News Archive News Archive

Back

ኤጀንሲው የአሰልጣኞች ስልጠና ሲከታተሉ ለቆዩ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት በመስጠት አስመረቀ።(ታህሳስ 2012 ዓ.ም)

ኤጀንሲው የአሰልጣኞች ስልጠና ሲከታተሉ ለቆዩ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት በመስጠት አስመረቀ።

ኤጀንሲያችን በሪከርድ ስራ አመራር ለ15 ቀናት የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት በዛሬው ዕለት አስመርቋል። ስልጠናውን የወሰዱት 18 ባለሙያዎች ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተውጣጡ እንደሆነ ከክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

እነዚህ ሰልጣኞች በየቢሮው የሚታየውን የሪከርድ እና የመዛግብት አያያዝ ችግሮችን ለመፍታት ለባለሙያዎች አጫጭር ስልጠናዎችን መስጠት የሚያስችላቸውን እውቀት እንዳገኙ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ሰልጣኞቹ በስልጠና በቆይታቸው የታዘቡትን አስተያየት ሰጥተዋል።

የስልጠና ክፍሉ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መኮንን ከፋለ አስተያየታቸውን ተቀብለው ወደፊት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ጥሩ ግብዓት መሆኑን በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ገልጸዋል። በመጨረሻም ከኤጀንሲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ከአቶ ሽመልስ ታዩ እጅ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል።