News Archive News Archive

Back

ለመቐለ ማረሚያ ቤት የመጽሐፍ ልገሳ ተደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ከትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከመቐለ ከተማ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጋር በመተባበር “በመጻሕፍት እንታረም በሚል መሪ ቃል ሰኔ 21/20011ዓ.ም በመቀሌከተማ ማረሚያ ቤት ተካሂዷል፡፡

ለመቐለው ዝግጅት ጉዞውን ሰኔ አስራ ዘጠኝ ወደ መቐለ ያደረገው ቡድን በሰኔ ሃያ አንድ ዝግጅቱን በመቀሌ ማረሚያ ቤት ጀምሯል፡፡

በዝግጅቱሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በኮማንደር ትበርዝ ሲደረግ የመክፈቻ ንግግር በኤጀንሲው የኢትዮጵያ ጥንትና ህግ ክምችት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በወ/ሮ እስከዳር ግሩም የዝግጅቱ ዓላማ የንባብ ባህል በማዳበር የለማና የበለጸገ አእምሮ ያለው ዜጋ በመፍጠር ሀገርንና ወገንን የሚጠቅም ትውልድ ለማድረግ የመጽሐፍት የገበያ ትስስር በመፍጠር ለደራሲንና በዘርፉ ለሚገኙ ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡

የዝግጅቱም መሐል በታራሚዎቹ የተጻፉ ትምህርት አዘል የሆኑ ሥነ-ጽሑፎች እየቀረቡ ታዳሚውን እያዝናኑ እንዲማሩ ሲያደርጓቸው ተስተውሏል፡፡

ደራሲና ተርጓሚ ኃይለመለኮት መዋዕል እና ደራሲ እየሩሳሌም ነጋ የህይወት ልምድ ተሞክሮ ቀርቦ ከታራሚዎቹ ሀሳብና አስተያየት ሲሰጥ የደራሲ ኃይመለኮት መዋዕል ጉንጉን ረጅም ልብወለድ መጽሐፍ በማረሚያ ቤቱ አለመኖሩን ታራሚዎች ጠቁመው ደራሲው እንደሚልኩላቸውና ማንበብ እንደሚችሉ ገልጸውላቸው አምስት ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በደራሲ ኃይለመለኮት የተተረጎመ የዊሊያም ሼክስፒር “ኦቴሎ” ቲያትር መጻሕፍትም ለማረሚያ ቤቱ ደራሲው አበርክተዋል፡፡

በዕለቱም በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በተሀድሶና ልማት ዘርፍ በትምህርትና ስልጠና ዳይሬክተር የትምህርትና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ተከተል ለታራሚዎቹ ሲናገሩ ይህን ፕሮግራም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ በኢትጵያ ውስጥ ላሉት የህግ ታራሚዎች መሪ ቃል አዘጋጅቶ ይህን ስራ ሊሰራ መነሳቱ የሚበረታታና ቀጣይነት እንዲኖረው ገልጸው በህግ ታራሚዎች ላይ እንዲሰራ መደረጉ ትክክለኛ እይታ ነው ምክንያቱም የህግ ታራሚው በህግ ጥላ ሥር ሆኖ የሚኖር ዜጋችን ነው በፍርድ ቤት ውሳኔ ለረጅም ዓመት በማረሚያ ቤት ሊቆዩ የሚችሉ ታራሚዎች ይኖራሉ ለእነዚህ የህግ  ታራሚዎች በወቅቱ ያሉትን የውጭ እባ የሀገር ውስጥ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉትን ሁኔታዎች ከሚድያ ቴክኖሎጂ ውጪ የሚያስተዋውቋቸው የተለያዩ መጽሐፍትን በማንበብና በማወቅ በመሆኑ እንደፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስድስት ማረሚያ ቤቶች እንዳሉና በሁሉም ማረሚያ ቤቶች ታራሚዎች ተደራጅተው የራሳቸውን ገቢ እንዲያገኑ በማድረግ በተለያዩ ስልጠናዎች በማሰልጠንና በማስተማር አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው በማረሚያ ቤቶች ሁሉ የሚገኙትን ለማሳተፍ እንደማይቻልና ምክንያቱም ያሉት የህግ ታራሚዎች ማንበብ መጻፍ ማስላት ከማይችን ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው በመሆኑ በተለያ ስልጠናዎች ላይ ማሣተፍ ያልተቻለው የህግ ታራሚዎች በየታራሚው መምሪያ ዞን ቤተ-መጻሕፍት ተከፍቶ የንባብ እና የውይይት አገልግሎት በመስጠት የተለያ መጻሕፍቶችን በማንበብ እትሙን በማጎልበት አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ተግባር ከዚህ በፊት በእነርሱም በዝዋይ ማረሚያ ቤት የንባብ ቀን የመጽሐፍት አውደርዕይ በማዘጋጀት አምስት መቶ ስልሳ መጻሕፍት የማበርከት ስራ መሰራቱን ገልጸው አሁንም ታዲያ ይህ መጽሐፍ ከኤጀንሲው መበርከቱ ታራሚዎቹ መጻሕፍቶችን በማንበብ አቅማቸውን እና እውቀታቸውን በማዳበር ያጠፉትን እና የበደሉትን ማህበረሰብ ይቅርታ በመጠየቅና በመፀፀት ለሀገሩና ለወገኑ የሚያስብ ዜጋ ማፍራት ስለሚቻል ፕሮግራሙ ለግዜው ብቻ ሳይሆን ቀጣይነት ባለው መልኩ በየዓመቱ መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

