News News

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ በደብረ ብርሃን ከተማ ታህሳስ 16 እና 17 /2012 ዓ.ም. የንባብ ሳምንት ማዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡
በዝግጅቱም፡-
 ለከተማው ትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት መመስረት አስፈላጊነት ላይ በታዋቂ ደራሲያንና የሥነ ጽሁፍ ባለሙያዎች ምክርና ግንዛቤ ይሰጣል፣ የንባብ ክበባት ይመሰረታሉ፣ የመጽሐፍት ልገሳ ይደረጋል፡፡

 የሥነ-ጽሑፍ ምሽት ለከተማ ነዋሪዎችና ወጣቶች ይካሄዳል፡- በታዋቂ ደራሲያን፣አርቲስቶችና የሥነ ጽሁፍ ባለሙያዎች ምክርና ግንዛቤ ይሰጥበታል፤ አነቃቂ ንግግሮች፣ግጥም፣ መነባንብ፣ ጭውውት እና ሌሎችም የኪነ ጥበባት ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡ ወጣቶች ክህሎታቸውን ያቀርባሉ፣ በኤጀንሲው ይሸለማሉ፤ ይበረታታሉ፡፡

 በደብረ ብርሃን ማረሚያ ቤት የንባብ ሳምንት ይካሄዳል፤ በታዋቂ ደራሲያንና የሥነ ጽሁፍ ባለሙያዎች ስለ ንባብ ጠቀሜታ ምክርና ግንዛቤ ይሰጣል፤ ለማረሚያ ቤቱ የመጽሐፍት ልገሳ ይደረጋል፡፡
በመሆኑም ይህንን ታላቅ ዝግጅት የሚድያ አካላት ቅድመ መረጃውን ለአድማጭ ተመልካች እንዲያስተላልፉ ተጠቁሟ ፣ ጥሪ የተደረገላችሁ ተሳታፊዎች፣ የሚድያ አካላትና የከተማው ነዋሪዎች በፕሮግራሙ ላይ እንድትገኙ ግባዣችንን እናቀርባለን በማለት የኤጀንሲው የህዝብ አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታዩ አስታውቀዋል፡፡


ኤጀንሲው የአሰልጣኞች ስልጠና ሲከታተሉ ለቆዩ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት በመስጠት አስመረቀ።

ኤጀንሲያችን በሪከርድ ስራ አመራር ለ15 ቀናት የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት በዛሬው ዕለት አስመርቋል። ስልጠናውን የወሰዱት 18 ባለሙያዎች ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተውጣጡ እንደሆነ ከክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

እነዚህ ሰልጣኞች በየቢሮው የሚታየውን የሪከርድ እና የመዛግብት አያያዝ ችግሮችን ለመፍታት ለባለሙያዎች አጫጭር ስልጠናዎችን መስጠት የሚያስችላቸውን እውቀት እንዳገኙ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ሰልጣኞቹ በስልጠና በቆይታቸው የታዘቡትን አስተያየት ሰጥተዋል።

የስልጠና ክፍሉ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መኮንን ከፋለ አስተያየታቸውን ተቀብለው ወደፊት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ጥሩ ግብዓት መሆኑን በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ገልጸዋል። በመጨረሻም ከኤጀንሲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ከአቶ ሽመልስ ታዩ እጅ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል።


ኤጀንሲው አማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ልማት ቢሮ እና ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከኀዳር 12 – 16 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት በውቢቷ ባህርዳር ከተማ « ህዳር ሲታጠን፤ መጽሐፍ ሲተነተን» በሚል መሪ ቃል የንባብ ሳምንት ዐውደ-ርዕይ፣የመጽሐፍ ሽያጭ ፣ የኪነ-ጥበባት መድረክ በደመቀ ሁኔታ አካሄደ፡፡ የዝግጅቱ ጅማሮ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ በፔዳ ጊቢ ኦዲሪየም አዳራሽ ሲሆን በዝግጅቱም በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የውጭ ሀገር ዜጎች ተገኝተዋል፡፡

ዝግጅቱን የከፈቱት የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ኘሬዝዳንት ተወካይና የኮሙዩኒኬሽን ክፍል ተወካይ አቶ ታደሰ አክሎክ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎቹ ያሉ ወቅታዊ ሁኔታ እንደዚህ ዓይነት ሁነቶች ለማዘጋጀት ቢከብድም ነገር ግን ያላቸው ፋይዳ ትልቅ በመሆኑ መካሄዱ ጥሩ እንደሆነና ወደፊት ከዩኒቨርስቲዎችና ከወጣት ማህበሩ ጋር እንደሚያዘጋጁም ተናግረዋል፡፡

የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዩች ኃላፊ አቶ ሽመልስ ታዩ የቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አመሠራረትንና ለዚህም ጅማሮ የአፄ ኃይለሥላሴ ሚና የኀላ መሆኑንና ለሀገራዊ ተልዕኮ ያለውን ጠቀሜታ ገልፀው፡፡ አሁን እየተሠራበት ያለው ሂደት ከ2ዐዐ6 ዓ.ም ጀምሮ እንደሆነና ኤጀንሲው በየክልሎቹ ባዘጋጀቸው ከዓመት ዓመት የተሻለ በማድረግ ለውጥ እየታየ እንደመጣም ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም በሀገራችን ብሎም በየክልሉ የሚገኙ ቅርሶችን ለማሰባሰብና ለማደራጀት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡

በዕለቱም ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ በዶ/ር ማረው አለሙ በጥልቀት ማንበብና በጥልቀት ማሰብ በሚል ርዕስ ጽሑፍ ሲቀርብ በደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል ከመጽሐፍ በተገኘና ከሕይወት ተሞክሯቸው ያገኙትን ገጠመኝ ሲያካፍሉ በዚሁ መድረክ ከሂዩማኒትስ ፋክሊቲ /ፎክሎር የባህል ጥናት/ ትምህርት ክፍል በመምህር ተመስገን በየነየዝግጅቱ መሪ ቃል በሆነው “ኀዳር ሲታጠን፤ መጽሐፍ ሲተነተን” በሚል ርዕስ ሰፋ ያለ ሃሳብ የያዘ ጥናታዊ ጽሑፍ ፣  በጋዜጠኛና ደራሲ ሄኖክ ስዩም ንባብን አስመልክቶ የሚገኙ ጥቅሞችን ገዳማትን መስኪዶችን በምንጐበኝበት ጊዜ ማንበብና ያለማንበባችንን በጥልቀት የምንፈትሽበት እንደሆነና ባለማንበብ የመጡ ችግሮችን በምሳሌ እያጣቀሱ የህይወት ተሞክሮውን ለተሳታፊው አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም ከተሳታፊዎቹ መጻሕፍቶቻችን ርዕሶቻቸው ቆንጆ ሆኖ ውስጣቸው ባዶ ነው የሚያስተምም አይደሉም? በየገዳማቱ ያሉ መጻሕፍቶች አይነበቡም ለማንበብም አይስቡም? ጉንጉን የወዲያነሽ በፊት ለመከላከያው ሠራዊት እንዲያነ እየተገዛ ይሰጥ ነበር አሁን ይሄ እየተደረገ ነው ወይ? ምንስ ያህል ሥራ እየተሠራ ነው? አሁን ባለው ሁኔታ ምን እየሠራህ ነው መጽሐፍ እየፃፍክ ነው ወይስ አቁመሃል? የቀረቡት ርዕሶች ጥሩ ናቸው በሀገራችን የማንበብ ፍላጐት ያላቸው 49% ነው ተብሏል ይሄ ቢጣራ 39% አይሆንም? ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል በሚል ሞቶ ተይዞ ሚድያ ይሠራል ነገር ግን ያደርጋል ወይ? የያዘው መልዕክት ቢስተካከል የንባብ ኢንዱስትሪው አድጎ ማየት እንደሚፈለግ ወረርሽኙን በጤናአዳም፣ በነጭ ሽንኩርት፣ በአረቄ አባረርነው ንባቡንስ በምን እናዳብረው የሚሉ ጥያቄዎች እና ሃሳብ አስተያየቶች ቀርበው አራቱም አካላት በጥልቀት ምላሽ በመሐስጠት ተጠናቋል፡፡

መሪ ቃሉ የያዘ ቲሸርት በመልበስና መሪ ቃሉንና ሌሎች መልዕክቶችን በመያዝ ህፃናት ተማሪዎች ከኋላ በመሆንና የክልሉ የማርሽ ባንድ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ በመጀመር መሀል ከተማውን የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን በማሰማት የመጽሐፍት ዐውደ ትዕይንቱ ሽያጭ መርኃ ግብሩ በተዘጋጀበት በግዮን ሆቴል አጠገብ ጣና ዳር በመጓዝ የተለያዩ ጣዕመ ዜማን በማሰማት የበዓሉ ድምቀት ሆነዋል፡፡

