Welcome

» Core Business

    » Training and Research

    » Archives and Manuscripts Administration

    » National Library Information Resources management

    » Ethiopian Studies and Legal Deposit service

    » Public Library Service

    » Records Management

» Wat's on...

    » Exhibition

    » Public Lecture

» Training

    » E-training

    » Training on demand

» Useful Information

    » Contacts

    » Videos

    » Nala Location

» Registration

    » ISBN Request

    » Record Center

Useful Links

Photo Gallery

» Download Membership Registration Form

የመዛግብትና የጽሑፍ ቅርስ አስተዳደር

የመዛግብት እና የጽሑፍ ቅርስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የዚህ ዳይሬክቶሬት ዋና ዋና  አገልግሎቶች  በመዛግብቱ ዘርፍ በኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚገኙ መንግስታዊ ከሆኑት መስሪያ ቤቶች በሚሰበሰቡና በሚደራጁ መዛግብት አገልግሎት መስጠት እንዲሁም በቤተመጻሕፍት ዘርፍ ጥንታዊ ጽሑፎችን በማደራጀት አገልግሎት መስጠት ነዉ፡፡

በዳይሬክቶሬቱ ስር የሚገኙ  ንዑሳን  ክፍሎች ፡-

 1. የመዛግብት ጽሑፍ አገልግሎት ክፍል
 2. የጥንታዊ ጽሑፍ አገልግሎት ክፍል
 3. የጥንታዉያን ጽሑፎች ዝዉውርና ማደራጀት ክፍል
 4. የመዛግብት ዝዉውርና ማደራጀት ክፍል እና 
 5. የማይክሮ-ፊልም እና ቀረፀ-ድምጽ መዛግብት አገልግሎት ክፍል  ናቸው

 

1.     የመዛግብት አገልግሎት ክፍል

 ይህ ክፍል በመዛግብትና ኢትዮጵያ ጥናት አገልግሎት አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት ዉስጥ የሚገኝ ክፍል ነዉ፡፡ የመዛግብት አገልግሎት መስጫ ክፍል ከተለያዩ መንግስታዊ ከሆኑ መስሪያ ቤቶች የተሰበሰቡ መዛግብትን    ያካተተ ክፍል ነዉ፡፡ እነሱም በከፊል፡-

 • የግቢ ሚኒስቴር መዛግብት
 • የአልጋ ወራሽ መዛግብት
 • የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መዛግብት
 • የገንዘብ ሚኒስቴር መዛግብት
 • የናሽናል ባንክ መዛግብት
 • የሀገር ግዛት መዛግብት እና  ሌሎች

መንግስታዊ ከሆኑ መስሪያ ቤቶች  ከተሰበሰቡ መዛግብት በተጨማሪ ከተለያዩ ታዋቂ ከሆኑ ግለሰቦች በግል ተይዘዉ የነበሩ መዛግብትም ይገኙበታል፡፡ በርካታ የካርታና የፎቶግራፍ ስብስቦችንም የያዙ ናቸዉ፡፡

የመዛግብቶች ይዘትና የተጻፉባቸዉ ቋንቋዎች

አብዛኞቹ መዛግብት  የተጻፉት በአማርኛ ቢሆንም በግዕዝ፣ በእንግሊዝኛ፣ በጣሊያንኛ፣ በፈረንሳይኛ እንዲሁም በአረብኛ ቋንቋዎች የተጻፉ መዛግብትም በብዛት ይገኙበታል፡፡ በአብዛኛዉ መዛግብቱ የሚያተኩሩት በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሀይማኖታዊና ታሪካዊ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ላይ  ነው ፡፡

በክፍሉ የሚሰጡ  አገልግሎቶች

 • የንባብ አገልግሎት
 • የጥናትና ምርምር አገልግሎት
 • የፎቶ ኮፒ አገልግሎት
 • የመዛግብት ክምችት ገለጻ ማድረግ
 • የአዉደ ርዕይ አገልግሎት

መዛግብቱ  ለተገልጋዮች በሚመች መንገድ ተደራጅተዉ ይገኛሉ፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት በኒለርምስ ሶፍት ዌር (Nilrm soft ware) በመታገዝ የበለጠ በዘመናዊ መንገድ በመደራጀት ላይ ይገኛሉ፡፡

o   አገልግሎት ፈላጊዎች ማሟላት የሚገባቸዉ

በክፍሉ ጥናትና ምርምር ለማድረግ የሚመጡ ተገልጋዮች ከየትኛዉም መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ  ተቋማት ወይም ከትምህርት ተቋማት ህጋዊ  የትብብር ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

o   አገልግሎት የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት

                        ከሰኞ እስከ አርብ ከ2.30 እስከ 11.30

2.    የጥንታዊ ጽሑፎች አገልግሎት ክፍል

የእጅ ጽሑፎችንና የቆዩ የሕትመት የመረጃ ምንጮችን ለማንበብና መረጃ ለማግኘት ጥናትና ምርምር ለመስራት ለሚፈልጉ ተገልጋዮች አገልግሎት ይሰጣል፡፡

