News Archive News Archive

Back

5ኛው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባኤ በመቐለ ከተማ ተካሄደ (ሰኔ 05/2011 ዓ.ም)

5ኛው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባኤ በመቐለ ከተማ ተከናወነ። የዓመቱ መሪ ቃል "ግዕዝ ወሥነ ፈውስ" "ግዕዝና ሥነ-ፈውስ" ፕ/ር ኸንድያ ገ/ኃይወት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ታዳሚውን የተቀበሉ ሲሆን በመክፈቻው ላይ የኤፌድሪ ባ/ቱ/ሚ/የባህል ዘርፍ ዴኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት በንግግር ከፍተውታል። ግዕዝና የጉባኤው አስፈላጊነት ላይ እንዲሁም በመሪ ቃሉ ላይ አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሰፊ ገለጻ ሰጥተውበታል። በጉባኤው የኃይማኖት አባቶች፣የተለያዩ ክልሎች ባ/ቱ/ቢሮ ተወካዮች፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዪችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሞያች ተሳትፈውበታል።

የግዕዝ ጉባኤው ቋንቋውን መልሶ እንዲያንሰራራ ለቀጣይ ምን መደረግ አለብት በሚል አቅጣጫ አስቀምጦ የተጠናቀቀ ሲሆን በመድረኩም ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። ጥናታዊ ጽሑፎቹ በዶ/ር አሰፋ ባልቻ preservation of indigenous Ethiopian medical manuscripts በሚል ርዕስ ከወሎ ዮኒቨርሲቲና አቶ ሃጎስ አብርሃ ፀበልና ማየ ፀሎት በግዕዝ ባህል ወፊዚክስ በሚል ርዕስ ከመቐለ ዮኒቨርሲቲ አቅርበዋል። በመጨረሻም የአራተኛውን የወልቂጤ ጉባኤ ሪፓርት በዶ/ር ትግሉ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ቀርቦ አድምጧል። በቀጣይ ግዕዝ በተቋምና በፖሊሲ እንዲደገፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ፣ ግዕዝን በስፋት ማስተማር እንደሚገባ፣ በግዕዝ የተጻፉትን ተተርጉመው ለተመራማሪውና ለተጠቃሚው ማቅረብ እንደሚገባ ዩኒቨርሲቲዎች የጀመሩትን የግዕዝ ትምህርት ክፍል ማጠናከር እንደሚገባ በማስቀመጥ ተጠናቋል።