አክለውም በማረሚያ ቤት ውስጥ ያሉት መጻሕፍቶች ውስን በመሆናቸው አንዳንድ ታራሚዎች አንዱን መጽሐፍ ሁለትና ሶስት ግዜ እንዳነበቡት አስተያየት ሲሰጡ ሰምተናልና እኛም እንደፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አዲስ እየተገነቡ ባሉ ማረሚያ ቦች ደረጃውን የጠበቀ ቤተ-መጻሕፍት ለማደራጀት በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ተናግረው ከብሔራዊ ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ ጋርም በጋራ እየተሰራ ያለው ነገር ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ምክንያቱም ሁለቱም ተቋማቶች ሀገራዊ ግዴታ ያለባቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የተለያዩ የክፍልና የትምህርት ደረጃ የያዙ ሶስት መቶ አርባ አንድ መጻሕት ለማረሚያ ቤቱ ተወካይ ሲሰጥ በእለቱ በሥነ-ጽሑፍ ዘርፍ ለተወዳደሩ አምስት ታራሚዎች መጻሕፍት ፤ ኤጀንሲው ለማረሚያ ቤቱ ያዘጋጀውን የምስጋና ምስክር ወረቀት ከኤጀንሲው የስልጠናና ጥናት ምርምር ዳይሬክቶሬት  ዳይሬክተሩ ከአቶ መኰንን ከፈለ እጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡

የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተወካይ እና የባህል ልማት አስተባባሪ አቶ ዳዊት ትከቦ የዝግጅቱን ዓላማና በክልሉ መካሄዶ ያለውን ጠቀሜታ አስመልክቶ ለታሪሚዎቹ በመንገር ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡

 

በመጨረሻም ከታራሚዎቹ መካከል ያነጋገርናቸው ታራሚ መ/ር ሞገስ ካልሃይ እና ታራሚ አዜብ እንደተናገሩት በትምህርት ቤቶችና ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታ በርካታ ቤተ-መጻሕፍቶች አሉ በማረሚያ ቤት ግን ስለማይኖር ማረሚያ ቤት ያለው ታራሚ ገዝቶ ለማንበብ ፍላጎቱም የለውም ታራሚው ተስፋ የመቁረጥ ነገር ስለሚታይበት ዓለምን ለማወቅ ደግሞ መረጃ ሀብት ነው ስለዚህ ቤተ-መጻሕፍት በማረሚያ ቤት መኖሩ በርካታ ሰው እንዲያነብና ቀድሞ የነበረውን አስተሳሰቡን እንዲቀይር ይረዳዋል ሴቶች እንደወንዶቹ እንዲያነቡም እድል ይፈጥራል ሌላው እንደዚህ ደራሲያን ከታራሚዎች ር በሚቀራረቡበት ወቅት ከህይወት ተሞክሯቸው ውጪ መጻሕፍቶችን ለማረሚያ ቤቱ ስለሚለግሱና አንባቢ እንዲፈጠር ስለሚያደርጉ ይህ ስራ በኤጀንሲውና በማረሚያ ቤቱ ተጠናክሮ ቢሰራ በማለት ተናግረዋል፡፡

የማህበረሰቡን የንባብ ባህል ለማዳበር የንባብ ሳምንት ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ከትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የማህበረሰቡን የንባብ ባህል ለማዳበር “ክረም ተ መጻሕፍት ” በሚል መሪ ቃል ሰኔ 22 /20011ዓ.ም በመቐለ ከተማ በእንድራእሲ ሎጅ የንባብ ሳምንት ሲካሄድ በዝግጅቱም ላይ በርካታ ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡

 

በዝግጅቱም መጀመሪያ በአቶ ግርማይ ፍሮዝ የሚያሰለጥነው የወወክማ መቐለ የሙዚቃ ቡድን ባህላዊ ውዝዋዜ አቅርቦ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በተወካይ በአቶ ዩናስ ከተደረገ በኃላ የመክፈቻ ንግግር በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በአቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ ሲደረግ የዝግጅቱን ዓላማ፣መሪቃሉንና በክልሉ አጠቃላይ 1200 መጽሐፍት እንደተሰጠ ተናግረው እነዚህ መጻሕፍቶች ተማሪውም ሆነ ማህበረሰቡ በማንበብ እራሱንና ሀገሩን መለወጥ ይኖርበታል በማለት አበክረው ተናግረዋል፡፡

 

የደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕልና  የደራሲ እየሩሳሌም ነጋ የህይወት ተሞክሮ አስተማሪ በሆነ መልኩ ለታዳሚ ቀርቧል፡፡በዝግጅቱም ደራሲ እየሩሳሌም ነጋ ህጻን ሶሊያና ባቀረበችው ግጥም ተማርካ በእርስዋ የተፃፉ የልጆች መጻሕፍትን ለወወክማ መቐለ በስጦታ እንደምታበረክት ቃል ገብታለች፡፡

 

በመቀጠልም ጅማሮው ላይ ሲያዝናና የነበረው ወወክማ መቐለ የሙዚቃ ቡድን ንባብ ላይ ያተኮሩ በርካታ ግጥሞችን፣መነባንቦችንና አጭር ድራማ በማቅረብ ታዳሚውን አዝናንቷል፡፡

ከኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ከአቶ ይኩኖአምላክ እጅ ታዳሚውን በግጥምና በስነ-ፅሑፍ ላዝናኑት የመቐለ ወወክማ የሙዚቃ ቡድንና ለቡድኑ መሪ ለአቶ ግርማይ መጻሕፍት ሲበረከት በጋራ ለማዘጋጀት እቅዱን ቢያቅድም ብዙም በኃላፊነት ሥራዬ ነው ብሎ መስራት ላልደፈረው የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የምስጋና ምስክር ወረቀት በማበርከት ዝግጅቱ ተጠናቋል፡፡