በመቀጠልም የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታዩ የዝግጅቱን ዓላማ መድረኩ የመጽሐፍት ዐውደ-ርዕይ በማዘጋጀት ለመጻሕፍት የገበያ ትስስር መፍጠር እና ለደራሲያንና በዘርፉ ለሚገኙ ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ የሚፈጥር እንደሆነ ሲናገሩ በባህርዳር ዩኒቨርስቲ የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሙዩኒኬሽን ም/ኘሬዚዳንት ዶ/ር ዘውዱ ዕምሩ መሪ ቃሉን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ትንታኔ በመስጠት ግንዛቤ ካስጨበጡ በኋላ ስናነብ ሰው እንሆናለን ባለማንበባችን መረጃን እያዛባን እንገኛለንና በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ላይ የምናያቸው ችግሮች ሁሉ ከዚያ የመጣ እና ያለማንበብ የወለደው ችግር እንደሆነም ተናግረው ቀጥለውም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ መላኩ አላምረውም የሁለቱን ተናጋሪ ንግግር በማጣቀስና ዓላማችንን እየረበሹት ያለው የትርት መዛባት ነው ለዚህ ደግሞ መፍትሔው እንደነዚህ ዓይነት የንባብ ሳምንቶችን በተሻለ መልኩ አጠናክሮ በማጋጀት ትውልዱ መለወጥ እንደሚገባ እና ከዚህ በፊት በመጽሐፍት አዟሪነት የሚያውቋቸው በአሁኑ ወቅት ወደመጽሐፍት መደብር ባለቤትነት የተቀየሩ የመጽሐፍት መደብር ቤቶችን ጥንካሬያቸውን አድንቀው ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ዘርፉን በመደገፍ ወጣቱን መቀየር እንደሚገባም አሳስበው የማርሽ ባንዱ የመጨረሻ ጣዕመ ዜማ እያሰሙ የመጽሐፍት ዐውደ-ርዕይ ትዕይንት ሽያጩ በሶስቱ አዘጋጆች የበላይ አመራሮች ሪቫን በመቁረጥ ዝግጅቱ በይፉ ተከፍቷል፡፡

በዕለቱም በሙሉዓለም አዳራሽ በሕፃናት ተማሪዎች ግጥም፣ጥያቄና መልስ ውድድር ከእውቀት ፋና ሙሉ ሳይክል፣ ከድልችቦ የመጀመሪያ ሙሉ ሳይክል፣ ከሽንብጥ ሙሉ ሳይክል፣ ከአፄ ሰርፀ ድንግል ት/ቤት፣ ከየካቲት 23 ሙሉ ሳይክል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ከመስከረም 16 ሙሉ ሳይክል 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተካሂዶ ከአንደኛ እስከ አራተኛና በተመሳሳይ ውጤት ደብል ወይም አምስተኛ ለወጡት ተማሪዎች ከደራሲ ኃይለመለኮት እጅ መጽኀፍ ተበርክቶላቸዋል፡፡

በቀን 14/3/12 ዓ.ም በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ልማት ቢሮ አዳራሽ በህጻናት የንባብ መዝሙር ዝማሬ ተሰምቶ የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳ/ዳይሬክተር አቶ ኃይለየሱስ በዕለቱ የባህርዳር ወጣቶች ሕፃናት የማንበብን ጥቅም ማንበብ ትልቅ ሰውና ሙሉ ሰው እንደሚያደርግ ተረድታችሁ ታዳጊ ወጣቶችንና ሕፃናትን ወደስፍራው ያመጡ ወላጆች አመስግነው፡፡

በመቀጠልም በወላጆች በወ/ሮ ኤልሳ “የሰፈር ልጆች” በወ/ሮ ላይላ መሀመድ “ተመራማሪዎቹ የዱር እንስሳት” የሚሉ ተረቶች  ቀርቧል፡፡

