News News

እንሰት እምነት ውበት የጋሞ ዕሳቤዎች ቅኝት!” በሚል ርዕስ 27/01/2012 ዓ.ም ህዝበ ገለፃ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ተካሄደ፡፡

ህዝበ ገለፃውን ያቀረቡት ዶክተር ታደሰ ወልዴ ከoxfored university የስነ-ሰዕብ አስተማሪ ሲሆኑ በንግግራቸው እንዳሉት እንሰት በአፍሪካ ብሎም በኢትዮጵያ ሁሉም ክፍሎች ይመገቡት የነበረና በኢትዮጵያ በጓሮ አካባቢና ከጓሮ ውጭ የሚተከል ለምግብነት የሚጠቀሙበት ተክልሲሆን እንሰት  በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በተለይም በጋሞ ብሔረሰብ ዘንድ ከምግብነት ባለፈ ህብረተሰቡ የአኗኗር፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው የማህበረሰ አስተሳሰብና ወግ ትስስርና መስተጋብር መገለጫ፣ ውበት፣ እምነትና እንደሰው ትውልድ በቤት ዙሪያ የሚተከል፣ በማህበረሰቡ የቤተሰቡ የሥራ ድርሻ ተዘርዝሮ ሥራ የሚከናወንበት ፋይዳው ብዙ የሆነ ተክል እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ያለ እንሰት ምን ቤት አለ  ያሉን ንግግር አቅራቢው እንሰት ከተክልነት ባለፈ የመሬትን ለምነት የሚጠበቅ፣ የአካባቢን መራቆት የሚከላከል፣ ተፈጥሮ ሚዛን እንድትጠብቅ የሚረዳ ለቤት መስሪያና ለምግብነት የሚያገለግል፣ የብሔረሰቡን የሽምግልና ስርዓት የሚያሳይ፣ ድንቅ የሆነ ተክል ነው፡፡

የጋሞ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ታሪክ ባህል ወግ፣ ቋንቋና የድንቅ ባህል ባለቤት ሲሆን የራሱ የሆነ ሀገር በቀል እውቀት ማለትም የቤት አሰራር፣ አስተራረስ እርቅ የመሬት አጠቃቀም ያለው ሲሆን ከእንሰት መድሃኒት፣ ጌጥ፣ ምግብ፣ ምንጣፍ የመሳሰሉትን የቤትና ከቤት ውጭ ቁሳቁሶችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከእንሰት ጋር የተቆራኘ ህዝብ ነው ብለዋል፡፡

ክለውም ይህን ድንቅ የሆነ ተክል ከዚህ የበለጠ ጥቅም እንዲሰጥ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መደገፉ እንዳለበት አበክረው ተናግረዋል፡፡

በዕለቱም ከተሳታፊዎች የማህበረሰቡ ሀገር በቀል እውቀ በመጠቀም አሁን አሁን እየገጠሙን ላሉ ችግሮች እንደሚችሉ እንዲያገለግል መሥራት እንዳለበት ሲገለጽ  ሌላው በርካተ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ከመድረኩ ማብራሪያዎችና ገለጻዎች በስጠት ታዳሚዎች ግንዛቤ እንዲጨብጡ  ተደርጓል፡፡

በዕለቱ በዝግጅቱ የታደሙ ታዳሚዎች እንዲህ ዓይነት ዝግጅቶችና ውይይቶች በስፋት መቅረብ እንዳለባቸውና ሀገር በቀል እውቀት፣ ልምድ፣ ታሪክና ባህል ላይ ኤጀንሲውም ሆነ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመፍታት እንደሚያስችልና መግባባት ለመፍጠር አይነተኛ መፍትሔ መሆኑን በአፅኖት ተናግረዋል፡፡


የንባብ ክበባት!!!!

በትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት ምስረታ አውደ ምክክር በባህርዳር ከተማ ዋተር ፍሮንት ሆቴል እየትካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ኤጀንሲ ከአራት አመታት በፊት በከተማው ላቋቋማቸው
አስር የትምህርት ቤቶች የንባብ ክበባት ብቻ በድምሩ 3238 መጽሀፍት በስጦታ አበርክቷል።


የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ፣ ከአማራ ብሔራዊ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና ከባህርዳር ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር "ህዳር ሲታጠን መጽሐፍ ሲተነተን " በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው የንባብ ሳምንት፣ የሥነጽሑፍ ውጤቶች ሽያጭና አውደ ርዕይ፣ የንባብ ሳምንትና የፓናል ውይይት አንድ አካል የሆነው የህጻናትና የቤተሰብ ንባብ የተካሄደው በባህርዳር ከተማ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዳራሽ ነው።

በመርሀግብሩም፡-

ወላጆች ለልጆች ተረቶችን አንብበዋል።

የህጻናት እና የቤተሰብ የንባብ ጥያቄና መልስ ተካሂዷል።

በተማሪዎች መካከል የምንባብ ትውስታ ጥያቄና መልስ ውድድር ተከናውኗል።

ደራሲ ህይወት ተፈራ ቤተስብ ለንባብ ባህል መስፋፋት ያላቸውን ሚና አስመልክታ ሀሳብ አካፍላለች።

ለተወዳዳሪዎች እና ተሳታፊዎች የመጻህፍት ሽልማት ተበርክቷል።


"ህዳር ሲታጠን መጽሐፍ ሲተነተን"
ሀገር አቀፍ የንባብ ሳምንት መርሀግብር አንድ አካል የሆነው የውይይት መድረክ በባህርዳር እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ ከአማራ ባህልና ቱሪዝምና ከባህርዳር ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ከህዳር 12 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ህዳር 16 ቀን 2012 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ መርሀግብር አንድ አካል የሆነው ይህ ውይይት በባህርዳር ዩንቨርስቲ ፔዳ ግቢ ትልቁ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ የውይይት መርሀግብር ላይ:-

"የንባብ ባህል በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ ማረው ዓለሙ (ዶ/ር)
"የንባብ ክሂል" በደራሲ ሀይለመለኮት መዋዕል

"ህዳር ሲታጠን ታሪካዊና ባህላዊ ገጽታው" በመምህር ተመስገን በየነ
"የጣና ደሴት ሕያው ላይብረሪ"በተጓዥ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም
"የንባብ ባህል በግዕዝ ሥነ ጽሁፍ ውስጥ" በአማን ግሩም (አባ) ጥናታዊ ወረቀቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።


ህዳር 15/2012 ዓ ም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ከጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ፣ ከሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር በመጡ እንዲሁም በኤጀንሲው የዘርፉ ምሁራን በዲጂታል ላይብራሪና የህትመት ዝግጅት ደረጃ በኢትዮጵያ እና አብያተ መዛግብት መቋቋም ታሪካዊ አሻራዎችን ከመጠበቅ እስከ ማስቀጠል እና በመሳሰሉት ርዕሶች ላይ ውይይት ተካሄደ።

News Archive News Archive

Back

በድሬዳዋ የንባብ ሳምንት ተካሄደ

ኤጀንሲው “ክረም ተ መጻሕፍት በአንባቢዋ ድሬ” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ ከተማ ከድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የንባብ ሳምንት በስኬት ተጠናቋል፡፡ፕሮግራሙ ሰኔ 19 ቀን 2011ዓ.ም. በለገሀር የባቡር ጣቢያ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በከተማው የትምህርት ቢሮ የማርሺንግ ባንድ እና ከአስር ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ የተማሪዎች ሰልፍ ታጅቦ በደማቅ ሁኔታ ተከፍቷል፡፡ በመክፈቻው ሥነሥርዓት ላይ የከተማው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙራድ በደዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ይኩኖአምላክ መዝገቡ በፕሮግራሙ ዓላማና አስፈላጊነት ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

