News News

የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ፣ ከአማራ ብሔራዊ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከባህርዳር ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር "ህዳር ሲታጠን መጽሐፍ ሲተነተን " በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የንባብ ሳምንት፣ የሥነጽሑፍ ውጤቶች ሽያጭና አውደ ርዕይ፣ የንባብ ሳምንትና የፓናል ውይይት አንድ አካል የሆነው የህጻናትና የቤተሰብ ንባብ የተካሄደው በባህርዳር ከተማ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዳራሽ ነው።

በመርሀግብሩም፡-

ወላጆች ለልጆች ተረቶችን አንብበዋል።

የህጻናት እና የቤተሰብ የንባብ ጥያቄና መልስ ተካሂዷል።

በተማሪዎች መካከል የምንባብ ትውስታ ጥያቄና መልስ ውድድር ተከናውኗል።

ደራሲ ህይወት ተፈራ ቤተስብ ለንባብ ባህል መስፋፋት ያላቸውን ሚና አስመልክታ ሀሳብ አካፍላለች።

ለተወዳዳሪዎች እና ተሳታፊዎች የመጻህፍት ሽልማት ተበርክቷል።


"ህዳር ሲታጠን መጽሐፍ ሲተነተን"
ሀገር አቀፍ የንባብ ሳምንት መርሀግብር አንድ አካል የሆነው የውይይት መድረክ በባህርዳር እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ ከአማራ ባህልና ቱሪዝምና ከባህርዳር ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ከህዳር 12 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ መርሀግብር አንድ አካል የሆነው ይህ ውይይት በባህርዳር ዩንቨርስቲ ፔዳ ግቢ ትልቁ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ የውይይት መርሀግብር ላይ:-

"የንባብ ባህል በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ ማረው ዓለሙ (ዶ/ር)
"የንባብ ክሂል" በደራሲ ሀይለመለኮት መዋዕል

"ህዳር ሲታጠን ታሪካዊና ባህላዊ ገጽታው" በመምህር ተመስገን በየነ
"የጣና ደሴት ሕያው ላይብረሪ"በተጓዥ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም
"የንባብ ባህል በግዕዝ ሥነ ጽሁፍ ውስጥ" በአማን ግሩም (አባ) ጥናታዊ ወረቀቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።


ህዳር 15/2012 ዓ ም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ከጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ፣ ከሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር በመጡ እንዲሁም በኤጀንሲው የዘርፉ ምሁራን በዲጂታል ላይብራሪና የህትመት ዝግጅት ደረጃ በኢትዮጵያ እና አብያተ መዛግብት መቋቋም ታሪካዊ አሻራዎችን ከመጠበቅ እስከ ማስቀጠል እና በመሳሰሉት ርዕሶች ላይ ውይይት ተካሄደ።

"እስርን ያመለጥነው በንባብ ነው።"
ደራሲት ህይወት ተፈራ

በባህርዳር ማረሚያ ቤት ታራሚዎች ተጎበኙ፤ መጻሕፍት ተበረከተላቸው።

በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው "ህዳር ሲታጠን መጽሀፍ ሲተነተን" በሚል አብይ መሪ ቃል ስር በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የሥነ ጽሑፍ አውደ ርዕይ፣ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ፣ ሽያጭ፣ የንባብ ሳምንት እና የውይይት መድረክ መርሀ ግብር አንድ አካል የሆነው መርሀ ግብር አንድ አካል በሆነውና በባህርዳር ማረሚያ ቤት በተካሄደው ስነስርዓት ላይ የባህር ዳር ማረሚያ ቤት ታራሚዎች፣ ሀላፊዎች፣ የጥበቃ ሰራተኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች፣ ደራስያን፣ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኑ አምላክ መዝገቡ እና የባህር ዳር ማረሚያ ቤት ምክትል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር መልካሙ አዛናው በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በከፈቱት ዝግጅት ደራሲ ህይወት ተፈራ በዘመነ ደርግ በፖለቲካ ምክንያት በነበራቸው ቆይታ
"ራሳችንን ከውጭው አለም ጋ የምናገናኘውም ሆነ የእስርን መጥፎ ዘመን ያለፍነው በመጻሕፍት ንባብ ነው። ጊዜአችንን በቤተመጻሕፍት ለማጥፋትና መጻሕፍትን ለማንበብ በሰልፍ ነበር የምንዋሰው። መጻሕፍት ከክፉ ነገሮችና አመለካከቶች የምናመንጥበት መንገድ ነው።"
በማለት የመጻሕፍትን ወዳጅነትና የንባብን ጠቀሜታ ለታራሚዎች አካፍላለች።
ጋዜጠኛ እና ደራሲ ሄኖክ ስዩም ለታራሚዎች ባስተላለፈው መልእክት የተለያዩ ደራስያን እና ተርጓሚዎች የስነ ጽሑፍ ስራዎቻቸውን ለማበርከት ማረሚያ ቤቶች የነበራቸውን ሚና አንስቷል።
"ማረሚያ ቤት ሆናችሁ ራሳችሁን ከማረሚያ ቤት ውጭ የምታገኙት በመጻሕፍት አማኝነት ነው። " ያለው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ሄኖክ ስዩም " ጊዜአችሁን በአግባቡ ከተጠቀማችሁ ስለማርፈድ ሳይሆን ስለመቅደም ነው የምታስቡት።" ብሏል
ሌላው በማረሚያ ቤቱ ልምዳቸውን ያካፈሉት መምህር መሰረት አበጀ ናቸው። ከእርሳቸው በተጨማሪም አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን፣ መምህርና ደራሲ ሀይለመልኮት መዋዕል፣ ደራሲና ተርጓሚ ጌታነህ ሀሳቦቻቸውን ካካፈሉት እንግዶች መካከል ናቸው።
በዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይም ደራስያን በግላቸው በስጦታ ከሰጡት በተጨማሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ለባህርዳር ማረሚያ ቤት ቤተ መጻሕፍት ከ600 በላይ የተለያዩ መጻሕፍትን ለግሷል::

በበፍቃዱ አባይ የተዘገበ


በባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው የንባብ ሳምንት የመጽሐፍት አውደርዕይና የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ህዳር 13/2012ዓ.ም.በድምቀት ተከፍቷል።
የባህር ዳር ክልላዊ መስተዳድር የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ መላኩ አላምረው የባህር ዳር ዪኒቨርሲቲ ኢንፎርሜሽን ስትራቴጂ ኮሚዪኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት እና የኤጀንሲያችን አመራሮች የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ከ10 ት/ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎችና ርዕሳነ መምህራን በተገኙበት በክልሉ ማርሽንግ ባንድ እና በተማሪዎች ሰልፍ ነበር የተከፈተው።
በመቀጠልም የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር በሙሉአለም አዳርሽ ተካሂዷል ።
በደራሲያን ምክርና ተረት ተነቧል።
ስነጽሁፍ ያቀረቡና በውድድሩ ላይ የተካፈሉ ተማሪዎች በኤጀንሲው ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

News Archive News Archive

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 33 results.