በወላጆች ለሀገራቸው በርካታ ልብወለድ መጽሐፍ ያበቡ ደራሲያን በጥያቄና መልስ ውድድር በባህርዳር የዓመቱ ምርጥ እና አንደኛ በመውጣት አቶ ፍትሕ አምላክ እና ቤተሰቦቹ ሁለተኛና ሶስተኛ የወጡ ወላጆች ረዥም ልብወለድ መጽሐፍ ሲበረከትላቸው የደራሲ ከበደ ሚካኤል ፅጌረዳ የሚለውን ግጥም ተሳተፉ ሕፃ መካከል በቃሏ ላነበነበች ህጻን የደራሲ አዲስ ዓለማየሁ ፍቅር እስከመቃብር መጽሐፍ ተበርክቶላታል፡፡

የአስኳላ ልብወለድ ፀሐፊ የአብነት /ቤቱን እንድናይ ያደረጉት ደራሲ ሕይወት ተፈራ የሕይወት ተሞክሮና ከመጽሐፍ ገጠመኝ ባቀረቡበት ወቅት ማንበብ ስለሚያመጣው ዕውቀት እና ተረቶችን የሚያነቡ ልጆች ስለችግር አፈታትና የእርስ በእርስ ግንኙነትን በሚፃፉ ጽሑፎች በጐነትን በትውልድ መካከል ያለውን የእርስ በእርስ ግንኙነትን እንደሚያዳብርም ተናግረዋል፡፡

አቶ ምስጋናው ፋንታ በልጁ ተጋብዞ “ዳንሰኞቹ ዋልያዎች”  በሚል ርዕስ ተረት ተነቦ ከስድስት 1ኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለተውጣጡ ስድስት የጥያቄና መልስ ተወዳዳሪዎች በዕለቱ በወላጆች ከተነበቡት ሶስት የተረት መጻሕፍቶች ለእያንዳንዱ የሕፃናት ተወዳዳሪ ሁለት ሁለት ጥያቄዎች ተዘጋጅቶላቸው በመለሱት ጥያቄ ልክ ደረጃ በመስጠት ደራሲ ጌትነት አንተነህ እጅ አማርኛ እንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት መጽሐፍ ለሁሉም ተሳታፊዎች ተበርክቶላቸዋል

በመጨረሻም በደራሲ መሠረት አበጀ በዕለቱ ተረት ላቀረቡ ሶስት ወላጆች ልብወለድ መጻሕፍትን በመሸለምና የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታዮ መጻሕፍትን እናንተንም ልጆቻችሁም ያንብቡ የንባብ ክበባት በት/ቤት እንዲደራጅና በስፋት እንዲሠራ በማሳሰብ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

በአርቲትስ ታምሩ ብርሃኑ የውሃን ጠብታ ደጋግሞ በማለት በበገና በማጀብ የኘሮግራሙ ማነቃቂያ በመሆን ጅማሮውን ያደረገ ሲሆን በመቀጠልም በበገና የታጀበ የያሬድ መንፈሳዊ ት/ቤት ጊዜውን የዋጀ ተነሽ ኢትዮጵያ የሚል መዝሙር ቀርቧል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ዝግጅቱን አስመልክቶ የዝግጅቱን ስም የንባብ ሳምንት እንደሚባል ጀምረው በውስጡም የሚተገበሩ ተግባራትን ከተናገሩ በኋላ ሕፃናት ወጣቶች ካነበባችሁ ተቋማችን የተቋቋመው የክልሎችን የንባብ ባህል እንዲዳብር በየክልሎች እንዲህ ዓይነት ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ወደሚፈልጉት የሙያ ዘርፍ እንዲበቁ የንባብ ባህል ማዳበር እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ገጣሚዎች ወቅቱን አስመልክቶ መልዕክት የሚያስተላልፍ ግጥሞች ሲቀርቡ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕልም የህይወት ተሞክሮውን እና የዘመኑ ወጣቶች ሀገራችሁን እንደ ዋርካ ጥላ ሆናችሁ ልትጠብቋት ይገባል ብሏል አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮንም ለወጣቱ መልዕክት ሲያስተላልፍ ሰው ራሱን ፈልጐ ማግኘት እንዳለበት በተለያዩ ምሳሌዎች በማዋዛት መልዕክት አስተላልፏል፡፡