የጥንታዊ ስነጽሑፍ አገልግሎት መስጫ የሚገኘዉ በነባሩ ሕንጻ ላይ ሆኖ የማንበቢያ ክፍሉ ከክምችት ክፍል ጋር ጎን ለጎን የሚገኝ ነዉ፡፡ ይህ ክፍል ኤጀንሲዉ በ1936 ዓ.ም ሲቋቋም አብሮ ስራዉን የጀመረ ሲሆን አሁንም በክፍሉ የሚገኙ የመረጃ ምንጮች ጥንታዉያን የመረጃ ምንጮች ናቸዉ፡፡

እነሱም፡-

1.      ከ14ኛው  ክ/ዘ/ ጀምሮ ያሉ በብራና ላይ የተጻፉ

2.     ከዘመናዊ ወረቀት በፊት በነበሩ ልዩ  ልዩ የመጻፊያ ወረቀት መሰል ላይ የተጻፉ

3.     ኤጀንሲዉ በዓለም የስነጽሑፍ ቅርስነት በዩኔስኮ ካስመዘገባቸዉ 12 የስነ-ጽሑፍ ቅርሶች መካከል 

 • 14ኛዉ መ/ክ  ዐርባዕቱ ወንጌል
 • የ15ኛው  መ/ክ የጰዉሎስ መልዕክት
 • የ15ኛው  መ/ክ ግብረ ህማማት
 • በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ ህትም መዝሙረ-ዳዊት

ይዘትና የተጻፉበት ቋንቋ፡-

የመረጃ ምንጮቹ የተጻፉበት ቋንቋ ግዕዝ፣ አረብኛ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ ኦሮምኛና ሌሎችንም ያካተተ ሲሆን ይዘታቸዉም በሃይማኖት፣ በሀገር ዉስጥና በዓለም ላይ ያተኮረ ታሪክ፣ ሕግ፣ ቋንቋ ፣ ፖለቲካና የዉጭ ግንኙነት፣ የልዩ ልዩ ብሔረሰቦችና ሃይማኖቶች ታሪክ፣ ባህላዊ መድኃኒት፣ የአስማት ጽሑፎችና በመሳሰሉት ላይ የተኮሩ ናቸዉ፡፡

የአገልግሎት አይነት

 1. የንባብ፣ የጥናትና ምርምር አገልግሎት
 2. ስለ ብራና መጻሕፍትና ስለ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ጽሕፎች አጀማመር ታሪክ ጉብኝትና ገለጻ

 

o   አገልግሎት ፈላጊዎች ማሟላት የሚገባቸዉ ፡-

 1. ለንባብ እንዲሁም ጥናትና ምርምር ማድረግ ለሚፈልጉ ሕጋዊ  ከሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ወይም ከትምህርት ተቋማት ሕጋዊ የትብብር ደብዳቤ በማምጣት አገልግሎቱን ማግኛት ይችላሉ፡፡
 2. ተሰባስበዉ ጉብኝት ማድረግ የሚፈልጉ ከላይ ከተጠቀሱት ተቋማት ደብዳቤ በማምጣት እና ቀደም ብሎ በማሳወቅ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

o   አገልግሎት የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት

               ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30

 1. የማይክሮፊልም እና ቀረፀድምጽ አገልግሎት ክፍል  

በዚህ ክፍል የኢትዮጵያን ስነጽሑፍ ጥንታዊነት የሚያሳዩ ዕድሜያቸዉ ከአንድ ሺ ዓመት በላይ የሆኑ በብራና ላይ የተጻፉ ጥንታዉያን መጻሕፍት ከተለያዩ የሀገሪቱ ታላላቅ የታሪክና ስነጽሑፍ ቦታዎች ከሆኑ በማይክሮፊልም ተቀርጸዉ የመጡ  በክፍሉ ይገኛሉ፡፡ ቁጥራዉ ከ9500 በላይ ሲሆን   በማይክሮፊልም ላይ የሚገኙት ጥንታዉያን የጽሑፍ ሀብቶች ለተገልጋዮች አገልግሎት ከመስጠት በሻገር ዋና ቅጂዎች በተለያየ ምክንያት ጉዳት ቢደርስባቸዉና ቢጠፉ እንደምትክ ሆነዉ ያገለግላሉ፡፡ በክፍሉ ያሉት የፊልም ክምችቶች በፊት የኢትዮጵያ ብራና ጽሕፎችና የማይክሮ-ፊልም ላይብራሪ (EMML) ተብሎ ከሚጠራዉ ድርጅት በመዋቅር ምክንያት ወደ ኤጀንሲዉ የተዛወሩ ናቸዉ፡፡

o   በዚህ ክፍል የሚሰጡ አገልግሎቶች ፡-

 • ለማይክሮ-ፊልም በተዘጋጀ ዘመናዊ የማንበቢያ መሣሪያ የንባብ አገልግሎት መስጠት
 • ከማይክሮፊልም ላይ ጥያቄ ሲቀርብ በሕትመት ወይም በዲጂታል ኮፒ የቅጂ አገልግሎት መስጠት፡፡

o   አገልግሎት ፈላጊዎች ማሟላት የሚገባቸዉ ፡-

በክፍሉ ጥናት እና ምርምር ለማድረግ የሚመጡ ተገልጋዮች ከየትኛዉም መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ  ተቋማት ወይም ከትምህርት ተቋማት  ህጋዊ የትብብር ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 • አገልግሎት የሚሰጥበት ቀንና ሰዓት ፡-

         ከሰኞ እስካ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 

 

 

Last Modified: 10/12/2017

NALA News

Downloads