News News

መስከረም 6/2012 ዓ.ም. የተጀመረው የቤተመጻሕፍት ሙያ ስልጠና ተጠናቆ መስከረም 30/2012 ዓ.ም. የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል፡፡ ኤጀንሲው ለሰልጣኞቹ ደረጃውን የሚመጥን ማስረጃ /ሰርተፊኬት አበርክቷል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተካፈሉ ሰልጠኞች በሥልጠናው የመጀመሪያ ደረጃ ክህሎት በማግኘታቸው የተደሰቱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከሌሎች ተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ሐምሌ 1ዐ ቀን 2ዐ11 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ ቢሲና ችግኝ ጣቢያ አካባቢ ችግኝ ተክለዋል፡፡

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ኢትዮጵያ የተለያዩ የደንና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት እንደነበረች እንደሆነች እና እነዚህም በሰው ሰራሽና ተፈጥሮ ክስተቶች እየተመናመኑ መጥተው ከፈተኛ ችግር ውስጥ እንደሆኑ ያመለክታሉ፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ተከታታይ ድርቅና ረሃብ የሙቀት መጨመር፣ የበረሃማነት መስፋፋት፣ የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት፣ የሙቀት መጨመር፣ ምክንያት በሰው ልጅ ሕይወት ላይ የተደቀኑ አደጋዎች ናቸው፡፡

“ከዛሬ 550 ዓመታት በፊት በነዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ ንግሥና በኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ ደንን የማጎልበት ሥራ እንደተጀመረ ቢነገርም፤ ያንን ስልጣኔ ማስቀጠል ተስኖን የዛሬውን ለሰው እና ለእንስሳት ኑሮ የማይመች አካባቢ እንድንይዝ ተገደናል” ያሉት ደግሞ አቶ ግዛት አበበ የጣብያው ከፍተኛ ባለሙ  ናቸው፡፡  ለዚህም አዲስ አለምና መናገሻ ህያው ምስክሮቻችን ናቸው ብለዋል ፡፡ “የችግሮቻችን መብዛት እና ካለፉ ስህተቶቻችን መማር አለመቻላችን ዋጋ አስከፍለውናል” ነው ያሉት፡፡

እንደ ኢትዮጵያ አይነት ሀገር የደን መመናመንና ድርቅ የሚያስከትሉት መዘዝ ትርጉሙ ብዙ ነው!!  ምክንያ/ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ  85% የኢትዮጵያ ሕዝብ መተዳደሪያ ግብርና ሲሆን ወቅቱን የጠበቀ ዝናብና ሚዛኑን የጠበቀ የአየር ንብረት ወሳኝ የግብርና ግብአቶች ናቸው፡፡ ደኖችን መንከባከብ እና መትከል የህልውና ጉዳይና ለነገ የማይባል  የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው፡፡

የኤጀንሲው ሠራተኞች ችግኝ በሚተክሉበት ወቅት እንዴት መትከል እንዳለባቸው ሰፊ መመሪያ የሰጡት አቶ ግዛት ተስፋዬ  እንዳሉት ችግኝ ስንተክል ስሩ እንዳይታጠፍ፣ መትከያ ጉድጓዱ ሲቆፈር ከችግኙ ሶስት እጥፍ እንዲሆን አድርጐ ማዘጋጀት፣ በሚተከልበት ጊዜ ግንድ ከመሬት እኩል መሆኑን ማረጋገጥና የጉድጓዱ ርዝመት ከችግኙ ከበለጠ ውሃ እንዳይዝ ማድረግ፣ ግንዱ ከመሬት እኩል እስኪሆን ድረስ ጉድጓዱን አፈር መሙላት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ችግኙ 9ዐ ዲግሪ ቀጥ ብሎ መቆሙን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ጉድጓዱ ከመሬት ልክ አፈር ካልተሞላ ውሃ ቋጥሮ ችግኙ እንዲደርቅ ስለሚያደርገው በጥንቃቄ አፈር መሙላቱን ማረጋገጥ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

ችግኝ መትከል ብቻውን ግብ አይደለም ግቡ ፀድቀው ዛፍ መሆን ሲችሉና ዛፎች እንዲጨምሩ ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም ገንዘብ፣ ጉልበትና ጊዜ ወጥቶባቸው ካበቃ በኋላ ለውጤት ችግሮችን ለመፍታት  እንዲውሉ ችግኞች ከተተከሉ እና ከመተከላቸው በፊት የግንዛቤ መስጫ ኘሮግራሞች  ተጠናክረው መሰጠት አለባቸው፡፡ እንዲሁም አረንጓዴ አሻራን የማኖር ቀን በሚል በአንድ ጀንበር 2 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በተያዘው ዕቅድም የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞች ገላን አካባቢ አሻራቸውን ያኖሩ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 


የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ በተለያዩ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሐምሌ 19 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ተጎበኘ፡፡ ኤጀንሲውን ከጎበኙ ተማሪዎች መካከል ሶስና የመጀመሪያ ና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በቁጥር ወንድ 40 ሴት 29 በድምሩ 69 ናቸው፡፡ ከጎበኟቸው የስራ ክፍሎች መካከል የኢትዮጵያ ጥናት ክፍል፣ የመዛግብት ንባብ ክፍል እና የፅሁፍ ቅርስ ንባብ ክፍል ሲሆኑ የከፍሉ ሠራተኞች ስለኤጀንሲው ታሪካዊ ዳራ፣ በውስጡ ስላሉ የመዛግብት ስብስብ፣ የጽሁፍ ቅርሶች አያያዝ አጠባበቅና እንክብካቤ በተመለከተ ኤጀንሲው ስለሚሰጠው አገልግሎት የመረጃ አሰባሰብና አደረጃጀት ዘመናዊ ሪከርድ ስራ አመራርና መዛግብት አስተዳደር  በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡

ስለሆነም ተማሪዎች ይህን ተቋም መጎብኘታቸው የፈጠረባቸውን ልዩ ስሜት በመግለፅ ኤጀንሲው ከዚህ የበለጠ እንዲሰራ እና የሀገሪቱን የመረጃ ሀብት እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡ የኢትዮጵያ  ብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ የሃገሪቱ መረጃ መዕከል እንደመሆኑ፣ የስነ-ፅሑፍ ኃብቶች በማሰባሰብ፣ በመጠበቅ በመንከባከብ ለጥናትና ምርምር በማዋል ነገን ዛሬ እየሰራ ያለ አንጋፋና ታሪካዊ ተቋም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመሰረተ ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን የሰሜን አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ተማሪዎች የኤጀንሲውን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡ ተማሪዎችን ለመጎብኘት ካነሳሷቸው ምክንያቶች መካከል የሃገራቸውን ታሪክ ለማወቅ ካላቸው ፍላጎት መኖር፣ የሀገርን ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ  መሰተጋብር ጠንቅቆ በማወቅ በስነ-ምግባር  የታነፀ ለመኾን በማሰብ ሲሆን በተመለከቱት ነገር እንደተደሰቱና ኩራት እንደተሰማቸው  በመግለፅ ኤጀንሲው ላመቻቸላቸው እድል  አመስግነዋል፡፡

በተመሳሳይ ከሚችጋን እስቴት ዪኒቨርሲቲ  በሚሰተር ፕሮቨስት ማርቲን ፊልበርት የተመራ የልዑካን ቡድን ነሐሴ 03 ቀን 2011 ዓ.ም የኤጀንሲውን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ ለእንግዶች ዝርዝር ማብረሪያና ገለፃ ያደረጉት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ በጽህፈት ቤታው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ከተቀበሉ በኋላ  ስለ ኤጀንሲው ታሪካዊ ዳራ፣ ስልጣንና ዝርዝር ተግባራት፣ እንዲሁም ስላለው የኤጀንሲው ነባራዊ   ሁኔታ አካተው አብራርተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ከተካተቱ ዋናዋና የስራ ክፍሎች መካከል የኢትዮጵያ ጥናትና  ህግ ከምችት፣ የመዛግብትና የፅሑፍ ቅርስ ክፍል፣ የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት  ይገኙበታል የየስራ ክፍሎች ባለሙያዎች ስለ ስራ ክፍሎች ዝርዝር ተግባራት  ለጎብኝዎች አስረድተዋል፡፡