አርቲስት ታምሩም ታዳሚውን ሶስት ጊዜ በማስጨብጨብ ንባብን ባህል በማድረግ ልታነቡ ይገባል በማለት ቃል አስገብተዋል፡፡የባህር ዳር ከተማ የሥነ-ጽሑፍ ክበብ አባላት በመላኩ ባዬ ሽለላ ቀርቦ ታዳሚውን ሲያዝናና ንባብ የወለደችው ሊኢቃን በደራሲ ገለፃ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ዘመናዊ ትምህርት በሌለበት ወቅት ራሳቸውን ያበቁ ደራሲዎችን የህይወት ተሞክሮ እና ንባብን በተመለከተ የንባብ ስልት ትችት የጠያቂነት ባህ እንደሚያስፈልግ በደራሲ መሠረት አበጀ ሰፋ ያለ ገለፃ በመስጠት ለታዳሚው ቀርቧል፡፡ እርካብ የቲያትርና የሥነ-ጽሑፍ ማህበር ኘሮዚዳንት “ምንድነሽ አንቺ ሰው” በሚል የግጥም ርዕስ የተዘጋጀ ግጥም በገጣሚ ሲቀርብ በገጣሚ ሕይወት “ፍቅር”  “ፈራጅ” እና “መሸ” በሚሉ ርዕሶች በሁለት ስንኝ የተዋቀሩ ግጥሞች ቀርበዋል፡፡

ተርጓሚና ደራሲ ጌትነት አንተነህ ስራቸውንና የህይወት ተሞክሮ እና የትርጉም ሥራ እንደ ሀገር ብዙ ውጣ ውረድ በአሳታሚዎች ችግር አንዳለ ለሕዝቡ፣ ለሀገር ለወጣቱ የሚጠቅሙ ቋንቋውን ባህሉን ተመልክቶ የሚተረጐሙ ቢሆኑ የሚሉ ሃሳቦችን አስተላልፈዋል፡፡ ጋዜጠኛና ደራሲ ሄኖክ ስዩም የንባብን ጥቅም እና የክልል ከተሞች ወጣቶች የተሻለ የማንበቢያ ስፍራ እና ይህን ተግባር ለማስቀጠል ኤጀንሲውን መጠበቅ እንደማይገባቸው መልዕክት አስተላልፏል፡፡ ሊቀዊ በላይ መኮንን “ንባብና ሥነ-ጽሑፍ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ጽሑፍ ቢኖራቸውም ከዛ ውስጥ የንባብን ትርጉም ከንባብ ስልት ጋር በማዋዛት እና ዩኒቨርስቲዎቻችን የተመረ ምሁሮች ሀገራቸውን ይጠብቃሉ የሚባሉት ድንጋይ የሚወረውሩ ዜጐች እተፈጠሩ ያሉባት ወጣት እየፈራ እንደሆነና ወጣቱ ራሱንና ሀገሩን ሊታደግ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም በዕለቱ ግጥም ላቀረቡ ገጣሚዎችና ፉከራና ሽለላ ላቀረቡ ወጣት ለያሬድ መንፈሳዊ ወጣቶች፣ ከመድረኩ የተዘጋጀ ጥያቄ የመለሱ እና ሁለት መንትያ ወጣቶች እና ለዋልታ ቴሌቪዥን ከኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር እጅ መጽሐፍ ተበርክቶ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

በዝግጅቱ ማጠቃለያ ቀን 16/ዐ3/2ዐ12 ዓ.ም በጠዋቱ መርሀ ግብር በፖፒረስ ሆቴል በመጀመሪያ በድጅታል ላይብረሪዎች ላይ ጠቅለል ያለ ገለፃ በአቶ ጌታቸው ቀርቦ በመቀጠልም የጐንደር ዩኒቨርስቲን፣የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ካምፖስን፣ የቴክኖሎጂና ኢኖቪየሽን ኢንስቲትዩት እንዲሁም የኤጀንሲውን የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍትና የህትመት ዝግጅት ደረጃን አስመልክቶ ተሞክሯቸውን በተወከሉ ባለሙያዎች ለተሳታፊዎች አቅርበው ከዚያም የመዛግብትና የጽሑፍ ቅርሶች ለጥናትና ምርምር ያላቸው ፋይዳ በሚል ርዕስ ኤጀንሲው የስልጠና ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ባለሙያ በአቶ ግርማ አበበ ሲቀርብ፤ የአብያተ መዛግብት መቋቋም ታሪካዊ አሻራዎችን የማስቀጠል ሚና በሚል ርዕስ የመነሻ ጽሑፍ በጽሑፍ ቅርስና የመዛግብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ገረመው ከበደ ቀርቧል፡፡ በቀረቡት የመነሻ ጽሑፎችም ላይ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል፡፡

