Welcome

» Core Business

    » Training and Research

    » Archives and Manuscripts Administration

    » National Library Information Resources management

    » Ethiopian Studies and Legal Deposit service

    » Public Library Service

    » Records Management

» Wat's on...

    » Exhibition

    » Public Lecture

» Training

    » E-training

    » Training on demand

» Useful Information

    » Contacts

    » Videos

    » Nala Location

» Registration

    » ISBN Request

    » Record Center

Useful Links

Photo Gallery

» Download Membership Registration Form

የኢትዮጰያ ጥናትና ህግ ክምችት

የዚህ ዳይሬክቶሬት ዋነኛ አገልግሎት በመዛግብቱ ዘርፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት መንግሥታዊ ከሆኑ መሥሪያ ቤቶች በሚሰባሰቡና በሚደራጁ መዛግብት አገልግሎት መስጠት እንዲሁም በቤተመጻሕፍት ዘርፍ ስለ ኢትዮጵያ የተጻፉትን ማንኛውንም ሕትመትና ሕትመት ያልሆኑ መረጃዎች፣ ጥንታዊ ጽሑፎችን በማደራጀት አገልግሎት መስጠት ነው፡፡
በዳይሬክቶሬቱ ስርም አምስት የአገልግሎት መስጫ ክፍሎች ሲኖሩ እነሱም፡-
1. የመዛግብት አገልግሎት
2. የጥንታዊ ጽሑፎች አገልግሎት
3. የኢትዮጵያ ጥናት አገልግሎት
4. የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አገልግሎት
5. የማይክሮፊልም ላይብረሪ አገልግሎት

1. የመዛግብት አገልግሎት ክፍል:-
በመዛግብትና ኢትዮጵያ ጥናት አገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ውስጥ የሚገኝ ክፍል ነው፡፡ የመዛግብት አገልግሎት መስጫ ክፍል የሚከተሉትን የመዛግብት ዓይነትና ስብስቦች ያካተተ ክፍል ነው፡፡ ከተለያዩ መንግሥታዊ ከሆኑ መስሪያ ቤቶች የተሰበሰቡ መዛግብቶች እነሱም በከፊል፡-
 የግቢ ማኒስቴር መዛግብቶች
 የአልጋ ወራሽ መዛግብቶች
 የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መዛግብቶች
 የገንዘብ ሚኒስቴር መዛግብቶች
 የናሽናል ባንክ መዛግብቶች
 የሀገር ግዛት መዛግብቶች
 የመሳሰሉት
መንግስታዊ ከሆኑ መስሪያ ቤቶች በተጨማሪ ከተለያዩ ታዋቂ ከሆኑ ግለሰቦች በግል ተይዘው የነበሩ መዛግብቶች፣ መዛግብቶቹ ከያዙት የጽሁፍ ዶክመንት በተጨማሪ በርካታ የካርታና ፎቶግራፍ ስብስቦችንም የያዙ ናቸው፡፡


የመዛግብቶቹ ይዘትና የተጻፉበት ቋንቋ

አብዛኛዎቹ መዛግብቶች የተጻፉት በአማርኛ ቢሆንም በግዕዝ፣ በእንግሊዘኛ፣ በጣሊያንኛ፣ በፈረንሳይኛ እንዲሁም በአረብኛ የተጻፉ መዛግብቶችም በብዛት ይገኛሉ፡፡ በአብዛኛው መዛግብቶቹ የሚያተኩሩት የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሀይማኖታዊና ታሪካዊ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን የሚዳስሱ ናቸው፡፡

ክፍሉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
- የንባብ አገልግሎት
- የጥናትና ምርምር አገልግሎት
- የፎቶ ኮፒ አገልግሎት
- ስላሉት የመዛግብት ክምችት ገለጻ ማድረግ

መዛግብቶቹ ለተገልጋዮች በሚመች መንገድ ተደራጅተው ይገኛሉ፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት በኒርምስ /Nilrms Soft Ware/ ሶፍትዌር በመታገዝ የበለጠ በዘመናዊ መንገድ በመደራጀት ላይ ይገኛሉ፡፡

አገልግሎት ፈላጊዎች ማሟላት የማገባቸው
በክፍሉ ጥናትና ምርምር ለማድረግ የሚመጡ ተገልጋዮች ከየትኛውም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ሕጋዊ ተቋማት ወይም ከትምህርት ተቋማት የትብብር ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

                           አገልግሎት የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት
                           ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡3ዐ - 11፡3ዐ

       2. የጥንታዊ ጽሑፎች አገልግሎት ክፍል
የእጅ ጽሑፎችንና የቆዩ የሕትመት የመረጃ ምንጮችን ለማንበብና መረጃ ለማግኘት ጥናትና ምርምርለሚፈልጉ ተገልጋዮች አገልግሎት ይሰጣል፡፡