በተቋሙ በርካታ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና  ኢኮኖሚዊ ፋይዳ ያላቸው በርካታ የመረጃ ሃብቶች  መኖራቸውን የተናገሩት ማርቲን  ፊልበርት  እነዚህን ሃብቶች በማደራጀት  በመጠበቅና በመንከባከብ እንዲሁም ለጥናትና ምርምር በማዋል  ሃገሪቱ ችግሮችን ለመፍታት ያግዛታል ብለዋል በጉብኝታቸው ወቀት፡፡ ሀገሪቱ ከአፍሪካ የራሷ ፊደል፣ ቋንቋ ባህልና ወግ ያላት ስትሆን የአፍሪካ የነፃነት ፋና ወጊና ቀደምት ስልጣኔ ባለቤት ናት፡፡ ኤጀንሲው ይህን የሚመጥን አደረጃጀት፣ አወቃቀር ቅርፅ ያለው ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት ሊኖር ይገባል ተወዳዳሪ እንዲሆን በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሀብት፣ አደረጃጀት እንዲሁም  ከሌሎች አቻ ተቋማት አብሮ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡


በእርግጥ ትንሽ ትመስላለች በአዋሽ መልካሳ ወጣቶች የተከፈተችው ቤተ መጻሕፍት ነገር ግን ትልቅ ራዕይ የሰነቁ ለያዙት ዓላማም የጨከኑ አንባቢ ወጣቶች ባለትልቅ ተስፋ ነገዋ እጅግ የገዘፈ እንደሆነ እሙን። 2006 የነገው ተስፋ በሚል ስም ተመሰረተች። 20 አባላትን አቅፋ መጻሕፍት ታስነብባለች ወጣቱን እውቀት እየመገበች ስታሳድግ እነሆ ዛሬ 5 ዓመት ሞላት። መስራቾቹ ባለራዕይዎች በቤተሰብ ጥገኝነት የሚኖሩ ተማሪዎች ናቸው።የንባብ ቤቱን ኪራይ ከቤተሰብ በሚያገኟት የሻይ በየወሩ እያዋጡ ይከፍላሉ።የታሪካዊዋን ከተማ ሕዝብ የንባብ ባህል ማሳደግ ዓላማቸው ነውና መጽሐፍትን ለምነው ያሰባስባሉ። ስለንባብ ጠቀሜታ በትምህርት ቤቶችና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሕዝቡን ያስተምራሉ።

ወጣቶቹ ምንም ዓይነት ችግር ካሰቡት ወደኋላ ሊመልሳቸው እንደማይችል ይናገራሉ። "ትውልድ ሳይገነባ ሀገር ገንብተን ተቸግረናል" እናም ትውልዱን መገንባት ግባችን ነው ከሰው በላይ ምንም የለም ይላሉ። እንዲህ ነው ወጣትነት ያስብላል። ነሐሴ 9/2011ዐዓ "ለንባብ እንተጋለን" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተን ቁርጠኝነታቸውን ታዘብን። በንባብና በመጽሐፍት ድርሰት አንቱ የተባሉ አንጋፋ ደራሲያን ልምድና ተሞክሯቸውን እንዲሁም ምክራቸውን ለግሰዋቸዋል። ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲም 797 በላይ መጻሕፍትን 100 000 ብር የሚገመት በመግዛት አበርክቶላቸዋል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ የወጣቶቹን ቁርጠኝነት አድንቀው በምክራቸው አበረታተዋል። የከተማው ከንቲባና አስተዳደርም በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ከጎናቸው እንዲሆንና ጥያቄያቸውንም በአጭርና በረጅም ጊዜ እንዲመልስላቸው አሳስበዋል። የከተማው ከንቲባ አቶ ገነ ጎሌም ወጣቶቹን አመስግነው የንባብ ቦታና ቤት እንደሚያሟሉ ቃል ገብተዋል። እነዚህን ወጣቶች ሁላችንም በርቱ ልንላቸውና እኛም ትውልድን ለመገንባት ድርሻችንን ልንወጣ ይገባል


12ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሀነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው" በሚል መሪ ቃል ሰኞ ጥቅምት 03 ቀን 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ አመራር አባላትና መላው ሰራተኞች የሀገራችንን ብሔራዊ መዝሙር በመዘመርና ሰንደቅ ዓላማችንን በመስቀል ተከብሯል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ሰንደቅ ዓላማችንን ከፖሊስ ሰራዊት አባላት እጅ በክብር ተረክበው እንዲሰቀል በማድረግ ነበር የተከበረው፡፡

News Archive News Archive

Back

የአድዋ ድል በዓል ተከበረ (የካቲት 2011 ዓ.ም.)