የንባብ ሳምንቱ በተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር፣ የፓናል ውይይቶች፣ ኤግዚብሽን፣ የመጽሐፍት ሽያጭ፣  የንባብ ክበባትን በማቋቋም የመጽሐፍት ልገሳን እና የስነጽሑፍ ምሽትን ያካተተ ነው፡፡ የፓናል ውይይቶቹ ላይ የኤጀንሲው ባለሙያዎች ጥናታዊ ጽሑፎችን አቅርበው ሰፊ ምክክር የተደረገበት እና በደራሲ ዘነበ ወላና በደራሲ እሴተ ታደሰ የንባብ ልምድና ተሞክሮ የተገለጸበት መድረክ ነበር፡፡ በዚህም የንባብ ባህላችን የሚያድግበትን መንገድ ለማመላከት ተሞክሯል፡፡የዚህ ጉባኤ ተሳታፊዎች ከከተማው ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራንና ተማሪዎች፣ የመንግስት ቢሮ ሰራተኞችና የወጣት ማዕከላት ሰራተኞችና የቤተ መጻሕፍት ሰራተኞች ይገኙበታል፡፡  

በተመሳሳይ “በመጻሕፍት እንታረም” በሚል መሪ ቃል ከድሬዳዋ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጋር ለድሬዳዋ ማረሚያ ቤት ታራሚዎች የተዘጋጀው ፕሮግራም ሰኔ 21 ቀን 2011ዓ.ም. በማረሚያ ቤቱ ኣዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በዚህ ዕለት ደራሲ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ እና ደራሲ እሴተ ታደሠ ታራሚዎቹ በማንበብ ራሳቸውን በእውቀት እንዲያንጹና በመጻሕፍት መታረምን እንዲያዘወትሩ መክረዋል፡፡ በተለይም ደራሲ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ በ20 ዓመት የማረሚያ ቤት ቆይታቸው እንዴት በማንበብ ራሳቸውን እንዳሳደጉና ደራሲ እከመሆን እንደደረሱ ምሳሌ ነኝ ብለው መክረዋል፡፡ በዋናነት ታራሚው የራሱን ንጽሕና እንዲጠብቅ፣ ያለበትን ሁኔታ መቀበልና ራሱን ማሳመን ተገቢ መሆኑን፣በማንበብ ራሱን ማነጽ እንደሚገባው በአንክሮ መክረዋል፡፡ታራሚዎቹ በንባብ ያዳበሩትን የግጥም ክህሎት አቅርበው ታዳሚውን አስደንቀዋል፡፡

በመጨረሻም ኤጀንሲው ለማረሚያ ቤቱ በግዥና በስጦታ ያሰባሰበውን መጻሕፍት በመለገስ እንዲሁም ማረሚያ ቤቱ ለዚህ ፕሮግራም ስኬት በመተባበሩ የምስጋና ምስክር ወረቀት በመስጠት የዕለቱ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡ 

በሌላ መኩል የዚሁ ፕሮግራም አካል የሆነው የሥነጽሑፍ ምሽት ሰኔ 21 ቀን 2011ዓ.ም. በድሬዳዋ ራስ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በመክፈቻ ላይ የአፍረን ቀሎ የባህል ቡድን  የሀረርን ባህላዊ ዘፈን በውዝዋዜ  አጅበው አቅርበዋል፡፡ የግጥምና የሥነጽሑፍ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች የግጥምና የመነባንብ ሥራዎቻቸውን አቅርበው ታዳሚዉን አስደምመውታል፡፡

በሥራዎቻቸው የተደነቁትና የሚያንጽ ምክር የለገሷቸው አንጋፋው ደራሲ ዘነበ ወላ ይህንን ችሎታችሁን በማንበብ ልታዳብሩት ይገባል ብለዋል፡፡ በተለይም አንድ ሰው በየቀኑ ለ15 ደቂቃ በማንበብ ጥሩ በሳምንት ከሁለት አስከ ሶስት መጻሕፍትን ስለሚያነብ ጥሩ አንባቢ ይወጣዋል ብለዋል እና ይህንን ልታዳብሩት ይገባል ብለው ምክራቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በማጠቃለያ ላይም ኤጀንሲው ለተወዳዳሪዎች የማበረታቻ የመጽሐፍት ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