የጥንታዊ ሥነ-ጽሑፍ አገልግሎት መስጫ የሚገኘው በነባሩ ሕንጻ ላይ ሆኖ የማንበቢያ ክፍሉ ከክምችት ክፍሉ ጋር ጐን ለጐን የሚኝ ነው፡፡ ይህ ክፍል ኤጀንሲው በ1936 ዓ.ም. ሲቋቋም አብሮ ሥራውን የጀመረ ሲሆን አሁንም ጥንታውያን የመረጃ ምንጮች ዓይነት
በክፍሉ የሚገኙ የመረጃ ምንጮች፡-
1. ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ያሉ በብራና ላይ የተጻፉ
2. ከዘመናዊ ወረቀት በፊት የነበሩ ልዩ የመጻፊያ ወረቀት መሰል ላይ የተጻፉ
3. በዘመናዊ ህትመት የታተሙ የቆዩ መጻሕፍትና ጋዜጦች
4. ኤጀንሲው በዓለም የሥነ ጽሑፍ ቅርስነት በዩኔስኮ ካስመዘገባቸው 12 የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች መካከል፡-
           - የ14ኛው መ/ክ ወንጌል
           - የ15ኛው መ/ክ የጳውሎስ መልዕክት
           - የ15ኛው መ/ክ ግብረ ሕማማት
           - በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ዕትም መዝሙረ ዳዊት
           - አጼ ቴዎድሮስ ለእንግሊዝ ንግሥት ቪክቶሪያ የላኩት ደብዳቤ
           - ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ለሞስኮው ቄሳር ዳግማዊ ኒኮላስ የላኩት ደብዳቤ
           - የሸዋው ንጉስ ሳህለ ሥላሴ ለእንግሊዝ ንግሥት የላኩት ደብዳቤ
              በክፍሉ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ይዘትና የተጻፉበት ቋንቋ :-
የመረጃ ምንጮቹ የተጻፉበት ቋንቋ ግዕዝ፣ አረብኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ኦሮምኛና ሌሎችንም ያካተተ ሲሆን ይዘታቸውም በሃይማኖት፣ በሀገር ውስጥና በዓለም ላይ ያተኮረ ታሪክ፣ ሕግ፣ ቋንቋ፣ ፖለቲካና የውጭ ግንኙነት የልዩ ልዩ ብሔረሰቦችና ሃይማኖቶች ታሪክ፣ ባህላዊ መድኃኒት፣ የአስማት ጽሑፎችና በመሳሰሉት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

የአገልግሎት አይነት
1. የንባብ፣ የጥናትና ምርምር አገልግሎት
2. ስለ ብራና መጻሕፍትና ስለ ኢትዮጰያ ጥንታዊ ጽሑፎች አጀማመርና ታሪክ ጉብኝትና ገለጻ


አገልግሎት ፈላጊዎች ማሟላት የሚገባቸው
1. ለንብብ እንዲሁም ጥናትና ምርምር ማድረግ ለሚፈልጉ ሕጋዊ ከሆነ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆነ ተቋም ወይም ከትምህርት ተቋማት ሕጋዊ የትብብር ደብዳቤ በማምጣት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
2. ተሰባስበው ጉብኝት ማድረግ ለሚፈልጉ ከላይ ከተጠቀሱት ተቋማት ደብዳቤ በማምጣትና ቀደም ብሎ በማሳወቅ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል፡፡

                                አገልግሎት የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት
                                ከሰኞ እስከ አርብ ፡- ጠዋት ከ2፡3ዐ - 11፡3ዐ

        3. የኢትዮጵያ ጥናት አገልግሎት ክፍል
ይህ አገልግሎት መስጫ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ተገልጋዮች አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ በክፍሉ ውስጥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1682 ዓ.ም. ጀምሮ በውጭ አገርና በኢትዮጰያውያን ፀሐፊዎች የተጻፉ ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ መካከለኛና ዘመናዊ ታሪክ እንዲሁም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ የተጻፉና የተተረጐሙ፤ በብሔር ብሔረሰቦች ታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ላይ የተጻፉ፣ የነገሥታት መሪዎችና ታዋቂ ሰዎች የሕይወት ታሪክና ሥራዎች ላይ በተለያዩ በአገር ውስጥና በውጭ ቋንቋዎች የተጻፉ መጻሕፍት ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በታሪክ ትምህርት፣ ጤናና የሕግ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መጽሔቶች (Journals) ይገኛሉ፡፡ በክፍሉ ያሉት የመረጃ ምንጮች ከመጻሕፍት በተጨማሪ ፎቶግራፎች፣ ካርታዎችና በሥዕል የተደገፉ የአገሪቱን ታሪክ፣ የሕዝቦችን ባሕልና መልክዓ ምድር የሚያሳዩ ይገኛሉ፡፡ ከታዋቂ የውጭ ታሪክ ፀሐፊዎች መካከል ኦገስት ዲልማን፣ ካርሎ ኮንቲ ሮሲኒ፣ ኢግናዚዮ ጉዊዲ፣ ጆብ ሉዶልፍ፣ ኢኖ ሊትማን፣ ጀምስ ብሩስ፣ ሲሊቪያ ፓንክረስትና ሪቻርድ ፓንክረስት ይገኙባቸዋል፡፡

