News Archive News Archive

Back

አድዋ የኢትዮጵያውያን ታላቅ የትብብርና የአንድነት ከፍታ ማሳያ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ

አድዋ ለምንና እንዴት ተከሰተ  ምን አስከተለ ፤ምን ፋይዳ አለው፣ አድዋ የኢትዮጵያውያን ታላቅ የትብብርና የአንድነት ከፍታ ማሳያ   በሚል  ርዕስ  ጥናታዊ  ጽሁፍ የቀረቡ ሲሆን በውይይቱ ወቅት በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጐባቸዋል፡፡ በኘሮግራሙ ላይ የኢጀንሲው ሠራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ወጣቶች፣ የድርጅት ተወካዮች፣ የአባት አርበኞች በርካታ ተሳታፊዎች የታደሙ ሲሆን በስኬት ተጀምሮ ተጠናቋል፡፡

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ለሰባዊ መብት መከበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገች ሀገር ስትሆን ከነዚህም መካከል  አለም አቀፍ ተቋማትን በግንባር ቀደምትነት በመመስረት በመምራት እና ድንጋጌዎችን በማክበርና በማስከበር ከፍተኛ አስተዋፅ ያበረከተች ሲሆን ለምሳሌ እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፡ ሌግ ኦፍ ኔሽን አፍሪካ ህብረት ተጠቃሽ ሲሆኑ በተጨማሪ ሰላም በማስከበር እና በመጠበቅ እንደ ኮርያ፡ሩዓንዳ ፡ለይቤሪያ፡ሱዳን እና ኮንጎ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ይህ ሊሆን የቻለው ሀገራችን ነፃነቷን ጠብቃ፣ አስከብራ ተፈረታ መኖር መቻሏ ነው፡፡