ከተነሱት ሃሳብና አስተያየቶች መካከል በጥቂቱ፡-የድጂታል ላይብረሪ የተለያዩ ዓይነት ዘዴን በመጠቀም በዩኒቨርስቲ፣ በተቋም ይከፈታሉ ነገር ግን ንዳኢንሳ ሁሉ አንድ ባደረ ቢጠቀሙ፣ኮፒራይት ላይ ገደብ ሊበጅለት እንደሚገባ፣ ከተሞችን በላይብረሪ መስየማድረግ ነገር በጥልቀት ቢሠራ እንደባህርዳር ከተማ ግን ጅምሩ ጥሩ ነው እየተሠራ ነው፣በከተማው ላይ የሕዝብ ቤተመጻሕፍት ቢኖሩ የድራፍት ቤቶች እየሰ ከሚሄ እንደባህርዳር አምስት ሺህ የድራፍት ቤቶች እንደሚኖሩ ተናግረው የድራፍት ቤቶች አይኑሩ ሳይሆን ወጣቱን ንባቢ ሊያርቁ ስለሚችሉ፣በየክልሎች በርካታ ቅርሶች አሉ ነገር ግን በሚፈለገው ልክ እየተሰበሰበ አይደለም? ከየገዳማቱ የሚሰበሰቡ በርካታ ቅርሶች/ዶክመንቶች አሉ እነዛ ግን ዶክመንት እየተደረጉ አይደለም? ከቤተክርስቲያኖች ጋር በመቀናጀት ኘሮጀክት ሰርቶ ዶክመንቶችን መሰብሰብ ቢቻል? በብዛት ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ እየሠራ ያለው ስልጠና ብቻ እንጂ ቅርሶችን መሰብሰብ ሥራ ሠራ አይታይም? መዛግብትና ቤተመጻሕፍት ላይ ሌሎች ሀገራቶች በጥልቀት ይሠራ ንደኛ ግን የሚፈለግም እንዳልሆነም ተገልጿል? አዲስአበባና ድሬዳዋ ላይ ብሔራዊ መዛግብት እንዳልተሰበሰበ በጽሑፍ ላይ ቀርቧል መሰብሰብ ለምን አልተቻለም ኃላፊነቱ የኤጀንሲው ስለሆነ? የክልሉ ባህልና ቱሪዝም መዛግብትን ጊዜው ያለፈ መረጃ እያለ ሲያቃጥል ይስተዋላል እንደ እናንተ እንዴት እየሠራችሁ ነው እናንተም ትኩረት ሰጥታችሁ እየሠራችሁ አይደለም? በተደጋጋሚ ከተሳታፊው የተነሱ ስልጠና ከመስጠት ወጪ ምንም እየሠራችሁ አይደለም?በኤጀንሲው ያለ ህግ ማዕቀፍ አዋጅ በቂ ነው ወይ? ሊከለስ አይገባም ወይ? ዲጅታል ቤተመጻሕፍቶች በአንድነት እንደ ሀገር መሠራት አለባቸው የሚሉ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡

በዛው እለትም በወተር ፎሮንት ሆቴል አዳራሽ የንባብ ክበባት ምስረታ በትምህርት ቤቶች በሚል ርዕስ የፖናል ውይይት ተካሂዶ

በዕለቱ የደራሲያን ተሞክሮና የሶስት አንደ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች ሲያካፍሉ በተጨማሪም የንባብ ክበባት ችግሮችና መፍትሔያቸው በቀረቡ ጽሑፎች ቀርበው ተሳታፊዎች ሲወያዩበት የተነሱ ችግሮችን በጥቂቱ በት/ቤቶች የመጻሕፍት እጥረትና የማንበቢያ ቦታ ምቹ ሁኔታ አለመፈጠር፣ የተማሪዎች የንባብ ፍላጐት ማነስ፣ የክበባት መብዛት ከጥራት ይልቅ ሪፖርት ላይ የማተኮር የመሳሰሉት ሃሳቦች ተነስተውና የመፍትሔ ሃሳቦች በመስጠትና በየትምህርት ቤቱ ለሚመሠረቱ የንባብ ክበባት ለቤተመጻሕፍቶች በቁጥር 3238 /ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት መጽሐፍ ከኤጀንሲው ተበርክቶ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