ኤጀንሲው 123ኛውን የአድዋ ድል በዓል “አድዋ የሰውነት ማህተም” በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ከየካቲት 16-23 2ዐ11 ዓ.ም በተለያዩ ዝግጅቶች በደመቀ ሁኔታ አከበረ፡፡

ዝግጅቱ በዋናነት ከሰውኛ ኘሮዳክሽን ጋር የተዘጋጀ ሲሆን በተባባሪነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ ከአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ጋር በተባባሪነት የተዘጋጀ ነበር፡፡ በዝግጅቱም ላይ የኤጀንሲው ሠራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ወጣቶች፣ የድርጅት ተወካዮች እና አባት አርበኞች ታድመዋል፡፡

በዝግጅቱም ላይ ዐውደ-ርዕይ፣ የፊልም ፌስቲቫል፣ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የምሽት የዛፍ ሥር ወግ እና የፖናል ውይይት ዋና ዋናዎቹ የኘሮግራሙ አካላት ናቸው፡፡ የአድዋ ድል የጭቁን ጥቁር ሕዝቦችን እንባ ያበሰ፣ የፀረ-ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ትግል ውጤት አፍሪካውያንና ደቡብ አሜሪካውያን ከባርነት ቀንበር እንዲላቀቁ በር የከፈተ ለፍትህ ለነፃነትና ለእኩልነት እንዲሰፍን እንደጧፍ ነደው እንደሰም ቀልጠው ለሀገር ፍቅርና ክብር የተከፈለ ታላቅና ውድ መስዋዕትነት ነው፡፡

አድዋ የነፃነት ቀንዲል የፖን አፍሪካ መመስረት ፋና ወጊ ታሪክን የቀየረ በጨለማ ዓለም የሚኖሩ ሕዝቦች የሰለጠነውን እና በሳይንስ የዳበረውን የአውሮፖ ሀያላን መንግስታት ያንበረከከና የውርደት ካባቸውን ያከናነበ ዓለም አቀፍ የጭቁን ሕዝቦች የድል እና የነፃነት ቀን  ነው፡፡

አድዋ ጀግኖች አባቶቻችን ሊወሩንና ቅኝ ሊገዛ የመጣውን የጣልያን ጦር በአንድነትና በመተባበር በይቻላል መንፈስ ከዳር እስከዳር በሕብረት በመንቀሳቀስ ኋላቀር በሆነ መሳሪያ በመታገዝ ጠላትን ያንበረከኩበት የእናቶቻችንና የአባቶቻችን የነፃነትና የአንድነት ተምሳሌት እና የሕዝብ ድል በዓል ነው፡፡

የአድዋ ድል የሕዝብ ድል ነው፡፡ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች ማለትም ሴቶች፣ ወንዶች፣ ነገስታት፣ አርሶአደር፣ ነጋዴ፣ አዝማሪ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጐችና በአጠቃላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የአፍሪካውያንና የዓለም ጥቁር ሕዝቦች የሉዓላዊነት  በዓል ነው፡፡

የታሪክ መዛግብት እንደሚነግሩን የጦርነቱ ዋና መነሻ ምክንያት የጣልያን መንግስት የቅኝ ግዛት ፍላጎት መኖርና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ በመጣል ሲሆን የወጣው የስምምነት ውል አንቀጽ 17 እንደ ዋና ምክንያት ይጠቀሳል፡፡ የውጫሌ ውል አንቀጽ 17 ሲተረጐም የአማርኛውና የጣልያንኛው ትርጉም ሆን ተብሎ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ሉአላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ስለነበር የጦርነቱ መቀስቀስ እንደ ምክንያት ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ የካቲት 23/1888 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ጦርነቱ በአድዋ የተካሔደ ሲሆን በኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ተጠናቋል፡፡

ከአድዋ ድል በኋላ በርካታ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ውጤቶች የመጡ ሲሆን ከነዚህም መካከል የፖን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መጀመር፣ በርካታ የአውሮፖ መንግስታት በአዲስ አበባ ኤምባሲያቸውን መክፈት መቻላቸው በዘመናዊ የኢትዮጵያ የዲኘሎማሲ ታሪክ እንደመነሻ መቆጠርና ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ የዲኘሎማት መቀመጫ መሆንና መስፋት የመሰረተ ልማት /የመንገድ፣ ባቡርና መገናኛ ዘዴዎች መስፋፋት በአጠቃላይ ወደ ዘመናዊነት መጓዝ መቻል፡፡

