Welcome

» Core Business

    » Archives and Ethiopian Study

    » Reference & Legal deposit

    » Customer Service &
Research

    » Information resource
administration

» Wat's on...

    » Exhibition

    » Public Lecture

» Training

    » E-training

    » Training on demand

» Useful Information

    » Contacts

    » Videos

    » Nala Location

» Registration

    » ISBN Request

    » Record Center

Useful Links

Photo Gallery

» Download Membership Registration Form

ስለ ኤጀንሲው

የዛሬው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ

• ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት “የሕእብ ቤተመጻሕፍት ወመዘክር” በሚል ስያሜ 1936 . በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተመርቆ የተከፈተ ሲሆን አገልግሎት መስጠት የጀመረውም ንጉሱ ባበረከቱት የመጻሕፍት ስጦታ ነው፣
• በ1958 ዓ.ም በተደረገው የቤተመጻሕፍት መዋቅር ለውጥ ብሔራዊ ቤተመጻሕፍት የሚል ስያሜ ይዞ በጥንታዊ ቅርሶች አስተዳደር ሥር እንድሠራ ተደረገ፣
• በ1967 ዓ.ም በመጀመሪያ ደረጃ ተዋቅሮ ሥራውን ቀጠለ፣
• በ1968 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 50/68 ለባህልና ስፖርት ጉዳይ ሚ/ር በሀገር ውስጥ ከሚታተሙ ማናቸም ህትመቶች ሶስት ሶስት ቅጂዎችን እንዲረከብ በመንግስት የተሰጠውን ሥልጣን ቤተመጻሕፍቱ እንድያስፈጽም ውክልና አገኘ፣
• በ1972 ዓ.ም ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት መምሪያ ተብሎ ስራውን እንድያከናውን ተደረገ፣
• በ1986 ዓ.ም በተረገ የመዋቅር ለውጥ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት የሚል ስያሜ ይዞ እንድሠራ ተደረገ፣
• የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት በአዋጅ ቁጥር 179/91 በሀገሪቱ የሚገኙ መዛግብትን መጻሕፍትንና መሠል ጽሁፎችን በእንድ ማዕከል ስር በማሰባሰብና በማደራጀት የሀገሪቱን የመረጃ አገልግሎት በተቀናጀ ሁኔታ መምራት የሚያስችለውን ህጋዊ ሰውነት አገኘ::
• በ1998 ዓ.ም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባፀደቀው አዋጅ ቁጥር 471/98 የአስፈጻሚ መ/ቤቶች ስያሜ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛብትና ቤተመጻሕፍት ድርጅት - ኤጀንሲ በሚል መጠሪያ እንድለወጥ ተደርጎ የተጣለበትን ኃላፍነት በመወጣትላይ ይገኛል::

ዓላማ
• የሀገሪቱን የመረጃ ሀብቶች በማሰባሰብ፣ በማደራጀት፣በመንከባከብና በመጠበቅ ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለማገናዘቢያ/ሪፈረንስ/ አገልግሎት ማቅረብ ነው፡፡ 
 
ተልዕኮ፡-
የአገሪቱን የመረጃ ሀብቶች በማሰባሰብ እና በማደራጀት ለጥናትና ምርምር ማዋልና ብሔራዊ የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረግ ለትውልድ ማስተላለፍ፡፡
ራዕይ፡-
በሀገሪቱ የመረጃ ሀብቶች አጠቃቀም ባህል በማዳበር ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና ለዕድገት በማዋል በ2012 በአፍሪካ በመጀመሪያ ደረጃ ካሉት አምስት ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት ማዕከላት አንዱ ማድረግ፡፡
የጋራ ዕሴቶችና መርሆዎች፡-
                 • ለሙያው ስነምግባር መገዛት፣
                 • ብቁና ቀልጣፋ አገልግሎት፣
                 • አሳታፊ አመራር፣
                 • ተጠያቂነት፣
                 • ግልጽነት፣
                 • ለለውጥ ዝግጁነት፣

