌላው ደግሞ ሙሉ ስራውን በኮምፒውተር የሚሰራ ነው አሰልጣኟ ከእርስዋ ዕውቀት መጀመሪያ ስለጀመረች ስልጠናው ሁሉንም  ያማከለ አይደለም? ለዚህ ስልጠና አክሰስ እንደውም አያስፈልግም? ከስልጠናው እንደውም ቢወጣ ጥሩ ነው የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው የስልጠናው ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ከፈለ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ለሰልጣኞቹ ከኤጀንሲው የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  በአቶ ሽመልስ ታዬ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡


ኤጀንሲው ከጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ከጅማ ዞን ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ ከጅማ ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር “ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት የሥነ-ፅሑፍ ውጤቶች እና አውደ-ርዕይ፣ የመጻሕፍት ሽያጭ ና ግንዛቤ ማስጨበጫ የፖናል ውይይቶች ከመጋቢት 21-25/ 2ዐ11 ዓ.ም በጅማ ከተማ አካሂዷል፡፡

ዝግጅቱን የከፈቱት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶይኩኖዓምላክ መዝገቡ የሥነ-ፅሁፍ ውጤቶች የአንድን ሀገር ባህል፣ወግ፣ልምድ ፣ ፍልስፍናና የቋንቋ ዕድገት የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ እና የመረጃ ምንጮች በመሆናቸው ዜጎች ሲያነቧቸው ዕውቀት ሊገነቡባቸው߹ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሊያገኙባቸው እንደሚገባ ተናግረው አክለውም አሁን ባለንበት ዘመን መረጃን በማዛባትና በማዛነፍ በህብረተሰቡ መካከል ውዥንብር የሚፈጥሩ በርካቶች በመሆናቸው ይህንን የሚፈታውን መረጃ በማሰባሰብና የንባብ ባህልን በማሳደግ በንባብ የበለፀገ ዜጋ በማፍራትና የሀገሪቱን የልማት ጉዞ ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና ስላለው ወጣቱ ትውልድ ላይ በሰፊው ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም በንባብ ዙሪያ የደራሲያን ተሞክሮ፣ የተማሪዎች ግጥም፣ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዶ ለግጥም አቅራቢዎችና ለጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊዎች ከኤጀንሲው የእውቅና ምስክር ወረቀት ፣ የመፀሐፍና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቷላቸዋል፡፡

በኤጀንሲውና በጅማ ዩኒቨርስቲ ሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ አዘጋጅነት የስነ-ፅሁፍ ምሽት ተካሂዶ በዝግጅቱም የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የግጥም፣ የመነባንብና አጭር ልብወለድ የፈጠራ ስራዎች ቀርበዋል ደራሲ ኃይለ መለኮት መዋል እና ጋዲሳ ብሩ ልምዳቸውን ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አካፍለው ተማሪዎች የእነርሱን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በዘመናዊ የሪከረድ ስራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር እንዲሁም የመረጃ ስርዓት በተመለከተ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በጅማና አካባቢው የሚገኙ ሪከርዶች ከፍተኛ ውድመት እየደረሰባቸው መሆኑና እንዴት መታደግ እንደሚገባ ጥናት ቀርቧል፡፡በጥናቱ መሰረት የጅማ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነቱን ወስዶ እየሰራ እንደሆነ በመጥቀስ ሁሉም ባለድርሻ አካት የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦ በጉባዔው ሴቶች߹ወጣቶች߹የዩኒቨርሲቲው መምህራን߹ተማሪዎች߹የጅማ ከተማ ነዋሪዎች እና ከየወረዳው የተጋበዙ እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

 


News Archive News Archive

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 30 results.