News Archive News Archive

Back

ክረም ተ መጻሕፍት!" እንዲሁም "በመጻሕፍት እንታረም!" የክረምት ንባብ ዘመቻ ሊጀመር ነው። (ሰኔ 14 ቀን 2011 ዓ.ም)

"ክረም ተ መጻሕፍት!" እንዲሁም "በመጻሕፍት እንታረም!"  በሚል መሪ ቃል የክረምት ንባብ ዘመቻ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ሊጀመር ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ በዋናነት የሚመራውና ከሳይንስና እውቀት ሽግግር ቴክኖሎጂ ማህበርና ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ጋር በመተባበር የሚካሄደው የክረምት የንባብ ዘመቻ ከስኔ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ይጀመራል።

አዲስ አበባ ከተማና ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን ጨምሮ በሚካሄደው ክረምተ ንባብ ድሬዳዋ ከተማና ድሬዳዋ ማረሚያ ቤት፣ደብረ ብርሀን ከተማና ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት፣ባህርዳር ከተማና የባህርዳር ከተማ ማረሚያ ቤት፣መቀሌ ከተማና መቀሌ ማረሚያ ቤት እንዲሁም ባሌ ሮቤ ከተማና ሮቤ ማረሚያ ቤት ዘመቻው የሚካሄድባቸው ከተሞች ናቸው።

ለዚህ የንባብ ዘመቻ ለእያንዳንዱ ከተማ የ100,000 (የአንድ መቶ ሺህብር መጻህፍት በግዢ የሚሰጥ ሲሆን የሳይንስ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማህበር ደግሞ አምስት ሺህ መጻሕፍትን ያበረክታል ተብሏል፡፡ ከዚህ ዘመቻ ህብረተሰቡ የተለያዩ ልምዶችና ዕውቀት ይቀስማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