የኤጀንሲው ስልጣንና ተግባር
• የታተሙ ጽሑፎች፣ በከፊል የታተሙ ጽሑፎች /ግሬይ ሊትሬቸር/፣ያልታተሙ ጽሑፎች የማኑስክሪኘት፣ የታሪካዊ መዛግብትና የሪከርዶች እንዲሁም የትውፊታዊም ሆነ የቃል ታሪኮች የቀረፀ ድምፅ የቀረፀ ምስልና የቀረፀ ምስልና ድምፅ ባጠቃላይም የመረጃ ቅርሶች ብሔራዊ የክምችት ማዕከል ሆኖ መስራት፣
• በውጭ ሀገር ያሉትን የኢትዮጵያ የስነጽሑፍ ቅርሶች ወደሀገር ለማስመለስ ጥረት ማድረግ፣
• ዋና/ኦሪጅናል መዛግብትና የዶክመንት ቅርሶች በቋሚነት ከአገር እንዳይወጡ ቁጥጥር ማድረግ፣
• የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝገበ መጻሕፍትንና መዝገበ መጽሔትን ማዘጋጀት፣ ማሳተምና ማሠራጨት፣
• የአገሪቱ ዓለም አቀፍ ስታንዳርድ የመጻሕፍትና የመጽሔት መለያ ሰጪ አካል ሆኖ መስራት፣
• ከአገር አቀፍና ዓለም አቀፍ አካላት ጋር ግንኙነት በማድረግ የቤተመጻሕፍትና የቤተመዛግብት ሙያ እንዲያድግና እንዲስፋፋ ጥረት ማድረግ፣
• ኤጀንሲው ለተቋቋመበት ዓላማ መሳካት የስልጠና ማዕከል ሆኖ መስራት፣
• በክልል መስተዳድሮች ከተቋቋሙና ከሚቋቋሙ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት እንዲሁም የሕዝብ ዓቢያተ መጻሕፍት ጋር በመተባበር መስራት የሚሉት ይገኙበታል ፡፡

Last Modified: 07/25/2016

NALA News

» ታህሳስ 2009 ዜና

የቻይና  የባህል ልዑካን ቡድን አባላት የኤጀንሲውን የስራ እንቅስቃሴ  ጎበኙ

የቻይና የባህል ልዑካን ቡድን አባላት እ.ኤ.አ ኖቬምበር 17 ቀን 2ዐ16 የብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት ኤጀንሲ የሥራ እንቅስቃሴዎችንና የመረጃ ሀብቶችን በመጎብኘት ኤጀንሲው እያደረገ ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡ የቻይና የባህል ቡድን አባላት ከጎበኗቸው የመረጃ ሀብቶች መካከል በዩኔስኮ በዓለም የጽሑፍ ቅርስነት የተመዘገቡ 12 የጽሑፍ ሀብቶች ይገኙበታል፡፡

የልዑካን  ቡድኑ አባላት የጎበኞቸው የሥራ ክፍሎች የጥንታዊ ጽሑፎች ክፍል፣ የማይክሮፊልም ንባብ ክፍል፣ የሪፈረንስና ዶክዩመንቴሽን አገልግሎት ክፍል፣ የሕግ ክምችት ክፍልና የመዛግብት ንባብ ክፍል ናቸው፡፡

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ በሚኒስትር ማዕረግ የቻይና ሕዝብ የፖለቲካ አማካሪ ኮንፈረንስ ምክትል ሊቀመንበር የተከበሩ ቺን ቹዋግሊን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በአፍሪካ  በቀዳሚነት  የራሷ ፊደልና ጽሑፍ ያላት ሀገር መሆኗን በታሪክ የሚያውቋት መሆናቸውን በማስታወስ አሁን ያሏትን ብርቅና ድንቅ የሆኑ በተለይ የብራና ጽሑፎችን በአግባቡ ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ  በአጽንኦት  አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ የቻይና የባህል ዘርፍ ከኤጀንሲው ጋር በመተባበር ዘርፉን በስልጠናና በመሰል ጉዳዮች ላይ ለማሳደግ በጋራ እንደሚሠሩ ቺን ቹዋግሊን ተናግረዋል፡፡

በኘሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ  የሀገሪቱን እና የተቋሙን መልካም ገጽታ መገንባት እንዲቻል   ሀገሪቱ  የጽሑፍ እና የሰው ዘር  መገኛ ብቻ ሳትሆን የቡና መገኛ ሀገር መሆኗንም  ለማስተዋወቅ እንዲቻል በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር  ክቡር አቶ አብርሃም  ጮሻ   የቡና ስጦታ ተበርክቶላቸው የጉብኝት ኘሮግራሙን በጥሩ ሁኔታ ለማጠቃለል ተችሏል፡፡

Downloads