በማጠቃለያው በባህርዳር ማረሚያ ቤት በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ የመክፈቻ ንግግር ከተደረገ በኋላ በደራሲ ሕይወት እና በደራሲ ኃይለመለኮት የህይወት ተሞክሮ ሲቀርብ በዕለቱ በተጋበዙ አንጋፋና ጀማሪ ደራሲያን ንባብን በተመለከተ ስላለው ጥቅምና ታራሚዎቹ ለማንበብ አሁንም እንዳልረፈደባቸው የመምከር እና ልምድ የማካፈል ሥራ ተሠርቷል፡፡

በዕለቱ መድረኩን የመራው አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ ታራሚውን የሚመጥኑ ወቅታዊ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የማበረታቻ የመጽሐፍ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ለማረሚያ ቤቱም ለመማሪያነትና ለዕውቀት የሚረዱ መጽሐፎቶችን እና ደራሲ ህይወት ሁለት የተለያዩ ይዘት ያላቸው አሥራ አምስት መጻሕፍትና ደራሲ ጌታነህ በእጁ ይዞት የነበረውን አንድ የራሱን መጽሐፍ በጥቅሉ ከስድስት መቶ በላይ መጽሐፍት አቶ ይኩኖአምላክ ለማረሚያ ቤቱ ኃላፊ አበርክተዋል፡፡ በመጨረሻም ለማረሚያ ቤቱ የምስጋና የምስክር ወረቀት  ተበርክቶ ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡


እንሰት እምነት ውበት የጋሞ ዕሳቤዎች ቅኝት!” በሚል ርዕስ 27/01/2012 ዓ.ም ህዝበ ገለፃ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ተካሄደ፡፡

ህዝበ ገለፃውን ያቀረቡት ዶክተር ታደሰ ወልዴ ከoxfored university የስነ-ሰዕብ አስተማሪ ሲሆኑ በንግግራቸው እንዳሉት እንሰት በአፍሪካ ብሎም በኢትዮጵያ ሁሉም ክፍሎች ይመገቡት የነበረና በኢትዮጵያ በጓሮ አካባቢና ከጓሮ ውጭ የሚተከል ለምግብነት የሚጠቀሙበት ተክልሲሆን እንሰት  በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በተለይም በጋሞ ብሔረሰብ ዘንድ ከምግብነት ባለፈ ህብረተሰቡ የአኗኗር፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው የማህበረሰ አስተሳሰብና ወግ ትስስርና መስተጋብር መገለጫ፣ ውበት፣ እምነትና እንደሰው ትውልድ በቤት ዙሪያ የሚተከል፣ በማህበረሰቡ የቤተሰቡ የሥራ ድርሻ ተዘርዝሮ ሥራ የሚከናወንበት ፋይዳው ብዙ የሆነ ተክል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ያለ እንሰት ምን ቤት አለ  ያሉን ንግግር አቅራቢው እንሰት ከተክልነት ባለፈ የመሬትን ለምነት የሚጠበቅ፣ የአካባቢን መራቆት የሚከላከል፣ ተፈጥሮ ሚዛን እንድትጠብቅ የሚረዳ ለቤት መስሪያና ለምግብነት የሚያገለግል፣ የብሔረሰቡን የሽምግልና ስርዓት የሚያሳይ፣ ድንቅ የሆነ ተክል ነው፡፡

የጋሞ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ታሪክ ባህል ወግ፣ ቋንቋና የድንቅ ባህል ባለቤት ሲሆን የራሱ የሆነ ሀገር በቀል እውቀት ማለትም የቤት አሰራር፣ አስተራረስ እርቅ የመሬት አጠቃቀም ያለው ሲሆን ከእንሰት መድሃኒት፣ ጌጥ፣ ምግብ፣ ምንጣፍ የመሳሰሉትን የቤትና ከቤት ውጭ ቁሳቁሶችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከእንሰት ጋር የተቆራኘ ህዝብ ነው ብለዋል፡፡

ክለውም ይህን ድንቅ የሆነ ተክል ከዚህ የበለጠ ጥቅም እንዲሰጥ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መደገፉ እንዳለበት አበክረው ተናግረዋል፡፡

በዕለቱም ከተሳታፊዎች የማህበረሰቡ ሀገር በቀል እውቀ በመጠቀም አሁን አሁን እየገጠሙን ላሉ ችግሮች እንደሚችሉ እንዲያገለግል መሥራት እንዳለበት ሲገለጽ  ሌላው በርካተ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ከመድረኩ ማብራሪያዎችና ገለጻዎች በስጠት ታዳሚዎች ግንዛቤ እንዲጨብጡ  ተደርጓል፡፡

በዕለቱ በዝግጅቱ የታደሙ ታዳሚዎች እንዲህ ዓይነት ዝግጅቶችና ውይይቶች በስፋት መቅረብ እንዳለባቸውና ሀገር በቀል እውቀት፣ ልምድ፣ ታሪክና ባህል ላይ ኤጀንሲውም ሆነ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመፍታት እንደሚያስችልና መግባባት ለመፍጠር አይነተኛ መፍትሔ መሆኑን በአፅኖት ተናግረዋል፡፡


የንባብ ክበባት!!!!

በትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት ምስረታ አውደ ምክክር በባህርዳር ከተማ ዋተር ፍሮንት ሆቴል እየትካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ ከአራት አመታት በፊት በከተማው ላቋቋማቸው
አስር የትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት ብቻ በድምሩ 3238 መጽሀፍት በስጦታ አበርክቷል።


News Archive News Archive

Back

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን/ማርች 8/ተከበረ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተመጻህፍትና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ ሰራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን/ ማርች 8/ ረቡዕ መጋቢት 11/2011 ዓ.ም በኤጀንሲው አዳራሽ አከበረ፡፡በዓሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ108ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ43 ጊዜ“ የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡

በዕለቱም በሴቶችና ህፃናት ወጣቶች ሚኒስቴር የግንዛቤና ንቅናቄ ማስፋፊያ ባለሙያ በወ/ሪት ሩሃማ እንግዳ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ታሪካዊ አመጣጡን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሑፍ ቀርቦ ታዳሚዎች ጥያቄና አስተያየት እንዲያነሱ ተደርጓል፡፡

የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቡድን መሪ እና የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ድረስ አልይ የሴቶች የመብት እንቅስቃሴ ታሪካዊ ዳራው በኢትዮጵያ አስመልክቶ በሴቶች ላይ ይደርስ የነበረው ጭቆና ለማስወገድ የተደረገው ሁለንታናዊ የትግል እንቅስቃሴና ውጤት ለመዘከር ሴቶች ከነበራቸው ጭቆና ተላቀው በኢኮኖሚዊ߹ በማህበራዊና በፖሊቲካዊ ተጠቃሚ የሚሆኑበትንና የፆታ እኩልነት የሰፈነበት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እንደሆነ ተናግረው አክለውም የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ትግል እንቅስቃሴ በንጉሱ፣ በደርግ እና በዘመነ ኢህአዲግ ዘርፈ ብዙ ኩነቶች እንደተመዘገቡም በዝርዝር ሲገልፁ የሴቶች ጉዳይ በዘመነ ኢሕአዴግ ስንመለከት ደግሞ (የሽግግር መንግስት ጀምሮ 1983 እስከ አሁን ድረስ መንግስት ሴቶች በፖለቲካው በማህበራዊና በኢኮሚያዊ እንዲሁም በስርዓተ ፍትህ እኩልነት በህግ በአደረጃጀትና በመዋቅራዊ ለውጥ የተለያዩ ማሻሻያ እየተደረገለት አሁን ያለበት ደረጃ መድረስ የቻለ በመሳሰሉት ጉዳዮች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችንና ስራዎችን ማከናወን ችሏል አስከነ ችግሩም ቢሆን በማለት ገልፀዋል፡፡

አንዳንድ ተሳታፊዎችም እንደሀገር አደረጃጀቱ ችግር ያለበትና የሴቷን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ይልቅ የሚገታት ሆኖ እየታየ እንዳለ የተለያዩ መረጃዎችን በማጣቀስ ሀሳብ ሰጥተው አሁን እንኳን ፕሮግራሙ የሌላ ተግባር ቢሆን በርካታ ታዳሚዎች እንደሚኖሩትና አዳራሹ እንኳን እንደማይበቃ ገልፀው ለሪፖርት ግብአትነት ካልሆነ በስተቀር ፋይዳው እምብዛም እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን ሁሉም አካል የሴቷ ጉዳይ የእኔም ነው፡፡ ይመለከተኛል ተብሎ ከተሰራ እንደወንዱ ሁሉ በተሰማሩበት የሙያ መስክ ለሀገር ባለውለታ የሚሆኑ በርካታ ሴቶች ወጥተው የሚታዩበት ሁኔታም ከአሁኑ በተሻለ እንደሚፈጠርም ተገልጿል፡፡