መጻሕፍቱ የተጻፉበት ቋንቋ፡-
ከአገር ውስጥ ቋንቋዎች በተጨማሪ የሚከተሉት የውጭ ቋንቋዎች ይገኙበታል፡፡ እንግሊዘኛ፣ ጀርመንኛ፣ ፈረንሳይኛና ጣሊያንኛ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የሚሰጡ አገልግሎቶች፡-
- የንባብ፣ የጥናትና የምርምር አገልግሎት
- የፎቶኮፒ አገልግሎት

ተጠቃሚዎች ማሟላት የሚገባቸው
በክፍሉ ጥናትና ምርምር ለማድረግ የሚመጡ ተገልጋዮች ከየትኛውም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ሕጋዊ ተቋማት ወይም ከትምህርት ተቋማት የትብብር ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

                                   አገልግሎት የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት
                                  ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡3ዐ - 11፡3ዐ
                                  ቅዳሜ ከ3፡ዐዐ - 1ዐ፡ዐዐ

    4. የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አገልግሎት ክፍል
በዚህ አገልግሎት መስጫ በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የተጻፉ የልብ ወለድና ለጠቅላላ ዕውቀት የሚረዱ የታሪክ፣ የቋንቋ፣ የሥነ ጽሁፍ፣ የሃይማኖትና የመሳሰሉት መጻሕፍት ይገኛሉ፡፡ በዚህ ክፍል ማንኛውም አንባቢ ያለ ቅድመ ሁኔታ መጠቀም ይችላል፡፡

                                       የሥራ ሰዓት
                             ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡3ዐ - 12፡ዐዐ
                                       ቅዳሜ ከ3፡ዐዐ - 1ዐ፡ዐዐ
                                       እሁድ ከ3፡ዐዐ - 1ዐ፡ዐዐ

     5. የማይክሮፊልም ላይብረሪ አገልግሎት
በዚህ ክፍል የኢትዮጵያን ሥነጽሑፍ ጥንታዊነት የሚያሳዩ እድሜያቸው ከአንድ ሺህ ዓመት በላይ የሆኑ በብራና ላይ የተጻፉ ጥንታውያን መጻሕፍት ከተለያዩ የሀገሪቱ ታላላቅ የታሪክና ሥነጽሑፍ ቦታዎች ከሆኑ በማይሮፊልም ተቀርፀው በክፍሉ ይገኛሉ፡፡ ቁጥራቸው ከ95ዐዐ በላይ የሆኑ በማይክሮፊልም ላይ የሚገኙት ጥንታውያን የጽሑፍ ሀብቶች ለተገልጋዮች አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ዋና ቅጂዎች በተለያየ ምክንያት ጉዳት ሲደርስባቸውና ቢጠፉ እንደምትክ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ በክፍሉ ያሉት የፊልም ክምችቶች በፊት የኢትዮጵያ ብራና ጽሑፎችና ማይክሮፊልም ላይብረሪ (EMML) ተብሎ ከሚጠራው ድርጅት በመዋቅር ምክንያት ወደ ኤጀንሲው የተዛወሩ ናቸው፡፡

 

የሚሰጡ አገልግሎቶች
- ለማይክሮፊልም በተዘጋጀ ዘመናዊ የማንበቢያ መሣሪያ የንባብ አገልግሎት፣
- ከማይክሮፊልም ላይ ጥያቄ ሲቀርብ በሕትመት ወይም በዲጂታል ኮፒ የቅጂ አገልግሎት መስጠት፡፡

አገልግሎት ፈላጊዎች ማሟላት የሚገባቸው
በክፍሉ ጥናት ምርምር ለማድረግ የሚመጡ ተገልጋዮች ከየትኛውም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ሕጋዊ ተቋማት ወይም ከትምህርት ተቋማት የትብብር ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

                          አገልግሎት የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት
                          ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡3ዐ - 11፡3ዐ

 

 

Last Modified: 11/15/2013

NALA News

Downloads