በኢትዮጵያኒዝም የሚል የሀይማኖት እንቅስቃሴ መጀመር በአሜሪካ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ መቀንቀንና መስፋፋት፣ የጣልያንና ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ይህም ኢትዮጵያ ፍፁም ነፃና ሉዓላዊት ሀገር መሆኗ መረጋገጥ፣ ሌሎች በወቅቱ የነበሩ የአውሮፖ ሀያላን መንግስታት ቅኝ ግዛትን እንደ መብት የሚቆጥሩ ማለትም እንግሊዝና ፈረንሳይ ይህን ሽንፈት በመመልከት እጃቸውን መሰብሰብ መቻላቸውና ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን የድንበር ውል መዋዋል መቻላቸውና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ማክበራቸው ሌሎች በቅኝ ግዛት የተያዙ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን እንደ ተምሳሌት በመመልከት ከቅኝ ግዛት ነፃ ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመር መቻላቸው ዋና ዋናዎቹ የድሉ ትሩፋቶች ናቸው፡፡

የዝክረ-አድዋ ዋና ዓላማ አባቶቻችን የአንድነት ጽናትና አይበገሬነት ለአሁኑ ትውልድ ማስተማርና ወኔ ማስታጠቅ የሀገር ፍቅርና ሉዓላዊነት ምን ማለት እንደሆነ ማሳየት፣ አባቶቻችን ዘር ሃይማኖት ብሔር ማንነት ሀብትና ብልፅግና ሳይለያያቸው አንድ በመሆንና ሕብረት በመፍጠር እንዴት ሀገርን ከጠላትና ከወራሪ መታደግና ነፃነትን በመጐናፀፍ አንገትን ቀና አድርጐ መጓዝ እንደሚቻል የሚያስተምር ደማቅ የታሪክ አሻራ እና ህያው ምስክር ነው፡፡

በዝግጅቱ በርካታ ኘሮግራሞች የተካሄዱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዐወደ-ርዕይ፣ ፊልም ፌስቲቫል፣ ጥናታዊ ፅሐፍ ፣ የሙዚቃ ዝግጅት እና የአባቶች የዛፍ ሥር የምሽት ወግ ፣ የእግር ጉዞ እና የግብር ማብላት ፕሮግራም ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የዛፍ ስር የምሽት ፕሮግራም የተካሄደበት ዋናው አላማ አባቶቻችን እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን ሀገርን ሊወር የመጣውን  ጠላት ለመመከት ዛፍ ስር ቁጭ በለው በመምከር በመወያት እና ለመደማመጥ ያላቸውን ልዩነት በመተው አንድ በመሆን ሀገራቸውን ከጥፋት የታደጉ ሲሆን  ያሁኑ ትወልድም  ልዩነቱን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ያለውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አባቶቹ አስከብርው ያቆዩለትን ሉዓላዊት ሀገር ማስቀጠልና የአባቶቹን ታሪክ ለመዘከር ነው፡፡

በዝግጅቱ የፖናል ውይይት ሲካሄድ “የአድዋ ድል እና ኢትዮጵያ” ፣  “የኢትዮጵያ ሕዝቦች የፀረ-ቅኝ ግዛት ትንቅንቅ በአድዋ” ጦር ሜዳ በሚል የቀረቡ ሲሆን በውይይቱም ወቅት በርካታ ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጐባቸዋል፡፡

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ለሰብዓዊ መብት መከበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገች ሀገር ስትሆን ከነዚህም መካከል  ዓለም አቀፍ ተቋማትን በግንባር ቀደምትነት በመመስረት፣ በመምራት እና ድንጋጌዎችን በማክበርና በማስከበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከተች ሲሆን ለምሳሌ እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፡ ሌግ ኦፍ ኔሽን አፍሪካ ህብረት ተጠቃሽ ሲሆኑ በተጨማሪ ሰላም በማስከበር እና በመጠበቅ እንደ ኮርያ፣ ሩዋንዳ፣ ላይቤሪያ፣ ሱዳን እና ኮንጎ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ሀገራችን ነፃነቷን ጠብቃ፣ አስከብራ ተፈረታ መኖር በመቻሏ ነው፡፡